Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 27:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አቤቱ፥ አም​ላኬ ሆይ፥ ወደ አንተ እጮ​ኻ​ለሁ፤ ቸልም አት​በ​ለኝ። ቸል ብት​ለኝ ግን ወደ ጕድ​ጓድ እን​ደ​ሚ​ወ​ር​ዱት እሆ​ና​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኅኔ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር ለሕይወቴ ዐምባዋ ነው፤ ማንን እፈራለሁ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሳይቀባ፥ የዳዊት መዝሙር። ጌታ ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፥ የሚያስፈራኝ ማን ነው? ጌታ የሕይወቴ ከለላዋ ነው፥ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ብርሃኔና ደኅንነቴ ስለ ሆነ ማንንም አልፈራም እግዚአብሔር የሕይወቴ ከለላ ስለ ሆነ የሚያስፈራኝ ማነው?

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 27:1
45 Referencias Cruzadas  

አሁ​ንም አም​ነን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይረ​ዳ​ኛል፥ አል​ፈ​ራም፥ ሰው ምን ያደ​ር​ገ​ኛል?” እን​በል።


ትእ​ዛ​ዝ​ህን ሁሉ ስመ​ለ​ከት በዚ​ያን ጊዜ አላ​ፍ​ርም።


እኔን ለማ​ዳን ረዳ​ትና ሰዋሪ ሆነኝ፤ ይህ አም​ላኬ ነው፤ አመ​ሰ​ግ​ነ​ው​ማ​ለሁ፤ የአ​ባቴ አም​ላክ ነው፤ ከፍ ከፍም አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


እር​ሱም፥ “ጸጋዬ ይበ​ቃ​ሀል፤ ኀይ​ልስ በደዌ ያል​ቃል” አለኝ፤ የክ​ር​ስ​ቶ​ስም ኀይል በእኔ ላይ ያድር ዘንድ በመ​ከ​ራዬ ልመካ ወደ​ድሁ።


ቅን​ነት ከም​ድር በቀ​ለች፥ ጽድ​ቅም ከሰ​ማይ ተመ​ለ​ከተ።


እን​ግ​ዲህ ስለ​ዚህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይች​ለ​ናል?


ዳግ​መ​ኛም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፥ “የዓ​ለም ብር​ሃን እኔ ነኝ፤ የሚ​ከ​ተ​ለኝ የሕ​ይ​ወት ብር​ሃ​ንን ያገ​ኛል እንጂ በጨ​ለማ ውስጥ አይ​መ​ላ​ለ​ስም” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።


እነሆ፥ አም​ላኬ መድ​ኀ​ኒቴ ነው፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ሬና ዝማ​ሬዬ ነው፤ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ሆኖ​አ​ልና በእ​ርሱ ታም​ኜ​አ​ለሁ፤ አል​ፈ​ራ​ምም።”


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅግ ደስ ይላ​ቸ​ዋል። ነፍ​ሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች። ሽል​ማ​ትን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽል​ማ​ቷም እን​ዳ​ጌ​ጠች ሙሽራ፥ የማ​ዳ​ንን ልብስ አል​ብ​ሶ​ኛ​ልና፥ የደ​ስ​ታ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ደር​ቦ​ል​ኛ​ልና።


በመ​ኝ​ታ​ዬም አስ​ብ​ሃ​ለሁ፥ በማ​ለ​ዳም እና​ገ​ር​ል​ሃ​ለሁ፤


በራ​ስ​ጌዬ ላይ መብ​ራቴ በበራ ጊዜ፥ እኔም ጨለ​ማ​ውን ዐልፌ በብ​ር​ሃኑ በሄ​ድሁ ጊዜ፥


በሚ​ያ​ስ​ች​ለኝ በክ​ር​ስ​ቶስ ሁሉን እች​ላ​ለሁ።


ከት​እ​ዛ​ዛ​ትህ የሚ​ርቁ ርጉ​ማን ናቸው።


ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር።


ኀይ​ል​ህ​ንና ክብ​ር​ህን ዐውቅ ዘንድ እን​ዲሁ በመ​ቅ​ደስ ውስጥ ተመ​ለ​ከ​ት​ሁህ።


ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፣ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።


አሁ​ንም የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ፥ ኑ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብር​ሃን እን​መ​ላ​ለስ።


ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣሉ።


ለሰው ሁሉ የሚ​ያ​በ​ራው እው​ነ​ተ​ኛው ብር​ሃ​ንስ ወደ ዓለም የመ​ጣው ነው።


በታላቅም ድምፅ እየጮሁ “ማዳን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው የአምላካችንና የበጉ ነው!” አሉ።


ዐይ​ኖች ትድ​ግ​ና​ህን አይ​ተ​ዋ​ልና።


አቤቱ፥ አድ​ነኝ፥ ደግ ሰው አል​ቆ​አ​ልና፥ ከሰው ልጆ​ችም መተ​ማ​መን ጐድ​ሎ​አ​ልና።


ማዳን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ በረ​ከ​ት​ህም በሕ​ዝ​ብህ ላይ ነው።


ሰውም ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትድ​ግና ይይ።”


እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ስለ ምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸ፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።


ክብ​ርና ጽድቅ ወደ እርሱ ይመ​ጣሉ፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ርቁ ሁሉ ያፍ​ራሉ።


እጅህ ጠላ​ትን አጠ​ፋች፥ እነ​ር​ሱ​ንም ተከ​ልህ፤ አሕ​ዛ​ብን አሠ​ቃ​የ​ኻ​ቸው፥ አሳ​ደ​ድ​ኻ​ቸ​ውም።


ነገር ግን አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ር​ዖ​ንና በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ሁሉ ያደ​ረ​ገ​ውን ፈጽ​መህ አስብ፤


ከፊ​ታ​ቸው አት​ደ​ን​ግጥ፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከአ​ንተ ጋር ነውና፥ እር​ሱም አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላ​ቅና ጽኑዕ ነውና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እንደ ኀያል ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለ​ዚህ አሳ​ዳ​ጆች ይሰ​ና​ከ​ላሉ፤ አያ​ሸ​ን​ፉም፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም የማ​ይ​ረሳ ጕስ​ቍ​ል​ና​ቸ​ውን አላ​ወ​ቁ​ምና ፈጽ​መው አፈሩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios