Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


72 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ኃጢአት

72 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች፡ ኃጢአት

ኃጢአት ማለት እግዚአብሔርን የሚቃወም አቋም ወደ ተግባር የሚተረጎም ነው። ከተራ ተግባር ይልቅ፣ ኃጢአት የፍጡር ለፈጣሪው እግዚአብሔር የእምቢተኝነትና የንቀት ባህሪ ነው። ይህ አቋም እይታችንን ስለሚጋርድ የእግዚአብሔርን ፈቃድ አስፈላጊነት ከማየት ይከለክለናል። እርሱ ከእኛ እጅግ የላቀ ጥበብ ያለው ስለሆነ ለእኛ የሚበጀውን በሚገባ ያውቃል።

በተቃራኒው ግን፣ ሰው የእግዚአብሔርን ሕግና ፍጹም ፈቃዱን ንቆ የራሱን አመለካከት ሲከተል፣ ይህ ለሰው ልጅ ከባድ መዘዝ ያስከትላል። ደስታን ማጣት፣ የጥፋተኝነት ስሜት፣ የስሜትና የአካል ህመም፣ የመንፈስ ቅዱስን ህልውና ማጥፋት እና ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት ማበላሸት ያስከትላል።

ከኃጢአት መዘዝ ነጻ የምንወጣበት ብቸኛው መንገድ በኢየሱስ ፊት ልባችንን ማዋረድ፣ ለሠራነው ክፋት ይቅርታ መጠየቅ እና ምህረቱን ማግኘት ነው።


ሮሜ 6:23

የኀጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር ስጦታ ግን በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 15:56

የሞት መንደፊያ ኀጢአት ነው፤ የኀጢአትም ኀይል ሕግ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 8:34

ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “እውነት እላችኋለሁ፤ ኀጢአት የሚያደርግ የኀጢአት ባሪያ ነው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:15

ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 5:12

ስለዚህ ኀጢአት በአንድ ሰው በኩል ወደ ዓለም እንደ ገባ ሁሉ፣ ሞትም በኀጢአት በኩል ገብቷል፤ በዚሁ መንገድ ሞት ወደ ሰዎች ሁሉ መጣ፤ ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 59:2

ነገር ግን በደላችሁ ከአምላካችሁ ለይቷችኋል፤ ኀጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል፤ በዚህም ምክንያት አይሰማም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 5:22

ክፉውን ሰው የገዛ መጥፎ ሥራው ያጠምደዋል፤ የኀጢአቱም ገመድ ጠፍሮ ይይዘዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሰቈቃወ 1:8

ኢየሩሳሌም ከባድ ኀጢአት ሠርታለች፤ ስለዚህም የረከሰች ሆናለች፤ ያከበሯት ሁሉ ናቋት፤ ዕራቍቷን ሆና አይተዋታልና፤ እርሷ ራሷ ታጕረመርማለች፤ ወደ ኋላዋም ዘወር ብላለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 13:6

ጽድቅ ቅን የሆነውን ሰው ትጠብቀዋለች፤ ክፋት ግን ኀጢአተኛውን ትጥለዋለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:8

ኀጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፤ ምክንያቱም ዲያብሎስ ከመጀመሪያ አንሥቶ ኀጢአትን የሚያደርግ ነው። የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ያፈርስ ዘንድ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 3:23

ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሏቸዋል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 2:4

እግዚአብሔር ኀጢአት የሠሩትን መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሃነም ከጣላቸውና በጨለማ ጕድጓድ ለፍርድ ካስቀመጣቸው፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 18:20

መሞት የሚገባት ኀጢአት የሠራችው ነፍስ ናት። ልጅ በአባቱ ኀጢአት አይቀጣም፤ አባትም በልጁ ኀጢአት አይቀጣም። ጻድቁ የጽድቁን ፍሬ ያገኛል፤ ኀጢአተኛውም የኀጢአቱን ዋጋ ይቀበላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:8

በሥጋ የሚመሩትም እግዚአብሔርን ማስደሰት አይችሉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 2:17

ነገር ግን መልካምና ክፉን ከሚያሳውቀው ዛፍ አትብላ፤ ምክንያቱም ከርሱ በበላህ ቀን በርግጥ ትሞታለህ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 6:16

ራሳችሁን እንደ ባሪያ አድርጋችሁ ስታቀርቡ፣ ለምትታዘዙት ለርሱ፣ ይኸውም ወደ ሞት ለሚወስደው ለኀጢአት ወይም ወደ ጽድቅ ለሚያደርሰው ለመታዘዝ ባሮች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 5:17

ዐመፅ ሁሉ ኀጢአት ነው፤ ለሞት የማያበቃም ኀጢአት አለ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 92:7

ክፉዎች እንደ ሣር ቢበቅሉ፣ ክፉ አድራጊዎች ቢለመልሙ፣ ለዘላለሙ ይጠፋሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 2:16

እግዚአብሔርን ከማያስከብር ከንቱ ልፍለፋ ራቅ፤ በዚህ ነገር የተጠመዱ ሰዎች ከእግዚአብሔር እየራቁ ይሄዳሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 7:14

ሕጉ መንፈሳዊ እንደ ሆነ እናውቃለን፤ እኔ ግን ለኀጢአት እንደ ባሪያ የተሸጥሁ ሥጋዊ ነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 4:7

መልካም ብታደርግ ተቀባይነትን አታገኝምን? መልካም ባታደርግ ግን፣ ኀጢአት በደጅህ እያደባች ናት፤ ልታሸንፍህ ትፈልጋለች፤ አንተ ግን ተቈጣጠራት።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 12:37

ምክንያቱም ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህ፤ ከቃልህም የተነሣ ይፈረድብሃልና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:8

ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 25:46

“እነዚህም ወደ ዘላለም ፍርድ፣ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:14-15

ነገር ግን እያንዳንዱ የሚፈተነው በራሱ ክፉ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ነው። ምኞትም ከፀነሰች በኋላ ኀጢአትን ትወልዳለች፤ ኀጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:50

ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ወደ እቶን እሳት ይጥሏቸዋል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 7:15

የማደርገውን አላውቅም፤ ለማድረግ የምፈልገውን አላደርግም፤ ነገር ግን የምጠላውን ያን አደርጋለሁና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 9:16

እግዚአብሔር በትክክለኛ ፍርዱ የታወቀ ነው፤ ክፉዎችም በእጃቸው ሥራ ተጠመዱ። ሒጋዮን ሴላ

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 29:6

ክፉ ሰው በራሱ ኀጢአት ይጠመዳል፤ ጻድቅ ግን ይዘምራል፤ ደስም ይለዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 20:15

ስሙ በሕይወት መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘ ሁሉ ወደ እሳት ባሕር ተጣለ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 10:13

በሰዎች ሁሉ ላይ ከደረሰው የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ስለዚህ ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አይተዋችሁም፤ ነገር ግን በምትፈተኑበት ጊዜ ፈተናውን መታገሥ እንድትችሉ፣ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 12:21

ጻድቃን ጕዳት አያገኛቸውም፤ ክፉዎች ግን በመከራ የተሞሉ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 53:6

እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ እያንዳንዳችንም በየመንገዳችን ነጐድን፤ እግዚአብሔርም፣ የሁላችንን በደል በርሱ ላይ ጫነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 22:15

ውሾች፣ አስማተኞች፣ ሴሰኞች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸትን የሚወድዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 51:5

ስወለድ ጀምሮ በደለኛ፣ ገና እናቴም ስትፀንሰኝ ኀጢአተኛ ነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:19-21

የሥጋ ሥራ ግልጽ ነው፦ ይኸውም ዝሙት፣ ርኩሰት፣ መዳራት፣ የምለውን አስተውሉ! ትገረዙ ዘንድ ብትፈልጉ፣ ክርስቶስ ፈጽሞ ለእናንተ እንደማይበጃችሁ እኔ ጳውሎስ እነግራችኋለሁ። ጣዖትን ማምለክ፣ ሟርት፣ ጥላቻ፣ ጠብ፣ ቅናት፣ ቍጣ፣ ራስ ወዳድነት፣ መለያየት፣ ዐድመኛነት፣ ምቀኛነት፣ ስካር፣ ዘፋኝነት፣ እንዲሁም እነዚህን የመሰለው ነው። አስቀድሜ እንዳልሁ፣ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ በእንዲህ ሁኔታ የሚኖሩ ሁሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:26-27

የእውነትን ዕውቀት ከተቀበልን በኋላ ሆነ ብለን በኀጢአት ጸንተን ብንመላለስ፣ ከእንግዲህ ለኀጢአት የሚሆን ሌላ መሥዋዕት አይኖርም፤ የሚቀረው ግን የሚያስፈራ ፍርድና የእግዚአብሔርን ጠላቶች የሚበላ ብርቱ እሳት መጠበቅ ብቻ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 3:5

ስለዚህ ምድራዊ ምኞቶቻችሁን ግደሉ፤ እነዚህም፦ ዝሙት፣ ርኩሰት፣ ፍትወት፣ ክፉ ምኞትና አምልኮተ ጣዖት የሆነው መጐምጀት ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 2:1-3

እናንተም በበደላችሁና በኀጢአታችሁ ምክንያት ሙታን ነበራችሁ፤ ምክንያቱም፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ እንድንመላለስባቸው ያዘጋጀልንን መልካም የሆኑትን ሥራዎች እንድንሠራ በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርን የእግዚአብሔር እጅ ሥራዎች ነን። ስለዚህ እናንተ ቀድሞ በትውልድ አሕዛብ የሆናችሁ፣ በአካል ላይ በሰው እጅ ከተደረገው የተነሣ፣ ራሳቸውን “ተገርዘናል” በሚሉት፣ “ያልተገረዙ” የተባላችሁ ያን አስታውሱ፤ በዚያ ዘመን ከክርስቶስ ተለይታችሁ፣ ከእስራኤል ወገንነት ርቃችሁ፣ ለኪዳኑም ተስፋ ባዕዳን ሆናችሁ፣ በዓለም ላይ ያለ ተስፋና ያለ እግዚአብሔር እንደ ነበራችሁ አስታውሱ። አሁን ግን እናንተ ቀድሞ ርቃችሁ የነበራችሁ፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም አማካይነት ቀርባችኋል። ሁለቱን አንድ ያደረገ፣ የሚለያየውንም የጥል ግድግዳ ያፈረሰ ሰላማችን እርሱ ራሱ ነውና፤ ሕግንም፣ ከትእዛዞቹና ከሥርዐቱ ጋራ በሥጋው ሻረ። ዐላማውም ከሁለቱ አንድን አዲስ ሰው በራሱ ፈጥሮ ሰላምን ለማድረግ ነው። ጥልን በገደለበት በመስቀሉም ሁለቱን በዚህ በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋራ አስታረቀ። መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁት ለእናንተ፣ ቀርበው ለነበሩትም ለእነርሱ ሰላምን ሰበከ፤ ሁላችንም በርሱ አማካይነት በአንዱ መንፈስ ወደ አብ መቅረብ እንችላለንና። ከዚህ የተነሣ እናንተ ከቅዱሳን ጋራ የአንድ አገር ዜጋ፣ የእግዚአብሔርም ቤተ ሰብ አባል ናችሁ እንጂ፣ ከእንግዲህ ወዲህ መጻተኞችና እንግዶች አይደላችሁም። በዚህም፣ የዓለምን ክፉ መንገድ ተከትላችሁ፣ በአየር ላይ ላሉት መንፈሳውያን ኀይላት ገዥ ለሆነውና አሁንም ለእግዚአብሔር በማይታዘዙት ሰዎች ላይ ለሚሠራው መንፈስ እየታዘዛችሁ ትኖሩ ነበር። በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማእዘኑ ራስ ድንጋይም ክርስቶስ ኢየሱስ ራሱ ነው፤ በርሱ ሕንጻ ሁሉ አንድ ላይ ተገጣጥሞ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል። እናንተም ደግሞ እግዚአብሔር በመንፈሱ የሚኖርበት ማደሪያ ትሆኑ ዘንድ ዐብራችሁ እየተገነባችሁ ነው። እኛ ሁላችን በአንድ ወቅት የሥጋችንን ምኞት እያረካን፣ መንገዱንም እየተከተልን በመካከላቸው እንኖር ነበር፤ እንደ ሌሎቹም የቍጣ ልጆች ነበርን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 2:24

ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በዕንጨት መስቀል ላይ ተሸከመ፤ በርሱ ቍስል እናንተ ተፈውሳችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 32:5

ኀጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፤ በደሌንም አልሸሸግሁም፤ ደግሞም “መተላለፌን ለእግዚአብሔር እናዘዛለሁ” አልሁ፤ አንተም የኀጢአቴን በደል፣ ይቅር አልህ። ሴላ

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:28

እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ሴትን በምኞት ዐይን የተመለከተ ሁሉ በልቡ ከርሷ ጋራ አመንዝሯል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 7:20

ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግና ፈጽሞ ኀጢአት የማይሠራ ጻድቅ ሰው በምድር ላይ የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 2:1-2

ልጆቼ ሆይ፤ ይህን የምጽፍላችሁ ኀጢአት እንዳትሠሩ ነው፤ ነገር ግን ማንም ኀጢአት ቢሠራ፣ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን፤ እርሱም ጻድቁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ወንድሙን የሚወድድ በብርሃን ይኖራል፤ በርሱም ዘንድ የመሰናከያ ምክንያት የለውም። ነገር ግን ወንድሙን የሚጠላ በጨለማ ውስጥ ነው፤ በጨለማ ይመላለሳል፤ ጨለማው ስላሳወረውም የት እንደሚሄድ አያውቅም። ልጆች ሆይ፤ ኀጢአታችሁ ስለ ስሙ ተሰርዮላችኋልና፣ እጽፍላችኋለሁ። አባቶች ሆይ፤ ከመጀመሪያ ያለውን እርሱን ዐውቃችሁታልና፣ እጽፍላችኋለሁ። ጐበዛዝት ሆይ፤ ክፉውን አሸንፋችኋልና፣ እጽፍላችኋለሁ። ልጆች ሆይ፤ አብን ዐውቃችሁታልና፣ እጽፍላችኋለሁ። አባቶች ሆይ፤ ከመጀመሪያ ያለውን እርሱን ዐውቃችሁታልና፣ እጽፍላችኋለሁ። ጐበዛዝት ሆይ፤ ብርቱዎች ስለ ሆናችሁ፣ የእግዚአብሔር ቃል በእናንተ ስለሚኖር፣ ክፉውንም ስላሸነፋችሁ፣ እጽፍላችኋለሁ። ዓለምን ወይም በዓለም ያለውን ማንኛውንም ነገር አትውደዱ፤ ማንም ዓለምን ቢወድድ የአብ ፍቅር በርሱ ዘንድ የለም፤ ምክንያቱም በዓለም ያለው ሁሉ፦ የሥጋ ምኞት፣ የዐይን አምሮትና የኑሮ ትምክሕት ከዓለም እንጂ ከአብ የሚመጣ አይደለም። ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚፈጽም ግን ለዘላለም ይኖራል። ልጆች ሆይ፤ ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፤ እንደ ሰማችሁትም የክርስቶስ ተቃዋሚ ይመጣል፤ አሁን እንኳ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች መጥተዋል፤ የመጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ የምናውቀውም በዚህ ነው። ከእኛ መካከል ወጡ፤ ይሁን እንጂ ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገን ቢሆኑማ ኖሮ ከእኛ ጋራ ጸንተው በኖሩ ነበር። ነገር ግን ሁሉም ከእኛ ወገን እንዳልነበሩ ይታወቅ ዘንድ ከእኛ ተለዩ። እርሱም የኀጢአታችን ማስተስረያ ነው፤ ይኸውም ለዓለም ሁሉ ኀጢአት እንጂ ለእኛ ብቻ አይደለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:13

ኀጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝና የሚተወው ግን ምሕረትን ያገኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 38:18

በደሌን እናዘዛለሁ፤ ኀጢአቴም አውካኛለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:7-8

አትታለሉ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል። ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 5:21

እኛ በርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 12:1

እንግዲህ እነዚህን የመሳሰሉ ብዙ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፣ ሸክም የሚሆንብንን ሁሉ፣ በቀላሉም ተብትቦ የሚይዘንን ኀጢአት አስወግደን በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 106:6

እኛም እንደ አባቶቻችን ኀጢአት ሠራን፤ በደልን፤ ክፉም አደረግን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 14:34

ጽድቅ ሕዝብን ከፍ ከፍ ታደርጋለች፤ ኀጢአት ግን ለየትኛውም ሕዝብ ውርደት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:1

ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 18:30

“የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለዚህ እንደየሥራችሁ በእያንዳንዳችሁ ላይ እፈርዳለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። እንግዲህ ንስሓ ግቡ፤ በኀጢአት እንዳትጠፉ፣ ከኀጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:12

እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፣ በደላችንን ይቅር በለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 15:10

እላችኋለሁ፤ እንደዚሁም ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:18

በክፋታቸው እውነትን ዐፍነው በሚይዙ፣ በዐመፃቸውና በክፋታቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:11

አንተን እንዳልበድል፣ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 18:15

“ወንድምህ ቢበድልህ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻ ሆናችሁ ጥፋቱን ንገረው። ቢሰማህ፣ ወንድምህን እንደ ገና የራስህ ታደርገዋለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቲቶ 3:5

ስላደረግነው የጽድቅ ሥራ ሳይሆን፣ ከምሕረቱ የተነሣ አዳነን። ያዳነንም ዳግም ልደት በሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታደስ ነው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጴጥሮስ 3:9

አንዳንድ ሰዎች የዘገየ እንደሚመስላቸው ጌታ የተስፋ ቃሉን ለመፈጸም አይዘገይም፤ ነገር ግን ማንም እንዳይጠፋ ፈልጎ፣ ሁሉ ለንስሓ እንዲበቃ ስለ እናንተ ይታገሣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 4:17

እንግዲህ መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ እንዳለበት እያወቀ የማያደርግ ሰው ኀጢአት ያደርጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 6:4-6

አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን፣ ሰማያዊውን ስጦታ የቀመሱትን፣ ከመንፈስ ቅዱስ ተካፋዮች የሆኑትን፣ መልካሙን የእግዚአብሔር ቃልና የሚመጣውን ዓለም ኀይል የቀመሱትን፣ በኋላ ግን የካዱትን እንደ ገና ወደ ንስሓ መመለስ አይቻልም፤ ምክንያቱም እነርሱ ለገዛ ጥፋታቸው የእግዚአብሔርን ልጅ እንደ ገና ይሰቅሉታል፤ ያዋርዱታልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 66:18

ኀጢአትን በልቤ አስተናግጄ ቢሆን ኖሮ፣ ጌታ ባልሰማኝ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 4:30

ለቤዛ ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔር መንፈስ አታሳዝኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:1-2

እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው። እርስ በርሳችሁ በወንድማማች መዋደድ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፤ አንዱ ሌላውን ከራሱ በማስበለጥ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ። ጌታን ለማገልገል በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ እንጂ ከዚህ ትጋት ወደ ኋላ አትበሉ። በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ። ችግረኛ ለሆኑ ቅዱሳን ካላችሁ አካፍሉ፤ እንግዶችን ተቀበሉ። የሚያሳድዷችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያዝኑም ጋራ ዕዘኑ። እርስ በርሳችሁ በአንድ ሐሳብ በመስማማት ኑሩ። ዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ካሉ ጋራ ዐብራችሁ ለመሆን ፍቀዱ እንጂ አትኵራሩ፤ በራሳችሁም አትመኩ። ለማንም ክፉን በክፉ አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ትጉ። ቢቻላችሁስ በበኩላችሁ ከሰው ሁሉ ጋራ በሰላም ኑሩ። ወዳጆቼ ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ቍጣ ፈንታ ስጡ እንጂ አትበቀሉ፤ ጌታ “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” እንዳለ ተጽፏልና። መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 1:15

“ክርስቶስ ኢየሱስ ኀጢአተኞችን ለማዳን ወደ ዓለም መጣ” የሚለው ቃል እውነተኛና ሰው ሁሉ ሊቀበለው የሚገባ ነው፤ ከኀጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ቈላስይስ 2:13-14

እናንተም በበደላችሁና የሥጋችሁን ኀጢአታዊ ባሕርይ ባለመገረዝ ሙታን ነበራችሁ፣ እግዚአብሔር ግን ከክርስቶስ ጋራ ሕያዋን አደረጋችሁ፤ በደላችንንም ሁሉ ይቅር አለን፤ ሲቃወመንና ሲፃረረን የነበረውን የዕዳ ጽሕፈት ከነሕግጋቱ በመደምሰስ፣ በመስቀል ላይ ቸንክሮ ከመንገድ አስወገደው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 3:18-19

ምክንያቱም ከዚህ በፊት ደጋግሜ እንደ ነገርኋችሁ፣ አሁንም እንደ ገና፣ ያውም በእንባ እነግራችኋለሁ፤ ብዙዎች የክርስቶስ መስቀል ጠላቶች ሆነው ይመላለሳሉ። መጨረሻቸው ጥፋት ነው፤ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፤ ክብራቸው በነውራቸው ነው፤ ሐሳባቸው በምድራዊ ነገር ላይ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:1-2

“እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ፤ ወይም ዓሣ ቢለምነው እባብ የሚሰጥ ይኖራልን? እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ፣ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታን መስጠት ካወቃችሁበት፣ የሰማዩ አባታችሁ ታዲያ ለሚለምኑት መልካም ስጦታን እንዴት አብልጦ አይሰጥ? ሌሎች ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን እናንተም አድርጉላቸው፤ ኦሪትም፣ ነቢያትም በዚህ ይጠቃለላሉና። “በጠባቡ በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው መንገድ ትልቅ፣ በሩም ሰፊ ነውና፤ ብዙዎችም በዚያ ይገባሉ። ወደ ሕይወት የሚያደርሰው ግን መንገዱ ቀጭን፣ በሩም ጠባብ ነው፤ የሚገቡበትም ጥቂቶች ብቻ ናቸው። “በውስጣቸው ነጣቂ ተኵላዎች ሆነው ሳሉ የበግ ለምድ ለብሰው መካከላችሁ በመግባት ከሚያሸምቁ ሐሰተኛ ነቢያት ተጠንቀቁ። በፍሬአቸው ታውቋቸዋላችሁ፤ ከእሾኽ ቍጥቋጦ ወይን፣ ከኵርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁም ጥሩ ዛፍ ሁሉ ጥሩ ፍሬ፣ መጥፎ ዛፍ ግን መጥፎ ፍሬ ያፈራል። ጥሩ ዛፍ መጥፎ ፍሬ፣ መጥፎም ዛፍ ጥሩ ፍሬ ማፍራት አይችልም። ጥሩ ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል። በምትፈርዱበትም ፍርድ ይፈረድባችኋል፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 2:18

ያፈረስሁትን መልሼ የምገነባ ከሆነማ፣ ሕግ ተላላፊ መሆኔን አረጋግጣለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ሆይ፥ ዘላለማዊ አምላክ፥ ልዑል ጌታ፥ በኢየሱስ ስም ወደ አንተ እመጣለሁ። ከኃጢአት ባርነት እንድትፈታኝ እለምንሃለሁ፤ ምክንያቱም በሕይወቴ መዘዝና ጥፋትን አምጥቶብኛልና። ከአንተ ተለይቼ በዓመፀኝነት እንደኖርኩ አውቃለሁ። ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ከኃጢአት ባርነት ከሚያስረኝ ከሁሉ እንድላቀቅ እርዳኝ። ቃልህ «ሥጋን የሚዘራ ከሥጋ መበስበስን ያጭዳልና፤ መንፈስን የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለም ሕይወትን ያጭዳል» ይላል። ጌታ ሆይ፥ ከተስፋ መቁረጥ ጉድጓድና ከጭቃ ውስጥ አውጣኝ። በኢየሱስ ስም። አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች