Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 37 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለሰ​ን​በት መታ​ሰ​ቢያ የዳ​ዊት መዝ​ሙር።

1 አቤቱ፥ በመ​ዓ​ትህ አት​ቅ​ሠ​ፈኝ፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም አት​ገ​ሥ​ጸኝ።

2 ፍላ​ጾ​ችህ ወግ​ተ​ው​ኛ​ልና፥ እጅ​ህ​ንም በእኔ ላይ አክ​ብ​ደ​ህ​ብ​ኛ​ልና።

3 ከቍ​ጣህ ፊት የተ​ነሣ ለሥ​ጋዬ ድኅ​ነት የለ​ውም፤ ከኀ​ጢ​አ​ቴም ፊት የተ​ነሣ ለአ​ጥ​ን​ቶቼ ሰላም የላ​ቸ​ውም።

4 ኀጢ​አቴ ከራሴ ጠጕር በዝ​ቷ​ልና፥ እንደ ከባድ ሸክ​ምም በላዬ ከብ​ዶ​አ​ልና።

5 ከስ​ን​ፍ​ና​ዬም ፊት የተ​ነሣ አጥ​ን​ቶቼ ሸተቱ፥ በሰ​በ​ሱም፤

6 እጅግ ጐሰ​ቈ​ልሁ፥ ጐበ​ጥ​ሁም፥ ሁል​ጊ​ዜም በት​ካዜ እመ​ላ​ለ​ሳ​ለሁ፤

7 ነፍሴ ስድ​ብን ጠግ​ባ​ለ​ችና፥ ለሥ​ጋ​ዬም ድኅ​ነ​ትን አጣሁ።

8 ታመ​ምሁ እጅ​ግም ተሠ​ቃ​የሁ፥ ከል​ቤም ኀዘን የተ​ነሣ እጮ​ኻ​ለሁ።

9 አቤቱ፥ ፈቃዴ ሁሉ በፊ​ትህ ነው፥ ጩኸ​ቴም ከአ​ንተ አይ​ሰ​ወ​ርም።

10 ልቤ ደነ​ገ​ጠ​ብኝ፥ ኀይ​ሌም ተወኝ፥ የዐ​ይ​ኖ​ቼም ብር​ሃን ፈዘ​ዘ​ብኝ።

11 ወዳ​ጆቼም ባል​ን​ጀ​ሮ​ቼም ባላ​ጋራ ሆኑኝ፥ ከበ​ውም ደበ​ደ​ቡኝ፥ ዘመ​ዶቼም ተስፋ ቈር​ጠው ተለ​ዩኝ።

12 ነፍ​ሴ​ንም የሚ​ሹ​አት በረ​ቱ​ብኝ፥ መከ​ራ​ዬ​ንም የሚ​ፈ​ልጉ ከን​ቱን ተና​ገሩ፥ ሁል​ጊ​ዜም ያጠ​ፉኝ ዘንድ በሽ​ን​ገላ ይመ​ክ​ራሉ።

13 እኔ ግን እን​ደ​ማ​ይ​ሰማ ደን​ቆሮ፥ አፉ​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ከ​ፍት ዲዳ ሆንሁ።

14 እን​ደ​ማ​ይ​ሰማ ሰው፥ በአ​ፉም መና​ገር እን​ደ​ማ​ይ​ችል ሰው ሆንሁ።

15 አቤቱ፥ በአ​ንተ ታም​ኛ​ለ​ሁና፤ አቤቱ አም​ላኬ፥ አንተ ስማኝ።

16 የጠ​ላ​ቶቼ መዘ​ባ​በቻ አታ​ድ​ር​ገኝ ብያ​ለ​ሁና፥ እግ​ሬም ቢሰ​ና​ከል በእኔ ላይ ብዙ ነገ​ርን ይና​ገ​ራሉ።

17 እኔ​ንስ ይገ​ር​ፉኝ ዘንድ አቈ​ዩኝ፥ ቍስሌ ሁል​ጊዜ በፊቴ ነውና።

18 በደ​ሌን እና​ገ​ራ​ለ​ሁና፥ ስለ ኀጢ​አ​ቴም እተ​ክ​ዛ​ለሁ።

19 ጠላ​ቶቼ ሕያ​ዋን ናቸው፥ ይበ​ረ​ቱ​ብ​ኛ​ልም፥ በዐ​መ​ፃም የሚ​ጠ​ሉኝ በዙ።

20 በበጎ ፋንታ ክፉን የሚ​መ​ል​ሱ​ልኝ ጽድ​ቅን ስለ ተከ​ተ​ልሁ ይከ​ስ​ሱ​ኛል። እንደ ርኩስ በድን ወን​ድ​ማ​ቸ​ውን ጣሉ፥

21 አቤቱ፥ አንተ አት​ጣ​ለኝ፤ አም​ላኬ፥ ከእኔ አት​ራቅ።

22 አቤቱ፥ የመ​ድ​ኀ​ኒቴ አም​ላክ ሆይ፥ እኔን ለመ​ር​ዳት ፍጠን።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos