ኢያሱ 15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉምለይሁዳ ነገድ ርስት ሆኖ የተመደበ ምድር 1 የይሁዳ ነገድ ድርሻ በየወገናቸው እስከ ኤዶም ድንበር፥ ወደ ጺን ምድረ በዳ እስከ ደቡብ መጨረሻ ይደርሳል። 2 ደቡባዊው ድንበራቸው እስከ ጨው ባሕር መጨረሻ ወደ ደቡብ ትይዩ እስከ ሆነው እስከ ልሳነ ምድሩ ነበር። 3 ወደ ደቡብ አቅጣጫ ከዐቅራቢም መተላለፊያ እስከ ጺን ይደርሳል፤ በቃዴስ በርኔ ደቡብም በኩል ሔጽሮንን አልፎ ወደ አዳር ከፍ ይልና ወደ ቃርቃ አቅጣጫ ይታጠፋል። 4 ወደ ዓጽሞንም በመዝለቅ፥ በግብጽ ድንበር ላይ የሚገኘው ወንዝ፥ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ይከተላል፤ ያም የድንበሩ መጨረሻ ይሆናል፤ እንግዲህ በደቡብ በኩል የይሁዳ ድንበር ይህ ነው። 5 በምሥራቅ በኩልም ያለው ድንበር እስከ ጨው ባሕር፥ እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ መጨረሻ ነበር። በሰሜንም በኩል ያለው ድንበር ከዮርዳኖስ ወንዝ መጨረሻና ከባሕሩ ልሳነ ምድር 6 እስከ ቤትሆግላ ይወጣል፤ ከዚያም በሰሜን በዮርዳኖስ ሸለቆ በኩል አልፎ የሮቤል ልጅ ወደ ሆነው ወደ ቦሐን መታሰቢያ ድንጋይ ድረስ ይወጣል። 7 ድንበሩም ከአኮር ሸለቆ ተነሥቶ ወደ ዳቢር ይወጣል፤ በሰሜን በኩልም አድርጎ ወደ ጌልጌላ ይመለሳል፤ እርሱ ከአዱሚም ትይዩ ይኸውም ከሸለቆው በደቡብ በኩል ነው፤ ስለዚህ ድንበሩ በኤንሼሜሽ ምንጭ በኩል ያልፋል፤ መጨረሻውም ኤን ሮጌል ነው። 8 ድንበሩ በሔኖም ልጅ ሸለቆ ከደቡብ ዝቅተኛ ቦታ የኢያቡሳውያን ከተማ በሆነችው በኢየሩሳሌም በኩል ከሔኖም ሸለቆ ፊት ለፊት እስካለው ተራራ ጫፍ ድረስ በመዝለቅ በሰሜን በኩል ወደ ሬፋይም ሸለቆ ይደርሳል። 9 ከዚያም ድንበሩ ከተራራው ጫፍ ተነሥቶ ወደ ኔፍቶሐ ምንጮች ይደርሳል፤ ወደ ዔፍሮንም ተራራ ከተሞች ይወጣል፤ ወደ ባዓላ ወይም ቂርያት ይዓሪም ይታጠፋል፤ 10 ድንበሩም በበዓላ ዙሪያ በስተምዕራብ በኩል ወደ ኤዶም ተራራ ይዞራል፤ በይዓሪም ወይም ክሳሎን ተብሎ ወደሚጠራው ተራራ ቊልቊለት በኩል አድርጎ ያልፋል፤ ወደ ቤትሼሜሽም ይወርዳል፤ በቲምናም በኩል ያልፋል። 11 ይኸው ድንበር በዔቅሮን ሰሜናዊ ኮረብታ ከፍ በማለት ወደ ሺከሮን አቅጣጫ ይታጠፍና የባዓላን ኮረብታና እንዲሁም ያብኒኤልን አልፎ ይሄዳል፤ መጨረሻውም የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል፤ 12 የምዕራባዊው ዳርቻ እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕርና ጠረፉ ድረስ ነው፤ ይህም የይሁዳ ልጆች እንደየወገናቸው ዙሪያ ድንበራቸው ነው። ካሌብ ኬብሮንና ደቢርን ድል አድርጎ መያዙ ( መሳ. 1፥11-15 ) 13 እግዚአብሔር ኢያሱን ባዘዘው መሠረት ለይፉኔ ልጅ ለካሌብ ከይሁዳ ነገድ ኪርያት ዐርባን ወይም ኬብሮን እርስት አድርጎ ሰጠው። (አርባ የዐናቅ አባት ነበር) 14 ካሌብም የዐናቅን ሦስት ልጆች ሼሻይን፥ አሒማንና ታልማይን አባረረ፤ እነርሱም የዐናቅ ዘሮች ነበሩ። 15 ከዚያም ተነሥቶ በደቢር በሚኖሩት ሕዝብ ላይ አደጋ ለመጣል ሄደ፤ ይህች ከተማ ቀድሞ ቂርያትሴፌር ተብላ ትጠራ ነበር፤ 16 ካሌብም፥ “ቂርያትሴፌርን ወግቶ ለሚይዛት ሰው ልጄን ዓክሳን እድርለታለሁ” ብሎ ተናገረ፤ 17 ስለዚህም የካሌብ ወንድም ከሆነው ከቀናዝ የተወለደው ዖትኒኤል ያችን ከተማ ወግቶ ያዘ፤ ካሌብም ልጁን ዓክሳን ዳረለት፤ 18 ዖትኒኤልም በሠርጋቸው ቀን ዓክሳን ከአባትዋ የእርሻ መሬት እንድትለምን መከራት፤ እርስዋም ከበቅሎዋ ላይ ወረደች፤ (መሳ 1፥14 ተመልከት) ካሌብም “ምን ትፈልጊአለሽ” ሲል ጠየቃት፤ 19 እርስዋም “የሰጠኸኝ ምድር ደረቅ ስለ ሆነ ጥቂት የውሃ ጒድጓዶች እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ” አለችው። ካሌብም ከላይና ከታች በኩል ያሉትን ሁለቱን የውሃ ምንጮች ሰጣት። የይሁዳ ከተሞች 20 የይሁዳ ነገድ በየወገናቸው የተቀበሉት የርስት ድርሻ ይህ ነው፤ 21 በስተደቡብ በኤዶም ዳርቻ ያሉት የይሁዳ ነገድ ከተሞች ቃብዱኤል፥ ዔዴርና ያጉር ናቸው። 22 ቂና፥ ዲሞና፥ ዓድዓዳ፥ 23 ቃዴስ፥ ሐጾር፥ ይትናን፥ 24 ዚፍ፥ ጤሌም፥ በዓሎት፥ 25 ሐጾርሐዳታ፥ ቂርዮትሔጽሮን ወይም ሐጾር፥ 26 አማም፥ ሸማዕ፥ ሞላዳ፥ 27 ሐጻርጋዳ፥ ሔሽሞን፥ ቤትጳሌጥ፥ 28 ሐጻርሹዓል፥ ቤርሳቤህ፥ ቢዝዮትያ፥ 29 በዓላ፥ ዒዩም፥ ዔጼም፥ 30 ኤልቶላድ፥ ከሲል፥ ሖርማ፥ 31 ጺቅላግ፥ ማድማና፥ ሳንሳና፥ 32 ልባዎት፥ ሺልሒም፥ ዓይንና፥ ሪሞን ተብለው የሚጠሩት በድምሩ ኻያ ዘጠኝ ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙት ታናናሽ ከተሞችንም ሁሉ ያጠቃልላሉ። 33 በቆላማው ቦታ ያሉትም ከተሞች ኤሽታኦል፥ ጾርዓ፥ አሽና፥ 34 ዛኖሐ፥ ዔንጋኒም፥ ታፑሐ፥ ዔናም፥ 35 ያርሙት፥ ዐዱላም፥ ሶኮህ፥ ዐዜቃ፥ 36 ሻዕራይም፥ ዐዲታይም፥ ገዴራና ገዴሮታይም ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ አራት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው የሚገኙ ታናናሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልላል። 37 እንዲሁም ጽናን፥ ሐዳሻ፥ ሚግዳልጋድ፥ 38 ዲልዓን፥ ምጽጳ፥ ዮቅጥኤል፥ 39 ላኪሽ፥ ቦጽቃት፥ ዔግሎን፥ 40 ካቦን፥ ላሕማስ፥ ኪትሊሽ፥ 41 ገዴሮት፥ ቤትዳጎን፥ ናዕማና ማቄዳ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ ስድስት ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትን ታናናሽ ከተሞችን ሁሉ ያጠቃልላል። 42 ከነዚህም ሁሉ ጋር ሊብና፥ ዔቴር፥ ዐሻን፥ 43 ይፍታሕ፥ አሽና፥ ነጺብ፥ 44 ቀዒላ፥ አክዚብና፥ ማሬሻ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዘጠኝ ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትንም ታናናሽ ከተሞች ያጠቃልላሉ። 45 በዚያም ከታናናሽ ከተሞችዋና መንደሮችዋ ጋር ዔቅሮን የምትባል ከተማ ነበረች፤ 46 በአሽዶድም አቅራቢያ ከዔቅሮን እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር የተሠሩ ከተሞችና መንደሮቻቸው ነበሩ። 47 እንዲሁም በግብጽ ወሰን እስከሚገኘው ወንዝና እስከ ሜዲቴራኒያን ባሕር ጠረፍ ድረስ የሚደርሱ ታናናሽ ከተሞችና መንደሮች ያሉአቸው አሽዶድና ጋዛ ተብለው የሚጠሩ ከተሞች ነበሩ። 48 በኮረብታማውም አገር ሻሚር፥ ያቲር፥ ሶኮህ፥ 49 ዳና፥ ቂርያትሴፌር ወይም ደቢር፥ 50 ዐናብ፥ ኤሽተሞዓ፥ ዐኒም፥ 51 ጎሼን፥ ሖሎንና ጊሎ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥራ አንድ ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትንም ትናንሽ ከተሞችን ያጠቃልላሉ። 52 ደግሞም አራብ፥ ዱማ፥ ኤሽዓን፥ 53 ያኒም፥ ቤትታፑሐ፥ አፌቃ፥ 54 ሑምጣ፥ ኬብሮንና ጺዖር ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዘጠኝ ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትን መንደሮች ያጠቃልላሉ። 55 ከእነዚህም ሌላ ማዖን፥ ቀርሜሎስ፥ ዚፍ፥ ዩጣ፥ 56 ኢይዝራኤል፥ ዮቅድዓም፥ ዛኖሐ፥ 57 ቃይን፥ ጊብዓና ቲምና ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ዐሥር ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው ያሉትን ትናንሽ ከተሞችን ያጠቃልላሉ። 58 እንዲሁም ሐልሑል፥ ቤትጹር፥ ጌዶር፥ 59 ማዕራት፥ ቤትዓኖትና ኤልትቆን ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ስድስት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው ያሉትን መንደሮች ያጠቃልላሉ። 60 ደግሞም ቂርያትባዓል ወይም ቂርያትይዓሪምና ራባ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ከተሞች ሲሆኑ፥ በዙሪያቸው ያሉትን ትናንሽ ከተሞችን ይጨምራሉ። 61 ከእነዚህም ሁሉ ጋር በበረሓማው ምድር ቤትዐራባ፥ ሚዲን፥ ሴካካ፥ 62 ኒብሻን፥ የጨው ከተማና ዔንገዲ ተብለው የሚጠሩ በድምሩ ስድስት ከተሞች ሲሆኑ በዙሪያቸው የሚገኙትን መንደሮች ያጠቃልላሉ። 63 ነገር ግን የይሁዳ ሕዝብ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ማባረር አልቻሉም፤ ስለዚህም ኢያቡሳውያን እስከ አሁን ድረስ በኢየሩሳሌም ከይሁዳ ሕዝብ ጋር ይኖራሉ። |