Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕብራውያን 12:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የምንሮጠውም የእምነታችን መሥራችና ፈጻሚ የሆነውን ኢየሱስን በመመልከት ነው፤ እርሱ በፊቱ በተደቀነው ደስታ ምክንያት በመስቀል ላይ የመሞትን ውርደት ከምንም ሳይቈጥር የመስቀልን መከራና ሞት ታገሠ፤ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝም ተቀመጠ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፣ የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የእምነታችንንም ራስና ፍጽምና የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፥ ውርደቱንም ንቆ፥ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 12:2
78 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ለጌታዬ (ለመሲሑ) “ጠላቶችህን በእግርህ ማረፊያ ሥር እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው።


የገባኸውን ቃል ኪዳን ትፈጽምልኛለህ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ፍቅርህ ዘለዓለማዊ ነው፤ የእጅህን ሥራ ወደ ፍጻሜ ሳታደርስ አትተወው።


ብዙ ፈረሶች፥ ሠረገሎችና ወታደሮች ባሉት ብርቱ በሆነው በግብጽ ሠራዊት ተማምነው ርዳታ ለማግኘት ወደ ግብጽ ለሚወርዱ ወዮላቸው! ነገር ግን የእስራኤልን ቅዱስ ርዳታ አይለምኑም፤ መመሪያውንም አይቀበሉም።


“ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ ስለሌለ፥ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ያላችሁ ሁሉ ወደ እኔ ተመልሳችሁ ደኅንነትን አግኙ።


እርሱም በሌሎች የተናቀና የተጠላ ነበር፤ እርሱ የመከራና የሐዘን ሰው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እስኪያዞሩበት ድረስ እርሱ የተናቀ፥ እኛም ያላከበርነው ሰው ነበር።


ምንም እንኳ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን ላይ ፊቱን ቢመልስባቸውም እኔ በእርሱ ላይ እተማመናለሁ።


እኔ ግን እግዚአብሔርን ተስፋ አደርጋለሁ፤ የሚያድነኝን አምላክ እጠባበቃለሁ፤ እርሱም ይሰማኛል።


“በዚያን ጊዜ በዳዊት ዘሮችና በኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ላይ የርኅራኄና የጸሎት መንፈስ እሞላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው እነርሱ ለአንድያ ልጅና ለበኲር ልጅ እንደሚለቀስ ለወጉት ምርር ብለው እንዲያለቅሱለት ነው።


ሙሴም የነሐስ እባብ ሠርቶ በእንጨት ላይ ሰቀለው፤ በእባብ የተነከሰም ሁሉ ወደ ነሐሱ እባብ ቀና ብሎ ሲመለከት ዳነ።


ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ይላቸው ጀመር፦ “ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ አለብኝ፤ እዚያም ከሽማግሌዎች፥ ከካህናት አለቆችና ከሕግ መምህራን መከራ ይደርስብኛል፤ ይገድሉኛል፤ ግን በሦስተኛው ቀን እነሣለሁ።”


የሰው ልጅም ለማገልገልና ብዙዎችን ለማዳን ሕይወቱን አሳልፎ ለመስጠት መጣ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።”


እንዲህም አለ፤ “አባት ሆይ፥ ሁሉ ነገር ይቻልሃል፤ ይህን የመከራ ጽዋ ከእኔ አርቅልኝ፤ ነገር ግን እንደ አንተ ፈቃድ እንጂ እንደ እኔ ፈቃድ አይሁን።”


በዚህም ሁኔታ “ከዐመፀኞች ጋር ተቈጠረ፤” የሚለው የትንቢት ቃል ተፈጸመ።]


ጌታ ኢየሱስ ይህን ሁሉ ከነገራቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ። በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።


እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ “እርግጥ ነው፤ ኤልያስማ አስቀድሞ ይመጣል፤ ሁሉንም ያስተካክላል፤ ይሁን እንጂ፥ የሰው ልጅ ከባድ መከራ እንደሚቀበልና እንደሚናቅ የተጻፈው እንዴት ነው?


ወዲያውኑ የልጁ አባት፥ “ማመንስ አምናለሁ፤ ግን ማመን በሚያቅተኝ ነገር ሁሉ ደግሞ አንተ እርዳኝ!” ብሎ ጮኸ።


ሐዋርያቱም ጌታ ኢየሱስን “እባክህ እምነት ጨምርልን” አሉት።


ሄሮድስም ከጭፍሮቹ ጋር ሆኖ በንቀት አፌዘበት፤ ጌጠኛ ልብስ አልብሶም ወደ ጲላጦስ መልሶ ላከው።


መሲሕ ይህን ሁሉ መከራ መቀበልና ወደ ክብሩ መግባት ይገባው የለምን?”


በማግስቱ ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ “እነሆ፥ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ ይህ ነው!


እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ የስንዴ ቅንጣት በመሬት ወድቃ ካልሞተች፥ ብቻዋን ትቀራለች፤ ከሞተች ግን ብዙ ታፈራለች።


እኔም ከምድር ወደ ላይ ከፍ በተደረግሁ ጊዜ ሰውን ሁሉ ወደ እኔ አስባለሁ።”


አብ ሥልጣንን ሁሉ እንደ ሰጠውና ከእግዚአብሔር ወጥቶ እንደመጣ፥ ወደ እግዚአብሔርም እንደሚሄድ ኢየሱስ ያውቅ ነበር።


አዎ! የአባቴ ፈቃድ ወልድን የሚያይና በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲያገኝ ነው፤ እኔም በመጨረሻው ቀን ከሞት አስነሣዋለሁ።”


የአባታችሁ የአብርሃም ምኞት የእኔን ቀን አይቶ ለመደሰት ነበር፤ አይቶም ተደሰተ።”


“እንግዲህ ይህን እናንተ የሰቀላችሁትን ኢየሱስን እግዚአብሔር ጌታና መሲሕ እንዳደረገው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በእርግጥ ይወቅ!”


ሕይወት ሰጪ የሆነውንም ገደላችሁት፤ እግዚአብሔር ግን ከሞት አስነሣው፤ ስለዚህ ነገር እኛ ምስክሮች ነን።


እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ንስሓንና የኃጢአትን ይቅርታ እንዲሰጥ ኢየሱስን መሪና አዳኝ አድርጎ በቀኙ በክብር እንዲቀመጥ አድርጎታል፤


ሐዋርያት ግን ስለ ኢየሱስ ስም ውርደት ለመቀበል የተገቡ በመሆናቸው ደስ እያላቸው ከሸንጎው ወጥተው ሄዱ፤


የመስቀሉ ነገር ለሚጠፉት ሰዎች እንደ ሞኝነት ይቈጠራል፤ ለምንድን ለእኛ ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው።


እኛ ግን ክርስቶስ ስለ እኛ መሰቀሉን እናስተምራለን፤ ይህም ለአይሁድ መሰናከያ ነው፤ ለግሪክ ሰዎች ደግሞ ሞኝነት ነው።


በመስቀል ላይ በመሞትም ጠላትነትን አስወገደ፤ ሁለቱንም አንድ አካል አድርጎ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቃቸው።


ክርስቶስ እንደ ወደደንና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መልካም መዓዛ ያለው መባና መሥዋዕት አድርጎ ሕይወቱን ስለ እኛ አሳልፎ እንደ ሰጠ እናንተም በፍቅር ኑሩ።


ይህን መልካም ሥራ በእናንተ ሕይወት ውስጥ የጀመረ አምላክ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ለፍርድ በሚመለስበት ቀን ወደ ፍጻሜ እንደሚያደርሰው እርግጠኛ ነኝ።


እኛ ግን የሰማይ መንግሥት ዜጎች ነን፤ ከዚያም የሚመጣውን አዳኝ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን በናፍቆት እንጠባበቃለን።


ከእንግዲህ ወዲህ የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶ ይጠብቀኛል፤ ይህንንም አክሊል ያ ትክክለኛ ፍርድን ፈራጁ ጌታ በዚያን ቀን ይሰጠኛል፤ የሚሰጠውም ለእኔ ብቻ ሳይሆን የእርሱን መገለጥ ለሚወድዱ ሁሉ ነው።


እግዚአብሔር ከመላእክቱ መካከል፥ “ጠላቶችህን ከሥልጣንህ ሥር እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” ያለው ማንን ነው?


እርሱ የእግዚአብሔር ክብር ነጸብራቅ ነው፤ እርሱ በባሕርዩ ከእግዚአብሔር ጋር ፍጹም ትክክል ነው። በኀያል ቃሉ ዓለምን ሁሉ ደግፎ ይዞአል፤ ሰዎችንም ከኃጢአት ካነጻ በኋላ በሰማይ በኀያሉ እግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦአል።


ይህም የሆነው እነዚያን የተቀደሱትን በአንዱ መሥዋዕት አማካይነት ለዘለዓለም ፍጹሞች ስለ አደረጋቸው ነው።


አንዳንድ ጊዜ በሰው ፊት ተሰድባችኋል፤ ተንገላታችኋል፤ አንዳንድ ጊዜም ይህ ዐይነት ሥቃይ ከደረሰባቸው ሰዎች ጋር ጓደኞች በመሆናችሁ መከራ ተቀብላችኋል።


ሌሎች መዘባበቻ ሆነው ተገረፉ፤ ሌሎች በእግር ብረት ታስረው ወደ ወህኒ ቤት ተጣሉ፤


እንግዲህ ሳትሰለቹና ተስፋ ሳትቈርጡ ይህን ሁሉ የኃጢአተኞችን ተቃውሞ የታገሠውን ኢየሱስን ተመልከቱ።


እኛም ከሰፈር ወጥተን ወደ እርሱ እንሂድ፤ የውርደቱም ተካፋዮች እንሁን።


ፍጹም ሆኖ ከተገኘም በኋላ ለሚታዘዙት ሁሉ ለዘለዓለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።


በሙሴ ሕግ ምንም ነገር ፍጹም ሊሆን አልቻለም፤ አሁን ግን ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የተሻለ ተስፋ ተሰጥቶናል።


እንግዲህ ከምንነጋገርባቸው ነገሮች ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማይ በልዑል እግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ የካህናት አለቃ አለን፤


እንዲሁም ክርስቶስ የብዙዎችን ኃጢአት ለማስወገድ አንድ ጊዜ ተሠውቶአል፤ ደግሞም ኃጢአትን ለመሸከም ሳይሆን እርሱን የሚጠባበቁትን ለማዳን ሁለተኛ ጊዜ ይገለጣል።


ወንድሞቼ ሆይ! በክብር ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ የምታምኑ ከሆናችሁ አንዱ ከሌላው ይበልጣል በማለት በሰው መካከል አድልዎ አታድርጉ።


ከእነርሱ ውስጥ የነበረውም የክርስቶስ መንፈስ በመሲሑ ላይ ስለሚደርሰው መከራና ከመከራውም በኋላ ስለሚያገኘው ክብር አስቀድሞ አመልክቶ ነበር፤ እነርሱም ይህ ሁሉ በምን ጊዜና በእንዴት ያለ ሁኔታ እንደሚሆን መርምረው ነበር፤


ክርስቶስም ራሱ ወደ እግዚአብሔር ያቀርበን ዘንድ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ሳለ ጽድቅ ለሌለን ለእኛ በኃጢአታችን ምክንያት በማያዳግም ሁኔታ አንድ ጊዜ መከራን በመቀበል ሞቶአል፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።


እርሱ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ነው፤ መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ተገዝተውለታል።


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በምሕረቱ ወደ ዘለዓለም ሕይወት እንዲያደርሳችሁ በመጠባበቅ ራሳችሁን በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ጠብቁት።


“የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያን፥ ማለትም ወደ ኤፌሶን፥ ወደ ሰምርኔስ፥ ወደ ጴርጋሞን፥ ወደ ትያጥሮን፥ ወደ ሰርዴስ፥ ወደ ፊላደልፍያና ወደ ሎዶቅያ ላክ።”


ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ በእግሩ ሥር ወደቅኩ፤ እርሱ ግን ቀኝ እጁን በላዬ ጭኖ እንዲህ አለኝ፤ “አትፍራ፤ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እኔ ነኝ፤


ያለው፥ የነበረው፥ የሚመጣውም ሁሉን የሚችል ጌታ እግዚአብሔር “አልፋና ዖሜጋ፥ የመጀመሪያውና የመጨረሻው እኔ ነኝ!” ይላል።


“ለሰምርኔስ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ የመጀመሪያና የመጨረሻ ከሆነው፥ ሞቶ ከነበረውና ሕያው ከሆነው የተነገረ ነው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos