Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


68 የንስሐ ጥቅሶች፥ ከመጽሐፍ ቅዱስ

68 የንስሐ ጥቅሶች፥ ከመጽሐፍ ቅዱስ

እግዚአብሔርን መውደድና ትእዛዛቱን ከልብ ለመፈጸም መጓጓት ወደ ንስሐ ይመራል። ሐዋርያት ሥራ 3:19 «እንግዲህ ንስሐ ግቡ፥ ተመለሱም፥ ኃጢአታችሁ ይደመሰስ ዘንድ፥ ከጌታ ፊትም የመጽናናት ዘመናት ይመጡ ዘንድ» ይላል። የወንጌል ዋና መሠረት ከሆኑት አንዱ ሲሆን ለዚህ ሕይወትና ለዘላለም ደስታችን ወሳኝ ነው።

ንስሐ ስለ እግዚአብሔር፣ ስለራስህና ስለ ዓለም አዲስ አመለካከት የሚሰጥ የአስተሳሰብና የልብ ለውጥ ነው። ከርኩሰት ሕይወት እየራቀህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ቅድስና እንድትኖር የሚያደርግህ ነው።

ንስሐ ከውስጥህ ስለሚፈልቀው እንባ ብዛት አይደለም፤ ከሥጋ ሥራ ለመራቅና በፍጹም ልብህ፣ በፍጹም አሳብህና በፍጹም ኃይልህ እግዚአብሔርን ለማስደሰት መጣር ነው።

ሙሉ በሙሉ ንስሐ የገባ ልብ ብቻ ነው ድነትን የሚያገኘው፣ ኃጢአቱ የሚሰረይለትና በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወትን የሚወርሰው። ስለዚህ ከሁሉም በፊት መንፈስ ቅዱስ እንዲመረምርህና ከክፉ መንገድህ እንዲመልስህ ለምን፤ ከጨለማ ተለይተህ የብርሃን ልጅ እንድትሆን።


ማቴዎስ 4:17

ከዚያ ጊዜ አንሥቶ ኢየሱስ፣ “ንስሓ ግቡ፤ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና” እያለ መስበክ ጀመረ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 3:3

እንግዲህ የተቀበልኸውንና የሰማኸውን አስታውስ፤ ታዘዘውም፤ ንስሓም ግባ። ባትነቃ ግን እንደ ሌባ እመጣብሃለሁ፤ በየትኛው ሰዓት እንደምመጣብህም አታውቅም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 17:30

ቀደም ሲል እግዚአብሔር እንዲህ ያለውን አለማወቅ በትዕግሥት ዐልፏል፤ አሁን ግን በየቦታው ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሓ እንዲገቡ ያዝዛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 3:9

አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ማንም እንዳይጠፋ ፈልጎ፣ ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ ስለ እናንተ ይታገሣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 5:32

እኔም ኀጢአተኞችን ወደ ንስሓ ልመልስ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 8:22

አሁንም ስለዚህ ክፋትህ ንስሓ ግባ፤ ወደ ጌታም ጸልይ፤ ምናልባት ይህን የልብህን ሐሳብ ይቅር ይልህ ይሆናል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 3:19

እኔ የምወድዳቸውን እገሥጻለሁ፤ እቀጣለሁም። ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 3:2

ስብከቱም፣ “ንስሓ ግቡ፤ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና” የሚል ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 2:38

ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ ኀጢአታችሁም እንዲሰረይላችሁ፣ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 3:8

እንግዲህ ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አፍሩ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 11:18

ይህን በሰሙ ጊዜም የሚሉትን አጥተው እንዲህ እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ “ይህማ ከሆነ አሕዛብም ወደ ሕይወት ይመጡ ዘንድ፣ እግዚአብሔር ንስሓን ሰጥቷቸዋል ማለት ነዋ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 5:31-32

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም፤ እኔም ኀጢአተኞችን ወደ ንስሓ ልመልስ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 3:19

እንግዲህ ኀጢአታችሁ እንዲደመሰስ ንስሓ ግቡ፤ ከመንገዳችሁም ተመለሱ፤ ከጌታም ዘንድ የመታደስ ዘመን ይመጣላችኋል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 13:3

አይደለም፣ እላችኋለሁ፤ ንስሓ ካልገባችሁ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዩኤል 2:13

ልባችሁን እንጂ፣ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ እርሱ መሓሪና ርኅሩኅ፣ ቍጣው የዘገየና ፍቅሩ የበዛ፣ ክፉ ነገር ከማምጣትም የሚታገሥ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 4:8

ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች እጃችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 1:9

ኀጢአታችንን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን፣ ከዐመፃም ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 7:10

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ሐዘን ወደ ድነት ለሚያደርስ ንስሓ ያበቃል፤ ጸጸትም የለበትም። ዓለማዊ ሐዘን ግን ለሞት ያበቃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 3:11

“እኔ ለንስሓ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን ጫማውን መሸከም ከማይገባኝ ከእኔ የሚበረታ፣ ከእኔ በኋላ ይመጣል፤ እርሱም በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:13

ኀጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝና የሚተወው ግን ምሕረትን ያገኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 15:7

እላችኋለሁ፤ እንደዚሁም ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ፣ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 1:15

“ጊዜው ደርሷል፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች፤ ንስሓ ግቡ፤ በወንጌልም እመኑ!” እያለ ይሰብክ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 51:17

እግዚአብሔር የሚቀበለው መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ አትንቅም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ዜና መዋዕል 7:14

በስሜ የተጠራው ሕዝቤ ራሱን አዋርዶ ቢጸልይ፣ ፊቴን ቢፈልግና ከክፉ መንገዱ ቢመለስ፣ ከሰማይ እሰማዋለሁ፤ ኀጢአቱን ይቅር እላለሁ፤ ምድሩንም እፈውሳለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 20:21

በንስሓ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በኢየሱስ እንዲያምኑ፣ ለአይሁድም ለግሪክ ሰዎችም አጥብቄ መስክሬላቸዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 5:21

እንደ ነጋም፣ በተነገራቸው መሠረት ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ ገብተው ሕዝቡን ማስተማር ጀመሩ። ሊቀ ካህናቱና ከርሱ ጋራ የነበሩት መጥተው የአይሁድን ሸንጎና የእስራኤልን ሽማግሌዎች ጉባኤ በሙሉ በአንድነት ሰበሰቡ፤ ሐዋርያትንም እንዲያመጡ ሰዎችን ወደ እስር ቤት ላኩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 2:4

ወይስ የእግዚአብሔር ቸርነት ወደ ንስሓ የሚመራህ መሆኑን ሳትገነዘብ፣ የቸርነቱን፣ የቻይነቱንና የትዕግሥቱን ባለጠግነት ትንቃለህ?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 11:20

ከዚያም ኢየሱስ ብዙውን ታምራት ያደረገባቸው ከተሞች ንስሓ ባለመግባታቸው እንዲህ ሲል ወቀሳቸው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 12:41

የነነዌ ሰዎች በፍርድ ዕለት ከዚህ ትውልድ ጋራ ተነሥተው ይፈርዱበታል፤ እነርሱ በዮናስ ስብከት ንስሓ ገብተዋልና። እነሆ፤ ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 51:10-12

አምላኬ ሆይ፤ ንጹሕ ልብ ፍጠርልኝ፤ ቀና የሆነውንም መንፈስ በውስጤ አድስ። ከፊትህ አትጣለኝ፤ ቅዱስ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድ። የማዳንህን ደስታ መልስልኝ፤ በእሽታ መንፈስም ደግፈህ ያዘኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 15:10

እላችኋለሁ፤ እንደዚሁም ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 18:30

“የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለዚህ እንደየሥራችሁ በእያንዳንዳችሁ ላይ እፈርዳለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። እንግዲህ ንስሓ ግቡ፤ በኀጢአት እንዳትጠፉ፣ ከኀጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 55:7

ክፉ ሰው መንገዱን፣ በደለኛም ሐሳቡን ይተው። ወደ እግዚአብሔር ይመለስ፤ እርሱም ምሕረት ያደርግለታል፤ ወደ አምላካችን ይመለስ፤ ይቅርታው ብዙ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 12:16-17

ለአንድ ጊዜ መብል ሲል ብኵርናውን እንደ ሸጠው እንደ ዔሳው፣ ማንም ሴሰኛ ወይም እግዚአብሔርን የማያከብር ሆኖ እንዳይገኝ ተጠንቀቁ። በኋላም ይህንኑ በረከት ሊወርስ በፈለገ ጊዜ እንደ ተከለከለ ታውቃላችሁ፤ በረከቱን በእንባ ተግቶ ቢፈልግም ለንስሓ ስፍራ ሊያገኝ አልቻለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 11:28-30

“እናንተ ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ። ቀንበሬን ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ በልቤ የዋህና ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ “ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው አንተ ነህ? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ሲል ጠየቀ። ቀንበሬ ልዝብ፣ ሸክሜም ቀላል ነውና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 38:18

በደሌን እናዘዛለሁ፤ ኀጢአቴም አውካኛለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:7-8

አትታለሉ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል። ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:1

ወንድሞች ሆይ፤ አንድ ሰው በኀጢአት ውስጥ ገብቶ ቢገኝ፣ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ በገርነት ልትመልሱት ይገባል። ነገር ግን አንተም እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 24:47

ከኢየሩሳሌም ጀምሮ ለሕዝቦች ሁሉ ንስሓና የኀጢአት ስርየት በስሙ ይሰበካል’

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 2:5

እንግዲህ ከየት እንደ ወደቅህ ዐስብ፤ ንስሓ ገብተህ ቀድሞ ታደርገው የነበረውን ነገር አድርግ፤ ንስሓ ካልገባህ፣ መጥቼ መቅረዝህን ከቦታው እወስድብሃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 6:23

የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:59

መንገዴን ቃኘሁ፤ አካሄዴንም ወደ ምስክርህ አቀናሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 9:13

ሄዳችሁ፣ ‘ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወድዳለሁ፤’ የሚለውን ቃል ትርጕም አጢኑ፤ ኀጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:6

ስለዚህ እርሱ በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:6-7

ስለዚህ እርሱ በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤ እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በርሱ ላይ ጣሉት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 12:17

በኋላም ይህንኑ በረከት ሊወርስ በፈለገ ጊዜ እንደ ተከለከለ ታውቃላችሁ፤ በረከቱን በእንባ ተግቶ ቢፈልግም ለንስሓ ስፍራ ሊያገኝ አልቻለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 25:5

እነርሱም እንዲህ አሉ፤ “እንግዲህ ሁላችሁ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፤ እግዚአብሔር ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣት ምድር ለዘላለም ትቀመጣላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 19:10

ምክንያቱም የሰው ልጅ የመጣው የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 2:4

እርሱ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነትን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ይፈልጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 102:13

ትነሣለህ፤ ጽዮንንም በርኅራኄ ዐይን ታያለህ፤ ለርሷ በጎነትህን የምታሳይበት ዘመን ነውና፤ የተወሰነውም ጊዜ ደርሷል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 15:34

ወደ ሰከነ ልቡናችሁ ተመለሱ፤ ኀጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና፤ ይህንም የምለው ላሳፍራችሁ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 130:3-4

እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀጢአትን ብትቈጣጠር፣ ጌታ ሆይ፤ ማን ሊቆም ይችላል? ነገር ግን በአንተ ዘንድ ይቅርታ አለ፤ ስለዚህም ልትፈራ ይገባሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 145:18

እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፣ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 21:28-31

ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ምን ይመስላችኋል? ሁለት ወንዶች ልጆች ያሉት አንድ ሰው ነበረ፤ ወደ መጀመሪያው ልጁ ሄዶ፣ ‘ልጄ ሆይ፤ ዛሬ ወደ ወይኑ ቦታ ሄደህ ሥራ’ አለው። “ልጁም፣ ‘አልሄድም’ አለው፤ ኋላ ግን ተጸጽቶ ሄደ። ማንም ሰው ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ቢላችሁ፣ ‘ለጌታ ያስፈልጋሉ፤ እርሱም ወዲያውኑ መልሶ ይልካቸዋል’ በሉት።” “ወደ ሁለተኛው ልጁ ሄዶ እንደዚያው አለው፤ ልጁም ‘ዕሺ ጌታዬ እሄዳለሁ’ አለው፤ ነገር ግን ሳይሄድ ቀረ። “ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ የፈጸመው የትኛው ነው?” እነርሱም፣ “የመጀመሪያው ልጅ” አሉት። ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፣ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና አመንዝራዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሟችኋል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 26:20

ነገር ግን በመጀመሪያ በደማስቆ ለሚኖሩ፣ ቀጥሎም በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላሉት ሁሉ፣ ከዚያም ለአሕዛብ፣ ንስሓ እንዲገቡና ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ፣ የንስሓም ፍሬ እንዲያሳዩ ገልጬ ተናገርሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 33:11

እንዲህ በላቸው፤ ‘በሕያውነቴ እምላለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ከመንገዳቸው ተመልሰው በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ በክፉዎች ሞት ደስ አልሰኝም። ተመለሱ! ከክፉ መንገዳችሁ ተመለሱ! የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ለምን ትሞታላችሁ?’

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:18

“ኑና እንዋቀሥ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ኀጢአታችሁ እንደ ዐለላ ቢቀላ፣ እንደ በረዶ ይነጣል፤ እንደ ደም ቢቀላም፣ እንደ ባዘቶ ነጭ ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 17:3-4

ስለዚህ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። “ወንድምህ ቢበድል ገሥጸው፤ ቢጸጸት ይቅር በለው። “የሰው ልጅ በሚገለጥበትም ቀን እንደዚሁ ይሆናል። በዚያ ቀን በቤቱ ጣራ ላይ ያለ፣ ማንም ሰው በቤቱ ውስጥ ያለውን ንብረት ለመውሰድ አይውረድ፤ እንዲሁም በዕርሻ ቦታ ያለ ሰው ወደ ኋላው አይመለስ። የሎጥን ሚስት አስታውሱ። ነፍሱን ለማሰንበት የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል፤ ነፍሱን የሚያጠፋት ግን ያቈያታል። እላችኋለሁ፤ በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ ዐልጋ ይተኛሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል። ሁለት ሴቶች ዐብረው ይፈጫሉ፤ አንዷ ትወሰዳለች፤ ሌላዋ ትቀራለች [ ሁለት ሰዎች በዕርሻ ቦታ ዐብረው ይሆናሉ፤ አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል።”] እነርሱም መልሰው፣ “ጌታ ሆይ፤ የሚወሰዱት ወዴት ነው?” አሉት። እርሱም፣ “በድን ባለበት አሞሮች ይሰበሰባሉ” አላቸው። በቀን ሰባት ጊዜ ቢበድልህና ሰባት ጊዜ፣ ‘ተጸጽቻለሁ’ እያለ ወደ አንተ ቢመለስ ይቅር በለው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:19-21

የሥጋ ሥራ ግልጽ ነው፦ ይኸውም ዝሙት፣ ርኩሰት፣ መዳራት፣ የምለውን አስተውሉ! ትገረዙ ዘንድ ብትፈልጉ፣ ክርስቶስ ፈጽሞ ለእናንተ እንደማይበጃችሁ እኔ ጳውሎስ እነግራችኋለሁ። ጣዖትን ማምለክ፣ ሟርት፣ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ ቍጣ፣ ራስ ወዳድነት፣ መለያየት፣ ዐድመኛነት፣ ምቀኛነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:5

ስለዚህ ምድራዊ ምኞቶቻችሁን ግደሉ፤ እነዚህም፦ ዝሙት፣ ርኩሰት፣ ፍትወት፣ ክፉ ምኞትና አምልኮተ ጣዖት የሆነው መጐምጀት ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:1

ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:176

እንደ ጠፋ በግ ተቅበዘበዝሁ፤ ትእዛዞችህን አልረሳሁምና፣ ባሪያህን ፈልገው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 3:13-14

ወንድሞች ሆይ፤ እኔ ገና እንደ ያዝሁት አድርጌ ራሴን አልቈጥርም፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ ከኋላዬ ያለውን እየረሳሁ ከፊቴ ወዳለው እዘረጋለሁ። እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ላይ ስለ ጠራኝ፣ ሽልማት ለመቀዳጀት ወደ ግቡ እፈጥናለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 5:16

ስለዚህ ኀጢአታችሁን እርስ በርሳችሁ ተናዘዙ፤ ትፈወሱም ዘንድ አንዱ ለሌላው ይጸልይ። የጻድቅ ሰው ጸሎት ኀይል አለው፤ ታላቅ ነገርም ያደርጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 6:1-2

እንግዲህ ምን እንላለን? ጸጋ እንዲበዛ ኀጢአት እየሠራን እንኑር? በሞተ ጊዜ፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለኀጢአት ሞቷል፤ ነገር ግን በሕይወት መኖርን ለእግዚአብሔር ይኖራል። እንደዚሁም ለኀጢአት እንደ ሞታችሁ፣ ነገር ግን በክርስቶስ ኢየሱስ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቍጠሩ። ስለዚህ ክፉ መሻቱን ትፈጽሙ ዘንድ በሟች ሥጋችሁ ላይ ኀጢአት እንዲነግሥበት አታድርጉ። ብልቶቻችሁን የክፋት መሣሪያ አድርጋችሁ ለኀጢአት አታቅርቡ፤ ይልቁንስ ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገሩ ሰዎች አድርጋችሁ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ። ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላልሆናችሁ፣ ኀጢአት አይገዛችሁምና። እንግዲህ ምን ይሁን? ከሕግ በታች ሳይሆን፣ ከጸጋ በታች በመሆናችን ኀጢአት እንሥራን? ከቶ አይሆንም! ራሳችሁን እንደ ባሪያ አድርጋችሁ ስታቀርቡ፣ ለምትታዘዙት ለርሱ፣ ይኸውም ወደ ሞት ለሚወስደው ለኀጢአት ወይም ወደ ጽድቅ ለሚያደርሰው ለመታዘዝ ባሮች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን? ነገር ግን የኀጢአት ባሮች የነበራችሁ ቢሆንም፣ ለተሰጣችሁለት ትምህርት በሙሉ ልብ የታዘዛችሁ በመሆናችሁ፣ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን፤ ከኀጢአት ነጻ ወጥታችሁ፣ የጽድቅ ባሪያዎች ሆናችኋል። በተፈጥሮ ደካሞች ስለ ሆናችሁ፣ በሰው ቋንቋ ይህን እላለሁ፤ ብልቶቻችሁን በባርነት ለርኩሰትና እየባሰ ለሚሄድ ክፋት ታቀርቡ እንደ ነበር፣ አሁን ደግሞ ወደ ቅድስና ለሚወስደው ጽድቅ ባሪያ አድርጋችሁ አቅርቡ። ከቶ አይሆንም፤ ለኀጢአት ሞተናል፤ ታዲያ እንዴት አድርገን ከእንግዲህ በርሱ እንኖራለን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቲቶ 2:11-12

ድነት የሚገኝበት የእግዚአብሔር ጸጋ ለሰዎች ሁሉ ተገልጧልና፤ ይህም ጸጋ በኀጢአት መኖርንና ዓለማዊ ምኞትን ክደን፣ በአሁኑ ዘመን ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ፣ በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወት እንድንኖር ያስተምረናል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር አባቴ ሆይ ስለ ፍቅርህ አመሰግንሃለሁ። ስለ ክፋቴና ስለ ኃጢአቴ አንድ ልጅህን ስለሰጠኸኝ አመሰግንሃለሁ። በኢየሱስ ክቡር ደም የአንተን ፊት ማየት እችላለሁ። ዛሬ ተጸጽቼ ይቅርታ እጠይቃለሁ። ከአንተ ርቄ እንደኖርኩና በዚህም ምክንያት ሌሎችን እንዳስከፋሁ አውቃለሁ። ከዛሬ ጀምሮ ግን ልለወጥና ያለፈውን ሰው ላለመሆን ወስኛለሁ። ጌታ ኢየሱስ ሆይ ዛሬ በፊትህ እሰግዳለሁ፤ ክፋቴንም አምኛለሁ። እባክህ አድሰኝ፤ ቀይረኝ፤ በጉዞዬ ውስጥ የተጎዳሁባቸውን ቦታዎች ፈውሰኝ። ሙሉ በሙሉ ነፃ ሆኜ እንድኖር አዕምሮዬን አድስ። በደምህ እጠብኝ እባክህ፤ ስሜንም በሕይወት መጽሐፍ ላይ ጻፍ። ከዛሬ ጀምሮ መንፈስ ቅዱስህ በልቤ ውስጥ ይኑር። ጌታዬ ሆይ አመሰግንሃለሁ፤ ክብርና ምስጋና ሁሉ ላንተ ይሁን። በኢየሱስ ስም፤ አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች