እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፥ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። አብራምም ለእርሱ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ መሠውያን ሠራ።
ዘዳግም 30:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እንዲሰጣቸው በማለላቸው በምድሪቱ ትቀመጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይወትህ፥ የዘመንህም ርዝመት ነውና አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው፤ ቃሉን ስማው፤ አጥናውም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም አምላክህን እግዚአብሔርን እንድትወድድ፣ ቃሉን እንድታደምጥና ከርሱ ጋራ እንድትጣበቅ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕይወትህ ነው፤ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር ረዥም ዕድሜ ይሰጥሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አምላክህን ውደደው፤ ለቃሉም ታዘዝ፤ ከእርሱም ጋር ተጣበቅ። ጌታ ለአባቶችህም ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር የዕድሜህም ዘመን ሕይወትም ማለት ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ፤ ለእርሱም ታዛዥ ሁን፤ በእርሱም እመን፤ ይህም ለአንተ ሕይወት ከመሆኑም በላይ ለቀድሞ አባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በመሐላ ቃል በገባላቸው መሠረት ገብተህ በምትኖርባት ምድር ለረጅም ዘመን ትኖራለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም እንዲሰጣቸው በማለላቸው በምድሪቱ ትቀመጥ ዘንድ፥ እርሱ ሕይወትህ የዘመንህም ርዝመት ነውና አምላክህን እግዚአብሔርን ትወድደው ትጠባበቀውም ቃሉንም ትሰማ ዘንድ ምረጥ። |
እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፥ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። አብራምም ለእርሱ ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ መሠውያን ሠራ።
ከዚህም በኋላ አብራም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው “በፊትህ የሄድሁ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ፤ በፊቴ መልካም አድርግ፤ ንጹሕም ሁን፤
አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ቸልም አትበለኝ። ቸል ብትለኝ ግን ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱት እሆናለሁ።
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “የእውነትና የሕይወት መንገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።
ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንህ አንተን፥ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት።
በደረሰ ጊዜም የእግዚአብሔርን ጸጋ አየና ደስ አለው፤ በፍጹም ልባቸውም በእግዚአብሔር ጸንተው ይኖሩ ዘንድ መከራቸው።
እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን፥ ሌላውንም ነገር ሁሉ ለሁሉ ይሰጣልና እንደ ችግረኛ የሰው እጅ አያገለግለውም።
እኛ በእርሱ ሕይወትን እናገኛለን፤ በእርሱም እንንቀሳቀሳለን፤ በእርሱም ጸንተን እንኖራለን፤ ከመካከላችሁም፦ ‘እኛ ዘመዶቹ ነን’ የሚሉ ፈላስፎች አሉ።
ከክርስቶስ ጋርም ተሰቀልሁ፤ ሕይወቴም አለቀች፤ ነገር ግን በክርስቶስ ሕይወት አለሁ፤ ዛሬም በሥጋዬ የምኖረውን ኑሮ የወደደኝን ስለ እኔም ራሱን አሳልፎ የሰጠውን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመን እኖራለሁ።
እነሆ፥ ምድሪቱን ሰጠኋችሁ፤ ግቡ፥ እግዚአብሔር ለእነርሱ፥ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውን ምድር ውረሱ።
“እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትወድድ ዘንድ፥ በፍጹምም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ ነው እንጂ፥
አምላካችሁን እግዚአብሔርን ትወድዱ ዘንድ፥ በመንገዱም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ እርሱንም ትከተሉ ዘንድ፥ ዛሬ ለእናንተ የማዝዘውን ትእዛዝ ሁሉ ብትጠብቁ ብታደርጉአትም፥
እግዚአብሔር ለእነርሱና ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ይሰጣቸው ዘንድ ለአባቶቻችሁ በማለላቸው ምድር ላይ ዕድሜያችሁ እንዲረዝም።
ዮርዳኖስን ግን በተሻገራችሁ ጊዜ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር በሚያወርሳችሁ ምድር በተቀመጣችሁ ጊዜ፥ ያለ ፍርሀትም እንድትኖሩ ከከበቡአችሁ ጠላቶች ሁሉ ዕረፍት በሰጣችሁ ጊዜ፥
ዛሬ እኔ የማዝዝህን የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ብትሰማ፥ አምላክህን እግዚአብሔርንም ብትወድድ፥ በመንገዶቹም ሁሉ ብትሄድ፥ ሥርዐቱንና ፍርዱንም ብትጠብቅ በሕይወት ትኖራለህ፤ በቍጥርም ትበዛለህ፤ አምላክህ እግዚአብሔርም ልትወርሳት በምትሄድባት በምድሪቱ ሁሉ ይባርክሃል።
በሕይወትም እንድትኖር፥ አምላክህን እግዚአብሔርንም በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ እንድትወድድ እግዚአብሔር ልብህን፥ የዘርህንም ልብ ያጠራዋል።
ይህ ነገር ሕይወታችሁ ነው እንጂ ለእናንተ ከንቱ አይደለምና፤ በዚህም ነገር ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር ዘመናችሁ ይረዝማል።”
“አሁንም እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው፥ በሕይወትም እንድትኖሩ፥ እንድትበዙም፥ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ ዛሬ የማስተምራችሁን ሥርዐትና ፍርድ ስሙ።
ለእናንተ፥ ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም ይሆን ዘንድ፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ለዘለዓለም በሚሰጣችሁ ምድር ዕድሜአችሁ ይረዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማዝዛችሁን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ጠብቁ።”
ጠብቁት፤ አድርጉትም፤ ይህን ሥርዐት ሁሉ ሰምተው፦ እነሆ፥ ‘ይህ ታላቅ ሕዝብ ጠቢብና አስተዋይ ሕዝብ ነው’ በሚሉ በአሕዛብ ፊት ጥበባችሁና ማስተዋላችሁ ይህ ነውና፤
እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህ አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ።
እናንተ፥ ልጆቻችሁም፥ የልጅ ልጆቻችሁም በዕድሜአችሁ ሁሉ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ፈርታችሁ እኔ ለእናንተ ያዘዝሁትን ሥርዐቱንና ትእዛዙን ሁሉ ትጠብቁ ዘንድ፥ ዕድሜአችሁም ይረዝም ዘንድ፤