ዕብራውያን 12:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን እንከተለው፤ እርሱ ነውርን ንቆ፥ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፣ የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእምነታችንንም ራስና ፍጽምና የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፥ ውርደቱንም ንቆ፥ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምንሮጠውም የእምነታችን መሥራችና ፈጻሚ የሆነውን ኢየሱስን በመመልከት ነው፤ እርሱ በፊቱ በተደቀነው ደስታ ምክንያት በመስቀል ላይ የመሞትን ውርደት ከምንም ሳይቈጥር የመስቀልን መከራና ሞት ታገሠ፤ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝም ተቀመጠ። |
ርዳታ ለመፈለግ ወደ ግብፅ ለሚወርዱ፥ በፈረሶችና በሰረገሎችም ለሚታመኑ ወዮላቸው! ፈረሰኞቹ ብዙዎች ናቸውና፤ በእስራኤልም ቅዱስ አልታመኑምና፤ እግዚአብሔርንም አልፈለጉምና።
መልኩም የተናቀ፥ ከሰውም ልጆች ሁሉ የተዋረደ፥ የተገረፈ ሰው፥ መከራንም የተቀበለ ነው፤ ፊቱንም መልሶአልና አቃለሉት፥ አላከበሩትምም።
በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።
ከዚያን ቀን ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ ዘንድ ከሽማግሎችና ከካህናት አለቆች ከጻፎችም ብዙ መከራ ይቀበልና ይገደል ዘንድ በሦስተኛውም ቀን ይነሣ ዘንድ እንዲገባው ለደቀ መዛሙርቱ ይገልጥላቸው ጀመር።
በማግሥቱም ዮሐንስ ወደ እርሱ ሲመጣ ጌታችን ኢየሱስን አይቶ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ የዓለሙን ኀጢኣት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።
እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ የስንዴ ቅንጣት በምድር ላይ ካልወደቀችና ካልሞተች ብቻዋን ትኖራለች፤ ከሞተች ግን ብዙ ፍሬን ታፈራለች።
ጌታችን ኢየሱስም፥ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው፥ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣ፥ ወደ እግዚአብሔርም እንደሚሄድ ባወቀ ጊዜ፥
የአባቴ ፈቃዱ ይህ ነው፤ ወልድን አይቶ የሚያምንበት ሁሉ የዘለዓለም ሕይወትን እንዲያገኝ ነው፤ እኔም በመጨረሻዪቱ ቀን አስነሣዋለሁ።”
እንግዲህ የእስራኤል ወገኖች ሁሉ እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታም መሢሕም እንዳደረገው በርግጥ ይወቁ።”
እግዚአብሔር እርሱን ለእስራኤል ንስሓን፥ የኀጢአትንም ስርየት ይሰጥ ዘንድ ራስም አዳኝም አደረገው፤ በቀኙም አስቀመጠው።
ክርስቶስ እንደ ወደዳችሁ፥ ራሱንም ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ የሚሆን መሥዋዕትና ቍርባን አድርጎ እንደ ሰጠላችሁ በፍቅር ተመላለሱ።
እርሱ የጀመረላችሁን በጎውን ሥራ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመጣበት ቀን ድረስ እርሱ እንደሚፈጽምላችሁ አምናለሁ።
እኛስ ሀገራችን በሰማይ ያለችው ናት፤ ከዚያም እርሱን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን።
ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።
እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የመልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ ኀጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ።
እናንተ ተሰድባችሁ ነበር፤ መከራም አጽንተውባችሁ ነበር፤ ተዘባብተውባችሁም ነበር፤ በዚህም መንገድ እንዲህ ከሆኑት ጋር ተባብራችሁ ነበር።
ኦሪት ምንም ግዳጅ አልፈጸመችምና፤ ነገር ግን በእርስዋ ፋንታ ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት ከእርስዋ የሚሻል ተስፋ ገብቶአል።
እንዲሁ ክርስቶስም የብዙዎችን ኀጢአት ያስተሰርይ ዘንድ ራሱን አንድ ጊዜ ሠዋ፤ በኋላ ግን ያድናቸው ዘንድ ተስፋ ለሚያደርጉት ያለ ኀጢአት ይገለጥላቸዋል።
በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።
ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች አንድ ጊዜ በኀጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤
እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ፤” አለኝ።