የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ማስታወቂያዎች


ንዑስ ምድብ

63 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ሲኦል

እግዚአብሔር ፍቅር እንደሆነና ሁሉንም የሚያደርገው በፍቅር እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል (ኤርምያስ 31:3)። እግዚአብሔር የኃጢአተኛ ሞት እንደማይፈልግም ይነግረናል። ሕዝቅኤል 33:11 ላይ «ሕያው እኔ ነኝና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ የኃጢአተኛ ሞት ደስ አይለኝም፥ ነገር ግን ኃጢአተኛ ከመንገዱ ተመልሶ እንዲኖር ደስ ይለኛል። ተመለሱ፥ ተመለሱ፥ ከክፉ መንገዳችሁ፥ ስለምን ትሞታላችሁ? የእስራኤል ቤት ሆይ!» ይላል።

እኛም በመንፈስ ቅዱስ እንድንቀደስና ከገሃነም እሳት ከዘላለማዊ ሞት እንድንድን ሁልጊዜ መጠንቀቅ፣ መጸለይና መስገድ አለብን። ማቴዎስ 10:28 ላይ «ሥጋን የሚገድሉትን ነገር ግን ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚችለውን ይልቅ ፍሩ» ተብሎ ተጽፏልና።


ማቴዎስ 13:42

ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ወደ እቶን እሳት ይጥሏቸዋል።

ማቴዎስ 23:33

“እናንተ እባቦች፤ የእፉኝት ልጆች! ከገሃነም ፍርድ እንዴት ልታመልጡ ትችላላችሁ?

ማቴዎስ 5:29

ቀኝ ዐይንህ የኀጢአት ሰበብ ቢሆንብህ፣ አውጥተህ ወዲያ ጣለው፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል።

ማቴዎስ 10:28

ሥጋን መግደል እንጂ ነፍስን መግደል የማይችሉትን አትፍሩ፤ ይልቁንስ ነፍስንና ሥጋን በገሃነም ማጥፋት የሚቻለውን ፍሩ።

2 ጴጥሮስ 2:4

እግዚአብሔር ኀጢአት የሠሩትን መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ከጣላቸውና በጨለማ ጕድጓድ ለፍርድ ካስቀመጣቸው፣

ሉቃስ 9:25

ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጠፋ ወይም ቢያጐድል ጥቅሙ ምንድን ነው?

ያዕቆብ 3:6

ምላስም እንደ እሳት ናት፤ በሰውነት ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ የክፋት ዓለም ናት፤ ሰውነትን ሁሉ ታረክሳለች፤ ደግሞም የፍጥረትን ሩጫ ታቃጥላለች፤ ራሷም በገሃነም ትቃጠላለች።

ሐዋርያት ሥራ 2:27

ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፤ ቅዱስህም መበስበስን እንዲያይ አትፈቅድም።

ራእይ 20:15

ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘ ሁሉ ወደ እሳት ባሕር ተጣለ።

መዝሙር 9:17

ክፉዎች ተመልሰው ወደ ሲኦል ይወርዳሉ፤ እግዚአብሔርን የሚዘነጉ ሕዝቦችም ሁሉ እንደዚሁ።

ማቴዎስ 16:18

አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚህ ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም።

ራእይ 20:10

ያሳታቸው ዲያብሎስም፣ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፤ እነርሱም ቀንና ሌሊት ከዘላለም እስከ ዘላለም ይሠቃያሉ።

ማቴዎስ 25:41

“ከዚያም በግራው በኩል ላሉት ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው የዘላለም እሳት ከእኔ ተለይታችሁ ሂዱ፤

ራእይ 20:14

ከዚያም በኋላ ሞትና ሲኦል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ፤ የእሳቱ ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።

ዮሐንስ 15:6

በእኔ የማይኖር ተጥሎ እንደሚደርቅ ቅርንጫፍ ነው፤ እንዲህ ያሉት ቅርንጫፎች ተለቅመው ወደ እሳት ይጣላሉ፤ ይቃጠላሉም።

ማቴዎስ 13:50

ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ወደ እቶን እሳት ይጥሏቸዋል።”

ራእይ 19:20

ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከርሱም ጋራ በፊቱ ምልክቶችን ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ። በእነዚህ ምልክቶች የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትንና ለምስሉ የሰገዱትን አሳተ። ሁለቱም በሕይወት እንዳሉ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ተጣሉ።

ማቴዎስ 25:46

“እነዚህም ወደ ዘላለም ፍርድ፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።”

ኢሳይያስ 33:14

በጽዮን ያሉ ኀጢአተኞች ደነገጡ፤ አምላክ የሌላቸውም ፍርሀት ይዟቸው፣ “ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳት ጋራ ማን መኖር ይችላል፣ ከዘላለም እሳትስ ጋራ ማን መኖር ይችላል?” አሉ።

ማቴዎስ 25:41-42

“ከዚያም በግራው በኩል ላሉት ደግሞ እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ፤ ለዲያብሎስና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው የዘላለም እሳት ከእኔ ተለይታችሁ ሂዱ፤

ምክንያቱም ተርቤ አላበላችሁኝም፤ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝም፤

ዘዳግም 32:22

በቍጣዬ እሳት ተቀጣጥሏልና፤ እርሱ እስከ ሲኦል ዘልቆ ይነድዳል። ምድርን እስከ ሰብሏ ይበላል፤ የተራሮችንም መሠረት ያቀጣጥላል።

ማቴዎስ 13:41-42

የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፤ እነርሱም ለኀጢአት ምክንያት የሆኑትንና ክፉ የሚያደርጉትን ሁሉ ለቅመው ከመንግሥቱ ያወጣሉ።

ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ወደ እቶን እሳት ይጥሏቸዋል።

ሉቃስ 16:23

በሲኦልም እየተሠቃየ ሳለ ቀና ብሎ ከሩቅ አብርሃምን አየ፤ አልዓዛርንም በዕቅፉ ይዞት አየ።

ሉቃስ 16:23-24

በሲኦልም እየተሠቃየ ሳለ ቀና ብሎ ከሩቅ አብርሃምን አየ፤ አልዓዛርንም በዕቅፉ ይዞት አየ።

እርሱም፣ ‘አብርሃም አባት ሆይ፤ ራራልኝ፤ በዚህ ነበልባል እየተሠቃየሁ ስለ ሆነ፣ አልዓዛር የጣቱን ጫፍ ውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያቀዘቅዝልኝ እባክህ ላክልኝ’ እያለ ጮኸ።

ራእይ 21:8

ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”

ማርቆስ 9:43

ስለዚህ እጅህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እጅ ኖሮህ እሳቱ ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ከመሄድ፣ ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል፤ [

ማርቆስ 9:43-48

ስለዚህ እጅህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እጅ ኖሮህ እሳቱ ወደማይጠፋበት ወደ ገሃነም ከመሄድ፣ ጕንድሽ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል፤ [

በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና።]

እግርህ ብታሰናክልህ ቍረጣት፤ ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ ዐንካሳ ሆነህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል፤ [

በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና።]

ዐይንህ ብታሰናክልህ ጐልጕለህ አውጣት፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም ከመጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት ይሻልሃል፤

“ ‘በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና።’

2 ተሰሎንቄ 1:9

እነርሱም ከጌታ ፊትና ከኀይሉ ክብር ተወግደው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ፤

ራእይ 14:11

የሥቃያቸውም ጢስ ከዘላለም እስከ ዘላለም ወደ ላይ ይወጣል። ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ ወይም የስሙንም ምልክት የሚቀበሉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”

ሉቃስ 16:24

እርሱም፣ ‘አብርሃም አባት ሆይ፤ ራራልኝ፤ በዚህ ነበልባል እየተሠቃየሁ ስለ ሆነ፣ አልዓዛር የጣቱን ጫፍ ውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያቀዘቅዝልኝ እባክህ ላክልኝ’ እያለ ጮኸ።

ይሁዳ 1:7

እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ፣ በዙሪያቸውም ያሉ ከተሞች ለሴሰኛነትና ከተፈጥሮ ሥርዐት ውጭ ለሆነ ሩካቤ ሥጋ ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ፤ እነርሱም በዘላለም እሳት በመቀጣት ለሚሠቃዩት ምሳሌ ሆነዋል።

ሮሜ 2:6-8

እግዚአብሔር “ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይሰጠዋል”።

በጎ የሆነውን ጸንቶ በማድረግ ክብርን፣ ሞገስንና ዘላለማዊነትን ለሚሹ የዘላለም ሕይወት ይሰጣቸዋል።

ነገር ግን በራስ ወዳዶች፣ እውነትን ትተው ክፋትን በሚከተሉ ፍርድና ቍጣ ይደርስባቸዋል።

ማቴዎስ 5:29-30

ቀኝ ዐይንህ የኀጢአት ሰበብ ቢሆንብህ፣ አውጥተህ ወዲያ ጣለው፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል።

“በመንፈስ ድኾች የሆኑ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።

ቀኝ እጅህ ቢያሰናክልህ ቈርጠህ ወዲያ ጣለው፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ከሰውነትህ አንዱን ክፍል ብታጣ ይሻልሃል።

ማቴዎስ 5:22

እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወንድሙን ያለ አግባብ የሚቈጣ ይፈረድበታል፤ ማንም ወንድሙን ‘ጅል’ የሚል በሸንጎ ፊት ይጠየቅበታል፤ ‘ደደብ’ የሚለው ደግሞ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይጠብቀዋል።

ዕብራውያን 10:27

የሚቀረው ግን የሚያስፈራ ፍርድና የእግዚአብሔርን ጠላቶች የሚበላ ብርቱ እሳት መጠበቅ ብቻ ነው።

ሉቃስ 12:5

ነገር ግን መፍራት የሚገባችሁን አሳያችኋለሁ፤ ከገደለ በኋላ ወደ ገሃነም ለመጣል ሥልጣን ያለውን እርሱን ፍሩት፤ አዎን፣ እርሱን ፍሩት እላችኋለሁ።

ማቴዎስ 7:13-14

“በጠባቡ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ትልቅ፣ በሩም ሰፊ ነውና፤ ብዙዎችም በዚያ ይገባሉ።

ወደ ሕይወት የሚያደርሰው ግን መንገዱ ቀጭን፣ በሩም ጠባብ ነው፤ የሚገቡበትም ጥቂቶች ብቻ ናቸው።

ሮሜ 2:8-9

ነገር ግን በራስ ወዳዶች፣ እውነትን ትተው ክፋትን በሚከተሉ ፍርድና ቍጣ ይደርስባቸዋል።

ክፉ በሚያደርግ በማንኛውም ሰው፣ አስቀድሞ በአይሁድ ከዚያም በአሕዛብ ላይ መከራና ጭንቀት ይሆናል፤

ማቴዎስ 18:9

እንዲሁም ዐይንህ ለመሰናክል ምክንያት ቢሆንብህ፣ አውጥተህ ጣለው፤ ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትጣል፣ አንድ ዐይን ኖሮህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል።

ማቴዎስ 8:12

መንግሥተ ሰማይ ተዘጋጅቶላቸው የነበሩት ግን ወደ ውጭ ወደ ጨለማው ይጣላሉ። በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”

ሮሜ 6:23

የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው።

ማቴዎስ 22:13

“ንጉሡም አገልጋዮቹን፣ ‘እጅና እግሩን አስራችሁ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጥታችሁ ጣሉት፤ በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል’ አላቸው፤

ራእይ 14:10-11

እርሱ ደግሞ ምንም ነገር ሳይቀላቀልበት በቍጣው ጽዋ ውስጥ የተሞላውን የእግዚአብሔርን ቍጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል። በቅዱሳን መላእክትና በበጉ ፊትም በእሳትና በዲን ይሠቃያል።

የሥቃያቸውም ጢስ ከዘላለም እስከ ዘላለም ወደ ላይ ይወጣል። ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግዱ ወይም የስሙንም ምልክት የሚቀበሉ ሁሉ ቀንና ሌሊት ዕረፍት የላቸውም።”

ማቴዎስ 24:51

ይቈራርጠዋል፤ ዕድል ፈንታውንም ከግብዞች ጋራ ያደርግበታል፤ በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።

ኢሳይያስ 66:24

“ወጥተውም በእኔ ላይ ያመፁትን ሰዎች ሬሳ ያያሉ፤ የሚበሏቸው ትሎች አይሞቱም፤ የሚያቃጥላቸው እሳታቸው አይጠፋም፤ ለሰውም ዘር ሁሉ አስጸያፊ ይሆናሉ።”

ምሳሌ 15:24

ወደ ሲኦል ከመውረድ እንዲድን፣ የሕይወት መንገድ ጠቢቡን ሰው ወደ ላይ ትመራዋለች።

1 ጴጥሮስ 3:19-20

በመንፈስም ሄዶ በወህኒ ቤት ለነበሩ ነፍሳት ሰበከላቸው።

ይህም የሚሆነው ንጹሕና ፍጹም አክብሮት የተሞላውን ኑሯችሁን ሲመለከቱ ነው።

እነዚህ በወህኒ የነበሩት ነፍሳት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲሠራ እግዚአብሔር በትዕግሥት ይጠብቃቸው የነበሩ እንቢተኞች ናቸው፤ በውሃ የዳኑት ጥቂት፣ ይኸውም ስምንት ሰዎች ብቻ ነበሩ።

ሉቃስ 16:26

ከሁሉም በላይ ከዚህ ወደ እናንተ ለማለፍ የሚፈልጉ እንደማይችሉ፣ እዚያ ያሉትም ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ፣ በእኛና በእናንተ መካከል ትልቅ ገደል ተደርጓል።’

ራእይ 20:14-15

ከዚያም በኋላ ሞትና ሲኦል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ፤ የእሳቱ ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።

ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘ ሁሉ ወደ እሳት ባሕር ተጣለ።

ገላትያ 5:21

ምቀኛነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

መዝሙር 49:14

እንደ በጎች ለሲኦል የተዳረጉ ናቸው፤ ሞትም እረኛቸው ይሆናል፤ ቅኖች በማለዳ ይገዟቸዋል፤ አካላቸው ከክብር ቤታቸው ርቆ፣ በሲኦል ይፈራርሳል።

ሕዝቅኤል 18:30

“የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለዚህ እንደየሥራችሁ በእያንዳንዳችሁ ላይ እፈርዳለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። እንግዲህ ንስሓ ግቡ፤ በኀጢአት እንዳትጠፉ፣ ከኀጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።

ምሳሌ 23:14

በአርጩሜ ቅጣው፤ ነፍሱንም ከሞት አድናት።

መዝሙር 139:8

ወደ ሰማይ ብወጣ፣ አንተ በዚያ አለህ፤ መኝታዬንም በሲኦል ባደርግ በዚያ ትገኛለህ።

ሉቃስ 3:17

ዐውድማውን ፈጽሞ ለማጥራትና ስንዴውንም ወደ ጐተራው ለመክተት መንሹ በእጁ ነው፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”

ራእይ 14:10

እርሱ ደግሞ ምንም ነገር ሳይቀላቀልበት በቍጣው ጽዋ ውስጥ የተሞላውን የእግዚአብሔርን ቍጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል። በቅዱሳን መላእክትና በበጉ ፊትም በእሳትና በዲን ይሠቃያል።

ማቴዎስ 7:13

“በጠባቡ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ትልቅ፣ በሩም ሰፊ ነውና፤ ብዙዎችም በዚያ ይገባሉ።

መዝሙር 55:15

ሞት ሳይታሰብ ድንገት ይምጣባቸው፤ በሕይወት ሳሉ ወደ ሲኦል ይውረዱ፤ ክፋት በመካከላቸው ዐድራለችና።

መክብብ 12:14

መልካምም ይሁን ክፉ፣ ስውር የሆነውን ነገር ሁሉ አንድ ሳይቀር፣ ማንኛውንም ሥራ አምላክ ወደ ፍርድ ያመጣዋልና።

ማቴዎስ 13:41

የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል፤ እነርሱም ለኀጢአት ምክንያት የሆኑትንና ክፉ የሚያደርጉትን ሁሉ ለቅመው ከመንግሥቱ ያወጣሉ።

ማርቆስ 9:48

“ ‘በገሃነም ትሉ አይሞትም፤ እሳቱ አይጠፋምና።’

ገላትያ 6:8

ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።

ራእይ 21:27

በበጉ የሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፣ ርኩሰትን የሚያደርግና ውሸትን የሚናገር ሁሉ አይገባባትም።

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር አባቴ ሆይ፤ ታማኝና ቸሮታ ያለህ አምላክ፤ ክብርና ምስጋና ለአንተ ይሁን! በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አማካኝነት ወደ አንተ እቀርባለሁ። እስከ ዛሬ ከአንተ ተርቀው የኖሩትን፣ በሞት አፋፍ ላይ እያሉ እንዲፈልጉህ፣ ነፍሳቸውም ከዘላማዊ ሥቃይ እንድትድን እለምንሃለሁ። እግዚአብሔር ሆይ፤ በእነዚህ ሰዎች ላይ ምህረትህን አውርድ፤ በዚህች ምድር ላይ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በልባቸው ንስሐ ገብተው የነፍሳቸውን መዳረሻ ወደ ሰማያዊ መንግሥትህ እንድትለውጥላቸው አደራ እላለሁ። ሲኦልን የፈጠርከው ለሰው ልጅ ሳይሆን ለዲያብሎስና ለአጋንንቱ እንዲሁም ለሲኦል እንደሆነ ቃልህ ይናገራል፤ “ሞትና ሲኦልም ወደ እሳት ባህር ተጣሉ። ይህ የእሳት ባህር ሁለተኛው ሞት ነው።” በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፤ አሜን።