Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 49:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 “ሮቤል፥ ኀይልና የጐልማሳነት ብርታት በነበረኝ ጊዜ፥ የወለድኩህ የበኲር ልጄ ነህ። ከልጆቼ ሁሉ በክብርና በኀይል የምትበልጥ አንተ ነህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 “ሮቤል፣ አንተ የበኵር ልጄ ነህ፤ ኀይሌና የጕብዝናዬም መጀመሪያ፤ በክብር ትልቃለህ፤ በኀይልም ትበልጣለህ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሮቤል፥ አንተ በኩር ልጄና ኃይሌ፥ የጉብዝናዬም መጀመሪያ፥ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 “ሮቤል እርሱ የበ​ኵር ልጄና ኀይሌ፥ የል​ጆ​ችም መጀ​መ​ሪያ ነው፤ ክፉ ሆነ፤ አን​ገ​ቱ​ንም አደ​ነ​ደነ። ጭንቅ ነገ​ር​ንም አደ​ረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሮቤል አንተ በኵር ልጄና ኃይሌ የጕብዝናዬም መጀመሪያ ነህ፤ የክብር አለቃና የኃይል አለቃ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 49:3
17 Referencias Cruzadas  

ልያ ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እግዚአብሔር መከራዬን ተመለከተ፤ ከእንግዲህስ ወዲያ ባሌ ይወደኛል” ስትል ስሙን ሮቤል አለችው።


ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፥ ሮቤል ወደ አባቱ ቁባት ወደ ባላ ገባ። ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ። የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው።


የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮርና ዛብሎን ናቸው።


ከእስራኤል ጋር ወደ ግብጽ የወረዱት የእስራኤላውያን ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የያዕቆብ የበኲር ልጅ ሮቤል፥


“አባቴ ሆይ፥ እንደዚህ አይደለም፤ በኲሩ ይህኛው ስለ ሆነ ቀኝ እጅህን በእርሱ ራስ ላይ አኑር” አለው።


ያዕቆብ ዐሥራ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥


የያዕቆብ የበኲር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች ቀጥሎ የተመለከቱት ናቸው፤ (ሮቤል የአባቱን አልጋ ደፍሮ በማርከሱ የብኲርናውን መብት ስላጣ፥ ያ መብት ለዮሴፍ ተሰጥቶ ነበር፤


ከያዕቆብ ልጆች በኲር የሆነው ሮቤል አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ እነርሱም ሐኖክ፥ ፋሉ፥ ሔጽሮንና ካርሚ ተብለው የሚጠሩት ናቸው።


የእያንዳንዱን ግብጻዊ ቤተሰብ የበኲር ልጅ ገደለ።


የካምን ልጆች የመጀመሪያ የወንድነት ፍሬ፥ በግብጽ በኲሮችን ሁሉ ገደለ።


ሮቤል ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከኤፍሬም ይዞታ ጋር የሚዋሰን አንድ ድርሻ ይኖረዋል፤


ወታደር ሆነው ለማገልገል ችሎታ ያላቸው፥ ዕድሜአቸው ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆነ ወንዶች ከያዕቆብ ልጆች በኲር ከሆነው ከሮቤል ነገድ


የያዕቆብ የበኲር ልጅ የሮቤል ነገድ ተወላጆች ሐኖክ፥ ፋሉስ፥


ከማያፈቅራት ሚስቱ የተወለደ ቢሆንም እንኳ ለበኲር ልጁ የሚሰጠው ድርሻ ከሌሎቹ የነፍስ ወከፍ ድርሻ በእጥፍ ከፍ ያለ መሆን አለበት፤ ስለዚህም ያ ሰው ልጁ በመጀመሪያ በመወለዱ በኲር መሆኑን ተረድቶ የብኲርና ድርሻውን ሊሰጠው ይገባል።


ለእርግማንም በዔባል ተራራ ላይ መቆም የሚገባቸው የሮቤል፥ የጋድ፥ የአሴር፥ የዛብሎን፥ የዳንና የንፍታሌም ነገዶች ናቸው።


ሙሴ ሰለ ሮቤል ነገድ እንዲህ አለ፦ “ምንም እንኳ ብዛቱ ጥቂት ቢሆን፥ ጌታ ሆይ የሮቤል ነገድ ይኑር እንጂ አይሙት።”


“ለሎዶቅያ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፦ “ይህ፥ አሜን ከሆነው፥ ታማኝና እውነተኛ ምስክር ከሆነው፥ የእግዚአብሔር ፍጥረት ሁሉ መገኛ ከሆነው የተነገረ ነው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos