Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 110:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አቤቱ፥ በቅ​ኖች ሸንጎ በጉ​ባ​ኤም በፍ​ጹም ልቤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ጌታዬን፣ “ጠላቶችህን ለእግርህ መረገጫ፣ እስከማደርግልህ ድረስ፣ በቀኜ ተቀመጥ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የዳዊት መዝሙር። ጌታ ጌታዬን፦ “ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ለጌታዬ (ለመሲሑ) “ጠላቶችህን በእግርህ ማረፊያ ሥር እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 110:1
23 Referencias Cruzadas  

ጠላ​ቶቹ ሁሉ ከእ​ግሩ በታች እስ​ኪ​ወ​ድቁ ድረስ ይነ​ግሥ ዘንድ አለ​ውና።


ከሆነ ጀምሮ ከመ​ላ​እ​ክት፥ “ጠላ​ቶ​ች​ህን ከእ​ግ​ርህ ጫማ በታች እስከ አደ​ር​ግ​ልህ ድረስ በቀኜ ተቀ​መጥ” ማንን አለው?


እር​ሱም የክ​ብሩ መን​ጸ​ባ​ረ​ቅና የመ​ልኩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥ​ል​ጣኑ ቃል እየ​ደ​ገፈ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንን በራሱ ካነጻ በኋላ፥ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ቀኝ ተቀ​መጠ።


የእ​ም​ነ​ታ​ች​ን​ንም ራስና ፈጻ​ሚ​ውን ኢየ​ሱ​ስን እን​ከ​ተ​ለው፤ እርሱ ነው​ርን ንቆ፥ በፊ​ቱም ስላ​ለው ደስታ በመ​ስ​ቀል ታግሦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዙፋን ቀኝ ተቀ​ም​ጦ​አ​ልና።


ኢየሱስም “አንተ አልህ፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፥ ከእንግዲህ ወዲህ የሰው ልጅ በኀይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ፤” አለው።


እርሱም መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ከተገዙለት በኋላ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ።


በእ​ጆ​ች​ህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾም​ኸው፤ ሁሉን ከእ​ግ​ሮቹ በታች አስ​ገ​ዛ​ህ​ለት፥


ከተ​ና​ገ​ር​ነ​ውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰ​ማ​ያት በግ​ር​ማው ዙፋን ቀኝ የተ​ቀ​መጠ እን​ዲህ ያለ ሊቀ ካህ​ናት አለን።


ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋር ከተ​ነ​ሣ​ችሁ ክር​ስ​ቶስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ተቀ​ምጦ በአ​ለ​በት በላይ ያለ​ውን ሹ።


ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፤ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።


አቤቱ ጌታ​ችን፥ ስምህ በም​ድር ሁሉ እጅግ ተመ​ሰ​ገነ፥ ምስ​ጋ​ናህ በሰ​ማ​ዮች ላይ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና።


የድ​ን​ጋይ ውር​ወራ ያህ​ልም ከእ​ነ​ርሱ ፈቀቅ ብሎ እየ​ሰ​ገደ ጸለየ።


ንጉ​ሡም ዳዊት በጉ​ባ​ኤው መካ​ከል ቆሞ እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞቼና ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦ​ትና ለአ​ም​ላ​ካ​ችን እግር ማረ​ፊያ የዕ​ረ​ፍት ቤት ለመ​ሥ​ራት አሳብ በልቤ መጣ​ብኝ፤ ለዚ​ህም ሥራ የሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውን አዘ​ጋ​ጅ​ቻ​ለሁ፤


እርሱ የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራል፥ ክብርንም ይሸከማል፥ በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ ይነግሣል፣ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፥ የሰላምም ምክር በሁለቱ መካከል ይሆናል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios