ዘፍጥረት 35:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮርና ዛብሎን ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልያ ልጆች፦ የያዕቆብ የበኵር ልጅ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ በኩር ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የልያ ልጆች፤ የያዕቆብ በኵር ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የያዕቆብም ልጆች አሥራ ሁለት ናቸው የልያ ልጆች የያዕቆብ በኵር ልጅ ሮቤል ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፤ |
በመጀመሪያ ሁለቱን ሴቶች አገልጋዮቹንና ልጆቻቸውን አስቀደመ፤ ቀጥሎ ልያንና ልጆችዋን አስከተለ፤ በመጨረሻም ራሔልንና ዮሴፍን ከሁሉ በኋላ አደረገ።
የእስራኤል ነገዶች አስተዳዳሪዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ የሮቤል ነገድ አስተዳዳሪ፦ የዚክሪ ልጅ ኤሊዔዘር የስምዖን ነገድ አስተዳዳሪ፦ የማዕካ ልጅ ሸፋጥያ የሌዊ ነገድ አስተዳዳሪ፦ የቀሙኤል ልጅ ሐሻብያ የአሮን ነገድ አስተዳዳሪ፦ ሳዶቅ የይሁዳ ነገድ አስተዳዳሪ፦ ከንጉሥ ዳዊት ወንድሞች አንዱ የሆነው ኤሊሁ የይሳኮር ነገድ አስተዳዳሪ፦ የሚካኤል ልጅ ዖምሪ የዛብሎን ነገድ አስተዳዳሪ፦ የአብድዩ ልጅ ዩሽማዕያ የንፍታሌም ነገድ አስተዳዳሪ፦ የዐዝርኤል ልጅ ያሪሞት የኤፍሬም ነገድ አስተዳዳሪ፦ የዐዛዝያ ልጅ ሆሴዕ የምዕራባዊ የምናሴ ነገድ እኩሌታ አስተዳዳሪ፦ የፐዳያ ልጅ ኢዮኤል የምሥራቃዊ የምናሴ ነገድ እኩሌታ አስተዳዳሪ፦ የዘካርያስ ልጅ ዩዶ የብንያም ነገድ አስተዳዳሪ፦ የአበኔር ልጅ ያዕሲኤል የዳን ነገድ አስተዳዳሪ፦ የይሮሐም ልጅ ዐዛርኤል።
የከተማይቱ መውጫ በሮች አራት ማእዘኖች የሚከተሉት ናቸው፦ በየማእዘኑ ሦስት በሮች ሲኖሩ ለያንዳንዱ በር የአንድ ነገድ ስም ተሰጥቶታል። በሰሜን በኩል አራት ሺህ አምስት መቶ ክንድ ርዝመት አለው። በዚህ ማእዘን ያሉት ሦስት በሮች በሮቤል፥ በይሁዳና በሌዊ ስም ተሰይመዋል።
የመገረዝንም ኪዳን ሰጠው፤ ስለዚህ አብርሃም ይስሐቅን በወለደ ጊዜ በስምንተኛው ቀን ገረዘው፤ እንዲሁም ይስሐቅ ልጁን ያዕቆብን ገረዘው። ያዕቆብም የነገድ አባቶች የሆኑትን ዐሥራ ሁለቱን ልጆቹን ገረዘ።
ቀድሞ ዐማሌቃውያን ይኖሩበት ከነበረው ከኤፍሬም ወታደሮች መጡ፤ ሌሎችም ከብንያም መጡ። ከማኪር መሪዎች፥ ከዛብሎንም በትረ መንግሥትን የሚይዙ መጡ።
የይሳኮር መሪዎች ከዲቦራ ጋር መጡ፤ አዎ፥ ይሳኮርም ባራቅም መጡ፤ ወደ ሸለቆው ተከተሉት፤ ነገር ግን የሮቤል ነገድ ለሁለት ተከፈለ፤ ለመምጣት ወይም ላለመምጣት አመነታ።
በአደባባይ ተቀምጠው የነበሩት ሽማግሌዎችና ሌሎችም ሰዎች እንዲህ አሉ፥ “አዎ፥ እኛ ለዚህ ነገር ምስክሮች ነን፤ እግዚአብሔር ይህችን ሚስትህን ብዙ ልጆችን በመውለድ የያዕቆብን ቤት እንደ መሠረቱት እንደ ራሔልና እንደ ልያ ያድርግልህ፤ እግዚአብሔር በኤፍራታ ያበልጽግህ፤ በቤተልሔምም ዝነኛ ያድርግህ፤