Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 2:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ፀሐይ በሚወጣበት በስተምሥራቅ በኩል የሚሰፍሩት በይሁዳ ሥር የተመደቡት ነገዶች ናቸው። የይሁዳ ነገድ መሪም የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በምሥራቅ በኩል በፀሓይ መውጫ፤ የይሁዳ ምድብ፤ በየሰራዊቱና በዐርማቸው ሥር ይስፈር፤ የይሁዳ ሕዝብ አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በምሥራቅ በኩል ወደ ፀሐይ መውጫ የሚሰፍሩት እንደ ሠራዊቶቻቸው የይሁዳን ሰፈር ዓላማ የያዙት ይሆናሉ፤ የይሁዳ ልጆችም አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በመ​ጀ​መ​ሪያ በም​ሥ​ራቅ በኩል የሚ​ሰ​ፍ​ሩት ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር የይ​ሁዳ ሰፈር ሰዎች ይሆ​ናሉ፤ የይ​ሁዳ ልጆ​ችም አለቃ የአ​ሚ​ና​ዳብ ልጅ ነአ​ሶን ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በምሥራቅ በኩል ወደ ፀሐይ መውጫ የሚሰፍሩት እንደ ሠራዊቶቻቸው የይሁዳ ሰፈር ዓላማ ሰዎች ይሆናሉ፤ የይሁዳ ልጆችም አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 2:3
19 Referencias Cruzadas  

ያዕቆብ በዚያ ምድር ሲኖር ሳለ፥ ሮቤል ወደ አባቱ ቁባት ወደ ባላ ገባ። ያዕቆብም ይህን ነገር ሰማ። የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው።


የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ የመጀመሪያ ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮርና ዛብሎን ናቸው።


አራም የአሚናዳብ አባት ነበር፤ አሚናዳብም የይሁዳ ልጆች አለቃ የሆነው ነአሶንን ወለደ።


ይሁን እንጂ ከሁሉም ይበልጥ ብርቱ የሆነና ለነገዶች ሁሉ መሪ የሚሆን ሰው የሚገኝበት የይሁዳ ነገድ ነበር፤)


አሮን የነአሶን እኅት የሆነችውን የዓሚናዳብን ልጅ ኤሊሼባን አገባ፤ እርስዋም ናዳብ፥ አቢሁ፥ አልዓዛርና ኢታማር የተባሉትን ወንዶች ልጆች ወለደችለት።


የሚረዱአችሁ ሰዎች ስም የሚከተሉት ናቸው፦ ከሮቤል የሸዴኡር ልጅ ኤሊጹር


ከይሁዳ የዓሚናዳብ ልጅ ነአሶን


በአንድ መለከት ረዘም ላለ ጊዜ የማስጠንቀቂያ ድምፅ ሲሰማ በስተ ምሥራቅ የሰፈሩት ነገዶች ጒዞ ይጀምሩ።


የእርሱም ክፍል የሰው ብዛት ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነበር።


በመገናኛው ድንኳን በስተምሥራቅ፥ በፀሐይ መውጫ በኩል የሚሰፍሩት ሙሴ አሮንና የአሮን ልጆች ነበሩ፤ በመቅደሱ ውስጥ ስለ እስራኤል ሕዝብ ለሚፈጸም ማንኛውም ዐይነት የአገልግሎት ሥነ ሥርዓት ኀላፊዎች እነርሱ ነበሩ፤ ማንም ሌላ ሰው ወደ መቅደሱ ቢቀርብ በሞት ይቀጣል።


በመጀመሪያው ቀን መባውን ያቀረበው ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበረ፤


ለአንድነት መሥዋዕት ሁለት በሬዎች፥ አንድ ዓመት ዕድሜ ያላቸው፥ አምስት ተባት ፍየሎችና አምስት ተባት በጎች ይህ የአሚናዳብ ልጅ የነአሶን መባ ነበረ። የሚከተሉት ሌሎቹም ልክ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ያቀረበውን ዝርዝር አቅርበዋል።


አራም ዓሚናዳብን ወለደ፤ ዓሚናዳብ ነአሶንን ወለደ፤ ነአሶን ሰልሞንን ወለደ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos