Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


ዘፍጥረት 12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ​ራ​ምን እንደ ጠራው

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ራ​ምን አለው፥ “ከሀ​ገ​ርህ፥ ከዘ​መ​ዶ​ች​ህም፥ ከአ​ባ​ት​ህም ቤት ተለ​ይ​ተህ ውጣ፤ እኔ ወደ​ማ​ሳ​ይ​ህም ምድር ሂድ።

2 ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ቡሩ​ክም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ባ​ር​ኩ​ህ​ንም እባ​ር​ካ​ለሁ፤

3 የሚ​ረ​ግ​ሙ​ህ​ንም እረ​ግ​ማ​ለሁ፤ የም​ድር ነገ​ዶ​ችም ሁሉ በአ​ንተ ይባ​ረ​ካሉ።”

4 አብ​ራ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረው ሄደ፤ ሎጥም ከእ​ርሱ ጋር ሄደ፤ አብ​ራ​ምም ከካ​ራን በወጣ ጊዜ ሰባ አም​ስት ዓመት ሆኖት ነበረ።

5 አብ​ራ​ምም ሚስ​ቱን ሦራ​ንና የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገ​ኙ​ትን ከብት ሁሉና በካ​ራን ያገ​ኙ​አ​ቸ​ውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነ​ዓን ምድር ለመ​ሄድ ወጣ፤ ወደ ከነ​ዓ​ንም ምድር ገቡ።

6 አብ​ራ​ምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ታላቁ ዛፍ ድረስ በዚ​ያች ምድር አለፈ፤ የከ​ነ​ዓን ሰዎ​ችም በዚ​ያን ጊዜ በዚ​ያች ምድር ነበሩ።

7 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ብ​ራም ተገ​ለ​ጠ​ለ​ትና፥ “ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ለሁ” አለው። አብ​ራ​ምም ለእ​ርሱ ለተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ መሠ​ው​ያን ሠራ።

8 ከዚ​ያም በቤ​ቴል ምሥ​ራቅ ወዳ​ለው ተራራ ወጣ፤ በዚ​ያም ቤቴ​ልን ወደ ምዕ​ራብ፥ ጋይን ወደ ምሥ​ራቅ አድ​ርጎ ድን​ኳ​ኑን ተከለ፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያን ሠራ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም ጠራ።

9 አብ​ራ​ምም ከዚያ ተነሣ፤ እየ​ተ​ጓ​ዘም ወደ አዜብ ሄደ፤ በዚ​ያም ኖረ።


የአ​ብ​ራም እን​ግ​ድ​ነት በግ​ብፅ

10 በም​ድ​ርም ራብ ሆነ፤ አብ​ራ​ምም በዚያ በእ​ን​ግ​ድ​ነት ይቀ​መጥ ዘንድ ወደ ግብፅ ወረደ፤ በም​ድር ራብ ጠንቶ ነበ​ረና።

11 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አብ​ራም ወደ ግብፅ ለመ​ግ​ባት በቀ​ረበ ጊዜ ሚስ​ቱን ሦራን እን​ዲህ አላት፥ “አንቺ መልከ መል​ካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አው​ቃ​ለሁ፤

12 የግ​ብፅ ሰዎች ያዩሽ እንደ ሆነ ሚስቱ ናት ይላሉ፤ እኔ​ንም ይገ​ድ​ሉ​ኛል፤ አን​ቺ​ንም በሕ​ይ​ወት ይተ​ዉ​ሻል።

13 እን​ግ​ዲህ በአ​ንቺ ምክ​ን​ያት መል​ካም ይሆ​ን​ልኝ ዘንድ፥ ስለ አን​ቺም ነፍሴ ትድን ዘንድ እኅቱ ነኝ በዪ።”

14 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አብ​ራም ወደ ግብፅ በገባ ጊዜ የግ​ብፅ ሰዎች ሴቲ​ቱን እጅግ ውብ እንደ ሆነች አዩ፤

15 የፈ​ር​ዖ​ንም አለ​ቆች አዩ​አት፤ በፈ​ር​ዖ​ንም ፊት አደ​ነ​ቁ​አት፤ ወደ ፈር​ዖን ቤትም ወሰ​ዱ​አት።

16 ለአ​ብ​ራ​ምም ስለ እር​ስዋ መል​ካም አደ​ረ​ጉ​ለት፤ ለእ​ርሱ በጎ​ችም፥ በሬ​ዎ​ችም፥ አህ​ዮ​ችም፥ በቅ​ሎ​ዎ​ችም፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችም፥ ግመ​ሎ​ችም ነበ​ሩት።

17 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ብ​ራም ሚስት በሦራ ምክ​ን​ያት ፈር​ዖ​ን​ንና የቤ​ቱን ሰዎች በታ​ላቅ መቅ​ሠ​ፍት መታ።

18 ፈር​ዖ​ንም አብ​ራ​ምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብኝ ምን​ድን ነው? እር​ስዋ ሚስ​ትህ እንደ ሆነች ለምን አል​ገ​ለ​ጥ​ህ​ል​ኝም?

19 ለም​ንስ ‘እኅቴ ናት’ አልህ? ለእኔ ሚስት ትሆ​ነኝ ዘንድ ወስ​ጃት ነበር። አሁ​ንም እነ​ኋት፥ ሚስ​ትህ በፊ​ትህ ናት፤ ይዘ​ሃ​ትም ሂድ።”

20 ፈር​ዖ​ንም ሰዎ​ቹን ስለ አብ​ራም አዘዘ፤ እር​ሱ​ንም፥ ሚስ​ቱ​ንም፥ የነ​በ​ረ​ው​ንም ሁሉ ሸኙ​አ​ቸው።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos