Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


ለቅናሾች ጥቅሶች

ለቅናሾች ጥቅሶች

ልብህን ስማ፤ መስጠት እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘው ተግባር ነው። በምታቀርበው ጊዜ፣ ከሁሉ የተመረጠውን፣ ከልብ የመነጨውን አቅርብ። እግዚአብሔር ብዙ ሰጥቶናልና፣ የማንገባውን ያህል ባርኮናልና በደስታ እናድርገው። የተረፈንን ብቻ ብንሰጥ፣ ሕይወትም እንዲሁ ለእኛ የምትሰጠን የተረፈውን ብቻ እንደሆነ እናውቃለን።

ለራሳችን እንደምንሰጥ አድርገን እንስጥ፤ በግዴታ ወይም ተመልሶ እንዲሰጠን በማሰብ አይደለም። ሌላው እንዲያየን ወይም እንዲያመሰግነን ሳንፈልግ፣ በትህትና እንስጥ። ግራ እጃችን የቀኝ እጃችን የሰጠችውን እንኳን አታውቅ። ጌታችን በደስታ የሚሰጠውን ይወዳል፤ ልባችንን ያውቃልና።

እያንዳንዳችን በልቡ እንዳሰበው ይስጥ፤ በኀዘን ወይም በግዴታ አይደለም፤ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና። (2ኛ ቆሮንቶስ 9:7) መስጠት እግዚአብሔር ለእኛ ከሰጠን ውስጥ የምናቀርብለት የአምልኮ ምልክት ነው። እግዚአብሔር ሲሰጥ በልግስና እና ያለገደብ ነው። ስለዚህ ከልብ ስንሰጥ፣ እግዚአብሔር አብዝቶ እንዲባርከን በር እንከፍታለን። በሰጠህ መጠን ትቀበላለህ።


ዘፍጥረት 9:13-15

ቀስተ ደመናዬን በደመና ላይ አደርጋለሁ፤ ይህም በእኔና በምድር መካከል ለገባሁት ኪዳን ምልክት ይሆናል። ደመናን በምድር ላይ በጋረድሁና ቀስቴም በደመና ላይ በሚታይበት ጊዜ ሁሉ፣ ከእናንተና ከሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ጋራ የገባሁትን ኪዳን ዐስባለሁ፤ ሕይወት ያለውንም ሁሉ ያጠፋ ዘንድ፣ ከእንግዲህ የጥፋት ውሃ ከቶ አይመጣም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 15:18

በዚያ ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ሲል ኪዳን ገባለት፤ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ታላቁ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 17:7-8

በእኔና በአንተ፣ ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋራ ከትውልድ እስከ ትውልድ የዘላለም ኪዳኔን እመሠርታለሁ፤ በዚህም የአንተና ከአንተም በኋላ የዘርህ አምላክ እሆናለሁ። ይህችን አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን የከነዓንን ምድር በሙሉ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 19:5-6

አሁንም በፍጹም ብትታዘዙኝና ቃል ኪዳኔን ብትጠብቁ እነሆ ከአሕዛብ ሁሉ እናንተ የተወደደ ርስቴ ትሆናላችሁ፤ ምንም እንኳ ምድር ሁሉ የእኔ ብትሆንም፣ እናንተ ለእኔ የመንግሥት ካህናት የተቀደሰ ሕዝብ ትሆናላችሁ፤’ ለእስራኤላውያን የምትነግራቸው ቃሎች እነዚህ ናቸው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 24:7-8

ከዚያም የኪዳኑን መጽሐፍ ወስዶ ለሕዝቡ አነበበላቸው፤ እነርሱም፣ “እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን፤ እንታዘዛለን” አሉ። ከዚያም ሙሴ ደሙን ወሰደ፤ ሕዝቡም ላይ ረጭቶ፣ “ይህ እነዚህን ቃሎች በሰጠ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ የገባው የኪዳኑ ደም ይህ ነው” አላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 7:9

ስለዚህም አምላክህ እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቅ፤ እርሱ ለሚወድዱትና ትእዛዞቹን ለሚጠብቁት የፍቅሩን ኪዳን እስከ ሺሕ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ ታማኝ አምላክ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 9:5

ምድራቸውን ገብተህ የምትወርሳት ከጽድቅህ ወይም ከልብህ ቅንነት የተነሣ ሳይሆን፣ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ የማለላቸውን ቃል ለመፈጸም አምላክህ እግዚአብሔር እነዚህን አሕዛብ ከክፋታቸው የተነሣ ከፊትህ ስለሚያባርራቸው ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 29:9

እንግዲህ የምታደርጉት ሁሉ እንዲከናወንላችሁ፣ የዚህን ኪዳን ቃሎች በጥንቃቄ ተከተሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 30:15-16

እነሆ፤ ዛሬ ሕይወትንና በረከትን፣ ሞትንና ጥፋትን በፊትህ አኑሬአለሁ። አምላክህን እግዚአብሔርን እንድትወድድ፣ በመንገዱም እንድትሄድና ትእዛዙን፣ ሥርዐቱንና ሕጉን እንድትጠብቅ አዝዝሃለሁ፤ ከዚያም በሕይወት ትኖራለህ፤ ትበዛለህም፤ አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በምትገባበት ምድር ይባርክሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 54:10

ተራሮች ቢናወጡ፣ ኰረብቶች ከስፍራቸው ቢወገዱ እንኳ፣ ለአንቺ ያለኝ ጽኑ ፍቅር አይናወጥም፤ የገባሁትም የሰላም ቃል ኪዳን አይፈርስም” ይላል መሓሪሽ እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 61:8

“እኔ እግዚአብሔር ፍትሕን ስለምወድድ፣ ዝርፊያንና በደልን እጠላለሁ፤ በታማኝነቴም የሚገባቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ ከእነርሱም ጋራ የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 31:31-34

“ከእስራኤል ቤትና፣ ከይሁዳ ቤት ጋራ” ይላል እግዚአብሔር፣ “አዲስ ኪዳን የምገባበት፣ ጊዜ ይመጣል። ከግብጽ አወጣቸው ዘንድ፣ እጃቸውን ይዤ በመራኋቸው ጊዜ፣ ከአባቶቻቸው ጋራ እንደገባሁት ኪዳን አይደለም፤ የእነርሱ ባል ሆኜ ሳለሁ፣ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና።” ይላል እግዚአብሔር። “ነገር ግን ከዚያ ጊዜ በኋላ፣ ከእስራኤል ቤት ጋራ የምገባው ኪዳን ይህ ነው” ይላል እግዚአብሔር፤ “ሕጌን በአእምሯቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ። እኔ አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ። ከእንግዲህ ማንም ሰው ባልንጀራውን፣ ወይም ወንድሙን፣ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ አያስተምርም፤ ከትንሹ ጀምሮ እስከ ትልቁ፣ ሁሉም እኔን ያውቁኛልና፤” ይላል እግዚአብሔር። “በደላቸውን ይቅር እላለሁ፤ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ አላስብም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 34:25

“ ‘ከእነርሱ ጋራ የሰላም ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከዚያም ምድሪቱን ከዱር አራዊት ነጻ አደርጋለሁ፤ እነርሱም በምድረ በዳ ይኖራሉ፤ በደንም ውስጥ ያለ ሥጋት ይተኛሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 36:26-27

አዲስ ልብ እሰጣችኋለሁ፤ አዲስ መንፈስም በውስጣችሁ አሳድራለሁ፤ የድንጋይ ልባችሁን ከእናንተ አስወግዳለሁ፤ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ። መንፈሴን በውስጣችሁ አሳድራለሁ፤ ሥርዐቴን እንድትከተሉና ሕጌን በጥንቃቄ እንድትጠብቁ አደርጋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚልክያስ 2:5

“ከርሱ ጋራ የገባሁት ኪዳን የሕይወትና የሰላም ኪዳን ነበር፤ እነርሱንም ሰጠሁት፤ ይህም ክብርን አመጣ፤ እርሱም አከበረኝ፤ ስሜን በመፍራትም ጸና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 26:28

ስለ ብዙዎች የኀጢአት ይቅርታ የሚፈስስ የአዲስ ኪዳን ደሜ ይህ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 22:20

እንደዚሁም ከእራት በኋላ ጽዋውን አንሥቶ እንዲህ አለ፤ “ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈስሰው ደሜ የሚመሠረት አዲስ ኪዳን ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 8:6-7

ነገር ግን ኢየሱስ መካከለኛ የሆነበት ኪዳን ከቀድሞው እንደሚበልጥ ሁሉ፣ የተቀበለውም አገልግሎት ከእነርሱ አገልግሎት ይበልጣል፤ ይህም የተመሠረተው በተሻለ የተስፋ ቃል ላይ ነው። የመጀመሪያው ኪዳን ምንም ጕድለት ባይገኝበት ኖሮ፣ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 9:15

ስለዚህም የተጠሩት፣ ተስፋ የተሰጠውን የዘላለም ርስት እንዲቀበሉ ክርስቶስ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው፤ በመጀመሪያው ኪዳን ሥር በነበሩበት ጊዜ ከሠሩት ኀጢአት ነጻ ለማውጣት ቤዛ ሆኖ ሞቷልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:16-17

“ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእነርሱ ጋራ የምገባው ኪዳን ይህ ነው፤ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልባቸው አኖራለሁ፤ በአእምሯቸውም እጽፈዋለሁ።” ደግሞም፣ “ኀጢአታቸውንና ዐመፃቸውን፣ ከእንግዲህ አላስብም” ይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 11:27

ኀጢአታቸውንም ሳስወግድ፣ ከእነርሱ ጋራ የምገባው ኪዳኔ ይህ ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 12:1-3

እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “ከአገርህ ከወገንህ ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ሂድ። በዚያም ምድር ጽኑ ራብ ገብቶ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ አብራም ለጥቂት ጊዜ በዚያ ለመኖር ወደ ግብጽ ወረደ። ግብጽ ለመግባት ጥቂት ሲቀረው አብራም ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፤ “መቼም አንቺ ውብ ሴት መሆንሽን ዐውቃለሁ፤ ግብጻውያን አንቺን በሚያዩበት ጊዜ፣ ‘ይህች ሚስቱ ናት’ ብለው እኔን ይገድላሉ፤ አንቺን ግን ይተዉሻል። ስለዚህ ለአንቺ ሲሉ እንዲንከባከቡኝ፣ ሕይወቴም እንድትተርፍ፣ ‘እኅቱ ነኝ’ በዪ።” አብራም በግብጽ አገር እንደ ደረሰ ግብጻውያን፣ ሦራ እጅግ ውብ ሴት እንደ ሆነች አዩ፤ የፈርዖንም ሹማምት ባዩአት ጊዜ፣ ለፈርዖን አድንቀው ነገሩት፤ ወደ ቤተ መንግሥትም ወሰዷት። በርሷም ምክንያት ፈርዖን አብራምን አክብሮ አስተናገደው፤ በጎችና ከብቶች፣ ተባዕትና እንስት አህዮች፣ ወንድና ሴት አገልጋዮች እንዲሁም ግመሎችን ሰጠው። እግዚአብሔርም በአብራም ሚስት በሦራ ምክንያት ፈርዖንንና ቤተ ሰዎቹን በጽኑ ደዌ መታቸው። ከዚያም ፈርዖን አብራምን አስጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ይህ ያደረግህብን ነገር ምንድን ነው? ‘ሚስትህ እንደ ሆነች ለምን አልነገርኸኝም?’ ለምን ‘እኅቴ ናት’ አልኸኝ? ሚስቴ ላደርጋት ነበር። በል አሁንም ሚስትህ ይህችው፤ ይዘሃት ሂድ!” “ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ፤ ደግሞም እባርክሃለሁ፤ ስምህን ገናና አደርገዋለሁ፤ ለሌሎች በረከት ትሆናለህ። ከዚያም ፈርዖን ስለ አብራም ለባለሟሎቹ ትእዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም አብራምን ከሚስቱና ከንብረቱ ሁሉ ጋራ አሰናበቱት። የሚባርኩህን እባርካለሁ፤ የሚረግሙህን ረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም፣ በአንተ ይባረካሉ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 17:1-2

አብራም ዕድሜው 99 ዓመት በሆነ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ተገልጦለት እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ በፊቴ ተመላለስ፤ ነቀፋም አይኑርብህ፤ አንተና ከአንተም በኋላ የሚመጣው ዘርህ የምትጠብቁት ኪዳን ይህ ነው፤ በመካከላችሁ ያለ ወንድ ሁሉ ይገረዝ። ስለዚህ ሁላችሁም ሸለፈታችሁን ትገረዛላችሁ፤ ይህም በእኔና በእናንተ መካከል ላለው ኪዳን ምልክት ይሆናል። የሚመጣውም ትውልድ ሁሉ፣ ማንኛውም ወንድ ልጅ፣ ስምንት ቀን ሲሞላው ይገረዝ፤ እንደዚሁም በቤትህ የተወለደውና ከውጭ በገንዘብ የተገዛ ባዕድ ሁሉ ይገረዝ። በቤትህ የተወለደም ሆነ በገንዘብህ የተገዛ ሁሉ መገረዝ አለበት፤ በሥጋችሁ የሚፈጸመው ይህ ኪዳኔ የዘላለም ኪዳን ይሆናል። የሥጋ ሸለፈቱን ያልተገረዘ ማንኛውም ወንድ ኪዳኔን በማፍረሱ ከወገኖቹ ይወገድ።” እግዚአብሔር አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “ሦራን ከእንግዲህ ሦራ ብለህ አትጠራትም፤ ስሟ ከዛሬ ጀምሮ ሣራ ይሁን። እኔ እባርካታለሁ ከርሷም ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ የብዙም ሕዝቦች እናት ትሆን ዘንድ እባርካታለሁ፤ የሕዝቦችም ነገሥታት ከርሷ ይወጣሉ።” አብርሃምም በግንባሩ መሬት ላይ ተደፋ፤ ሣቀና በልቡ፣ “እንዲያው ምንስ ቢሆን የመቶ ዓመት ሽማግሌ የልጅ አባት መሆን ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመቷ ልጅ መውለድ ትችላለችን?” አለ። አብርሃም እግዚአብሔርን፣ “እስማኤልን ብቻ ባርከህ ባኖርህልኝ” አለው። እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ይሁን ዕሺ፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይሥሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ እኔም ከርሱ በኋላ ለዘሩ ሁሉ የሚሆን የዘላለም ኪዳን ከርሱ ጋራ እገባለሁ። በእኔና በአንተ መካከል የተመሠረተውን ኪዳን አጸናለሁ፤ ዘርህንም እጅግ አበዛለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 22:16-18

እንዲህም አለው፤ “እግዚአብሔርም በራሴ ማልሁ አለ፤ አንዱን ልጅህን ለእኔ ለመስጠት አልሣሣህምና፣ በርግጥ እባርክሃለሁ፤ ዘርህን እንደ ሰማይ ከዋክብት፣ እንደ ባሕር ዳር አሸዋም አበዛዋለሁ። ዘሮችህም የጠላቶቻቸውን ደጆች ይወርሳሉ፤ አሕዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ፤ ቃሌን ሰምተሃልና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 34:27-28

ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እነዚህን ቃሎች ጻፋቸው፤ በእነዚህ ቃሎች መሠረት ከአንተና ከእስራኤል ጋራ ቃል ኪዳን አድርጌአለሁና” አለው። ሙሴ እህል ሳይበላ፣ ውሃም ሳይጠጣ ከእግዚአብሔር ጋራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በዚያ ነበር፤ በጽላቱ ላይ የቃል ኪዳኑን ቃሎች፣ ዐሥርቱ ትእዛዛትን ጻፈ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 5:2-3

አምላካችን እግዚአብሔር በኮሬብ ከእኛ ጋራ ቃል ኪዳን ገብቷል። በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር። የባልንጀራህን ሚስት አትመኝ። በባልንጀራህ ቤትም ሆነ በመሬቱ፣ በወንድ ሆነ በሴት አገልጋዩ፣ በበሬውም ሆነ በአህያው ወይም የርሱ በሆነው በማንኛውም ነገር ላይ ዐይንህን አትጣል።” እግዚአብሔር በተራራው ላይ በእሳቱ፣ በደመናውና በድቅድቁ ጨለማ ውስጥ ለማኅበራችሁ ሁሉ በከፍተኛ ድምፅ የተናገራችሁ ትእዛዞቹ እነዚህ ናቸው፤ የጨመረውም ሌላ የለም፤ ትእዛዞቹንም በሁለት የድንጋይ ጽላት ላይ ጽፎ ሰጠኝ። ተራራው በእሳት ሲቃጠል፣ ከጨለማው ውስጥ ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ፣ እናንተ የየነገዶቻችሁ አለቆችና ሽማግሌዎቻችሁም በሙሉ ወደ እኔ ዘንድ መጣችሁ፤ እንዲህም አላችሁ፤ “አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ግርማውን አሳይቶናል፤ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል። እግዚአብሔር አነጋግሮትም እንኳ፣ ሰው በሕይወት ሊኖር እንደሚችል በዛሬው ቀን አይተናል። ከእንግዲህ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ድምፅ ብንሰማ እንሞታለን፤ ይህችም ታላቅ እሳት ፈጽማ ታጠፋናለች፤ ታዲያ ለምን እንሙት? ለመሆኑ ከእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር እኛ እንደ ሰማነው ሁሉ፣ የሕያው እግዚአብሔርን ድምፅ ሰምቶ በሕይወት ለመኖር የቻለ ከሥጋ ለባሽ ማን አለ? አንተ ቅረብ፤ አምላካችን እግዚአብሔር የሚለውን ሁሉ ስሙ፤ ከዚያም አምላካችን እግዚአብሔር የሚነግርህን ሁሉ ንገረን፤ እኛም እንሰማለን፤ እናደርገዋለንም።” ይህን ስትነግሩኝ እግዚአብሔር ሰማ፤ እግዚአብሔርም አለኝ፤ “ይህ ሕዝብ ምን እንዳለህ ሰምቻለሁ፤ ያሉትም ሁሉ መልካም ነው። ታዲያ ለእነርሱም ሆነ ለልጆቻቸው ለዘላለም መልካም እንዲሆንላቸው፣ እኔን እንዲፈሩና ሁልጊዜ ትእዛዞቼን ሁሉ እንዲጠብቁ እንደዚህ ያለ ልብ ቢኖራቸው ምናለ! እግዚአብሔር ይህን ቃል ኪዳን የገባውም ከአባቶቻችን ጋራ ሳይሆን፣ ዛሬ እዚህ በሕይወት ከምንገኘው ከእኛ ከሁላችን ጋራ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 89:34

ኪዳኔን አላፈርስም፤ ከአፌ የወጣውንም አላጥፍም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 50:5

“በመሥዋዕት ከእኔ ጋራ ኪዳን የገቡትን፣ ቅዱሳኔን ወደ እኔ ሰብስቧቸው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 25:1

እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አምላኬ ነህ፤ ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ስምህንም አወድሳለሁ፤ አስቀድሞ የታሰበውን፣ ድንቅ ነገር፣ በፍጹም ታማኝነት አድርገሃልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 53:5

ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 37:26

ከእነርሱም ጋራ የሰላም ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ቃል ኪዳኑም የዘላለም ይሆናል። አጸናቸዋለሁ፤ አበዛቸዋለሁ፤ መቅደሴንም በመካከላቸው ለዘላለም አኖራለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:17-18

“ሕግንና የነቢያትን ቃል ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ለመፈጸም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፤ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ሕግ ሁሉ ይፈጸማል እንጂ ከሕግ አንዲት ፊደል ወይም አንዲት ነጥብ እንኳ አትሻርም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 4:13

እርሱ የዓለም ወራሽ እንዲሆን አብርሃምና ዘሩ ተስፋን የተቀበሉት በሕግ በኩል አልነበረም፤ ነገር ግን በእምነት ከሆነው ጽድቅ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 3:15-16

ወንድሞች ሆይ፤ ከሰው ዕለታዊ ሕይወት የተለመደውን ምሳሌ አድርጌ ላቅርብ፤ የሰው ኪዳን እንኳ አንድ ጊዜ ከጸደቀ በኋላ ማንም ሊሽረው ወይም በርሱ ላይ ሊጨምርበት እንደማይችል ሁሉ፣ በዚህም ጕዳይ ቢሆን እንደዚሁ ነው። የተስፋውም ቃል የተነገረው ለአብርሃምና ለዘሩ ነበር፤ መጽሐፍ፣ ለብዙ ሰዎች እንደሚነገር፣ “ለዘሮቹ” አይልም፤ ነገር ግን ለአንድ ሰው እንደሚነገር፣ “ለዘርህ” ይላል፤ እርሱም ክርስቶስ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 3:29

የክርስቶስ ከሆናችሁ፣ እናንተ የአብርሃም ዘር ናችሁ፤ እንደ ተስፋውም ቃል ወራሾች ናችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:122

ለባሪያህ በጎነት ዋስትና ሁን፤ እብሪተኞች እንዲጨቍኑኝ አትፍቀድላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 103:17

የእግዚአብሔር ምሕረት ግን፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም በሚፈሩት ላይ ነው፤ ጽድቁም እስከ ልጅ ልጅ ድረስ በላያቸው ይሆናል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 56:4-5

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሰንበቶቼን ለሚያከብሩ ጃንደረቦች፣ ደስ የሚያሠኘኝን ለሚመርጡ፣ ቃል ኪዳኔን፣ ለሚጠብቁ በቤተ መቅደሴና በቅጥሮቼ ውስጥ፣ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የበለጠ፣ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ ለዘላለም፣ የማይጠፋ ስም እሰጣቸዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 12:14

“ይህን ቀን መታሰቢያ ታደርጉታላችሁ፤ በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ ቋሚ ሥርዐት ሆኖ የእግዚአብሔር በዓል አድርጋችሁ አክብሩት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 34:10

ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ከአንተ ጋራ ኪዳን እገባለሁ፤ ከዚህ ቀደም በዓለም ሁሉ ለየትኛውም ሕዝብ ከቶ ያልተደረገ፣ በሕዝብህ ሁሉ ፊት ድንቅ አደርጋለሁ፤ በመካከላቸው ዐብረሃቸው የምትኖር ሕዝብ እኔ እግዚአብሔር ለአንተ የማደርግልህ ሥራ የቱን ያህል አስፈሪ እንደ ሆነ ያያሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 4:23-24

አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ የገባውን ኪዳን እንዳትረሱ ተጠንቀቁ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር የከለከለውን ጣዖት በማንኛውም ዐይነት መልክ ለራሳችሁ አታብጁ። አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚባላ እሳት፣ ቀናተኛም አምላክ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 7:12-13

እነዚህን ሕግጋት ብታዳምጥና በጥንቃቄ ብትጠብቃቸው፣ አምላክህ እግዚአብሔር ለአባቶችህ እንደ ማለላቸው ከአንተ ጋራ የገባውን የፍቅር ኪዳኑን ይጠብቃል። ይወድድሃል፤ ይባርክሃል፤ ያበዛሃልም። ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር የማሕፀንህን ፍሬ፣ የምድርህን ሰብል፣ እህልህን፣ አዲሱን ወይንና ዘይት፤ የከብት መንጋህን ጥጆች፣ የበግና የፍየል መንጋህን ግልገሎች ይባርካል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 25:10

ኪዳኑንና ምስክርነቱን ለሚጠብቁ፣ የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 49:8

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በተወደደ ጊዜ እመልስልሃለሁ፤ በድነት ቀን እረዳሃለሁ። ለሕዝቡ ቃል ኪዳን እንድትሆን፣ ምድሪቱን እንደ ገና እንድትሠራት፣ ጠፍ የሆኑትን ርስቶች ለየባለቤታቸው እንድትመልስ፣ እጠብቅሃለሁ፤ እሠራሃለሁም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 31:33

“ነገር ግን ከዚያ ጊዜ በኋላ፣ ከእስራኤል ቤት ጋራ የምገባው ኪዳን ይህ ነው” ይላል እግዚአብሔር፤ “ሕጌን በአእምሯቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ። እኔ አምላክ እሆናቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 16:60

ነገር ግን በልጅነትሽ ጊዜ ከአንቺ ጋራ የገባሁትን ቃል ኪዳን ዐስባለሁ፤ ለዘላለምም የሚኖር ቃል ኪዳን ከአንቺ ጋራ እመሠርታለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 11:1-2

እንግዲህ እግዚአብሔር ሕዝቡን ተዋቸውን? ብዬ እጠይቃለሁ፤ ከቶ አይሆንም! እኔ ራሴ ከብንያም ነገድ፣ የአብርሃም ዘር የሆንሁ እስራኤላዊ ነኝ። ዐይኖቻቸው እንዳያዩ ይጨልሙ፤ ወገባቸውም ለዘላለም ይጕበጥ።” ተመልሰው እስከማይድኑ ድረስ ተሰናከሉን? ብዬ እንደ ገና እጠይቃለሁ፤ ከቶ አይሆንም! ይልቁንም እስራኤልን ለማስቀናት ሲባል በእነርሱ መተላለፍ ምክንያት ድነት ለአሕዛብ መጥቷል። ነገር ግን የእነርሱ መተላለፍ ለዓለም በረከት ከሆነ፣ ውድቀታቸውም ለአሕዛብ በረከት ከሆነ፣ ሙላታቸው ምን ያህል ታላቅ በረከት ያመጣ ይሆን? አሕዛብ ሆይ፤ ለእናንተ እናገራለሁ፤ የአሕዛብ ሐዋርያ እንደ መሆኔ መጠን አገልግሎቴን በትጋት እፈጽማለሁ፤ ይኸውም የገዛ ወገኖቼን እንዲቀኑ አነሣሥቼ ከእነርሱ ጥቂቱን ለማዳን ተስፋ በማድረግ ነው። የእነርሱ መተው ለዓለም ዕርቅን ካስገኘ፣ ተቀባይነት ማግኘታቸውማ ከሞት መነሣት ነው ከማለት በቀር ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? በኵር ሆኖ የቀረበው የቡሖው ክፍል ቅዱስ ከሆነ፣ ቡሖው ደግሞ ቅዱስ ነው፤ ሥሩ ቅዱስ ከሆነ፣ ቅርንጫፎቹም ቅዱሳን ናቸው። ከቅርንጫፎቹ አንዳንዶቹ ቢሰበሩ፣ አንተም የበረሓ ወይራ ሆነህ ሳለ በሌሎቹ መካከል ገብተህ ከተጣበቅህና ከወይራው ዘይት ሥር የሚገኘውን በረከት ተካፋይ ከሆንህ፣ በእነዚያ ቅርንጫፎች ላይ አትኵራራ። ብትኰራ ግን ይህን አስተውል፤ አንተ ሥሩን አትሸከምም፤ ሥሩ አንተን ይሸከምሃል እንጂ። እንግዲህ፣ “ቅርንጫፎች የተሰበሩት እኔ እንድገባ ነው” ትል ይሆናል። እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝብ አልጣላቸውም። ኤልያስ በእስራኤል ላይ ክስ ወደ እግዚአብሔር እንዴት እንዳቀረበ፣ መጽሐፍ ስለ እርሱ ምን እንደሚል አታውቁምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 7:22

ከዚህ መሐላ የተነሣ፣ ኢየሱስ ለተሻለ ኪዳን ዋስ ሆኗል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 89:28

ምሕረቴንም ለዘላለም ለርሱ እጠብቃለሁ፤ ከርሱ ጋራ የገባሁት ኪዳንም ጸንቶ ይኖራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:49

ለአገልጋይህ የገባኸውን ቃል ዐስብ፤ በዚያ ተስፋ ሰጥተኸዋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 1:1-17

የዳዊት ልጅ፣ የአብርሃም ልጅ የሆነው የኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ሐረግ የሚከተለው ነው። ሕዝቅያስ ምናሴን ወለደ፤ ምናሴ አሞንን ወለደ፤ አሞንም ኢዮስያስን ወለደ፤ ኢዮስያስ በባቢሎን ምርኮ ጊዜ፣ ኢኮንያንንና ወንድሞቹን ወለደ። ከባቢሎን ምርኮ በኋላ፣ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያልም ዘሩባቤልን ወለደ፤ ዘሩባቤል አብዩድን ወለደ፤ አብዩድ ኤልያቄምን ወለደ፤ ኤልያቄም አዛርን ወለደ፤ አዛር ሳዶቅን ወለደ፤ ሳዶቅ አኪምን ወለደ፤ አኪምም ኤልዩድን ወለደ፤ ኤልዩድ አልዓዛርን ወለደ፤ አልዓዛር ማታንን ወለደ፤ ማታን ያዕቆብን ወለደ፤ ያዕቆብ ዮሴፍን ወለደ፤ ዮሴፍም የኢየሱስ ክርስቶስ እናት የማርያም ዕጮኛ ነበር። እንግዲህ ከአብርሃም እስከ ዳዊት ዐሥራ አራት ትውልድ፣ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ዐሥራ አራት ትውልድ፣ ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ ልደት ዐሥራ አራት ትውልድ ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 1:72-73

ይህንም ያደረገው ለአባቶቻችን ምሕረቱን ለማሳየት፣ ቅዱስ ኪዳኑን ለማስታወስ፣ ለአባታችን ለአብርሃም የማለውን መሐላ ለማሰብ፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 3:25

እናንተም የነቢያት ልጆች ናችሁ፤ ደግሞም እግዚአብሔር ለአብርሃም፣ ‘በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ’ ብሎ የገባው ኪዳን ወራሾች ናችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 9:4-5

እነርሱም የእስራኤል ሕዝብ ናቸው፤ ልጅ መሆን፣ መለኮታዊ ክብር፣ ኪዳን፣ ሕግን መቀበል፣ የቤተ መቅደስ ሥርዐትና ተስፋ የእነርሱ ናቸውና። አባቶችም የእነርሱ ናቸው፤ ክርስቶስም በሥጋ የትውልድ ሐረጉ የሚቈጠረው ከእነርሱ ነው፤ እርሱም፣ ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘላለም የተመሰገነ አምላክ ነው! አሜን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 1:20

በእግዚአብሔር የተሰጡ ተስፋዎች ሁሉ፣ “አዎን” የሚሆኑት በርሱ ነውና፤ እኛም በርሱ አማካይነት ለእግዚአብሔር ክብር፣ “አሜን” የምንለው በዚህ ምክንያት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 3:10-14

ሕግን በመጠበቅ የሚተማመኑ ሁሉ ከርግማን በታች ናቸው፤ “በሕግ መጽሐፍ የተጻፈውን ሁሉ የማያደርግ የተረገመ ነው” ተብሎ ተጽፏልና። “ጻድቅ በእምነት ይኖራል” ስለ ተባለ፣ ማንም በእግዚአብሔር ፊት በሕግ እንደማይጸድቅ ግልጽ ነው። ሕግ በእምነት ላይ የተመሠረተ አይደለም፤ ነገር ግን “እነዚህን የሚፈጽም ሰው በእነርሱ ሕያው ይሆናል” ተብሏል። “በዕንጨት ላይ የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ፣ ክርስቶስ ስለ እኛ ርግማን ሆኖ ከሕግ ርግማን ዋጅቶናል። ለአብርሃም የተሰጠው በረከት፣ በክርስቶስ ኢየሱስ ለአሕዛብ እንዲደርስ ዋጅቶናል፤ ይኸውም በእምነት የመንፈስን ተስፋ እንድንቀበል ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 9:1

የመጀመሪያው ኪዳን የአምልኮ ሥርዐትና ምድራዊ መቅደስ ነበረው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 9:8-9

የመጀመሪያዪቱ ድንኳን ቆማ እስካለች ድረስ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚወስደው መንገድ ገና እንዳልተገለጠ መንፈስ ቅዱስ ያሳያል። ይህም ለአሁኑ ዘመን ምሳሌ ሲሆን፣ የሚቀርቡት መባና መሥዋዕት የሚያመልከውን ሰው ኅሊና ፍጹም ሊያደርጉ አልቻሉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 26:18

እግዚአብሔር በሰጠህ ተስፋ መሠረት አንተ፣ ሕዝቡና ርስቱ መሆንህን፣ ትእዛዙንም ሁሉ እንደምትጠብቅ በዛሬው ዕለት ተናግሯል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 147:19-20

ቃሉን ለያዕቆብ፣ ሥርዐቱንና ፍርዱን ለእስራኤል ይገልጣል። እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን መልሶ ይሠራታል፤ ከእስራኤል የተበተኑትን ይሰበስባል። ይህን ለማንኛውም ሌላ ሕዝብ አላደረገም፤ እነርሱም ፍርዱን አላወቁም። ሃሌ ሉያ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 28:13-15

እግዚአብሔርም ከጫፉ ላይ ቆሞ እንዲህ አለ፤ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ የተኛህበትን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ። ዘርህ እንደ ምድር አሸዋ ይበዛል፤ በምዕራብና በምሥራቅ፣ በሰሜንና በደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በአንተና በዘርህ አማካይነት ይባረካሉ። እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እመልስሃለሁ፤ የሰጠሁህን ተስፋ እስከምፈጽምልህ ድረስ አልተውህም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 17:19

እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ይሁን ዕሺ፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይሥሐቅ ብለህ ትጠራዋለህ፤ እኔም ከርሱ በኋላ ለዘሩ ሁሉ የሚሆን የዘላለም ኪዳን ከርሱ ጋራ እገባለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 30:19-20

ሕይወትንና ሞትን፣ በረከትንና ርግማንን በፊትህ እንዳስቀመጥሁ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እጠራብሃለሁ። እንግዲህ አንተና ልጆችህ በሕይወት እንድትኖሩ ሕይወትን ምረጥ፤ እንዲሁም ዛሬ እኔ በማዝዝህ ሁሉ መሠረት አንተና ልጆችህ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ተመልሳችሁ በፍጹም ልባችሁና በፍጹም ነፍሳችሁ እርሱን ስትታዘዙ፣ ይኸውም አምላክህን እግዚአብሔርን እንድትወድድ፣ ቃሉን እንድታደምጥና ከርሱ ጋራ እንድትጣበቅ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕይወትህ ነው፤ ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ ሊሰጣቸው በማለላቸው ምድር ረዥም ዕድሜ ይሰጥሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 147:14

በድንበርሽ ውስጥ ሰላም ያሰፍናል፤ ማለፊያ ስንዴም ያጠግብሻል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 78:68-69

ነገር ግን የይሁዳን ነገድ፣ የወደዳትን የጽዮንን ተራራ መረጠ። መቅደሱን እንደ ታላቅ ከፍታ፣ ለዘላለም እንደ መሠረታት ምድር ሠራት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 59:21

“በእኔ በኩል፣ ከእነርሱ ጋራ የምገባው ኪዳኔ ይህ ነው” ይላል እግዚአብሔር፤ “በአንተም ላይ ያለው መንፈሴ፣ በአፍህ ያኖርሁት ቃሌ ከአፍህ፣ ከልጆችህ አፍ፣ ከዘር ዘሮቻቸውም አፍ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም አይለይም” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 34:24

እኔ እግዚአብሔር አምላካቸው እሆናለሁ፤ ባሪያዬ ዳዊትም በመካከላቸው ገዥ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 26:29

እላችኋለሁ፤ በአባቴ መንግሥት ከእናንተ ጋራ በአዲስ መልክ እስከምጠጣበት እስከዚያ ቀን ድረስ፣ ከአሁን ጀምሮ ከዚህ የወይን ፍሬ አልጠጣም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 1:68-69

“የእስራኤል አምላክ፣ ጌታ ይመስገን፤ መጥቶ ሕዝቡን ተቤዥቷልና። በብላቴናው በዳዊት ቤት፣ የድነት ቀንድ አስነሥቶልናል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 2:39

የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ እንዲሁም ጌታ አምላካችን ወደ ራሱ ለሚጠራቸው፣ በሩቅ ላሉትም ሁሉ ነውና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 10:12-13

በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ልዩነት የለም፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፤ የሚለምኑትንም አብዝቶ ይባርካል፤ “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 2:9

እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ የተቀደሰ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ገንዘቡ ያደረገው ሕዝብ ናችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 9:11

ከእንግዲህ ሕይወት ያለው ፍጡር ሁሉ በጥፋት ውሃ እንደማይጠፋ፣ ዳግመኛም ምድርን የሚያጠፋ ውሃ ከቶ እንደማይመጣ ከእናንተ ጋራ ኪዳን እገባለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 17:4-5

“እነሆ፤ የምገባልህ ኪዳን ይህ ነው፤ የብዙ ሕዝቦች አባት ትሆናለህ። ከእንግዲህ ወዲያ ስምህ አብራም መባሉ ቀርቶ አብርሃም ይሆናል፤ የብዙ ሕዝቦች አባት አድርጌሃለሁና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 12:24

“እናንተም ሆነ ልጆቻችሁ ይህን መመሪያ ቋሚ ሥርዐት አድርጋችሁ ትታዘዛላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 111:5

ለሚፈሩት ምግብን ይሰጣል፤ ኪዳኑንም ለዘላለም ያስባል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 146:6

እርሱ ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንም፣ በውስጣቸውም የሚኖሩትን ሁሉ የፈጠረ፣ ታማኝነቱም ለዘላለም የሆነ ነው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 53:12

ስለዚህ ድርሻውን ከታላላቆች ጋራ እሰጠዋለሁ፤ ምርኮውን ከኀያላን ጋራ ይካፈላል፤ እስከ ሞት ድረስ ሕይወቱን አሳልፎ በመስጠቱ፣ ከክፉ አድራጊዎችም ጋራ በመቈጠሩ፣ የብዙዎችን ኀጢአት ተሸከመ፤ ስለ ዐመፀኞችም ማለደ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 33:20-21

“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ለቀንና ለሌሊት የወሰንሁትን ሥርዐት በማፋለስ ቀንና ሌሊት በተወሰነላቸው ጊዜ እንዳይፈራረቁ ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፣ በዚያ ጊዜ ከአገልጋዬ ከዳዊት ጋራ የገባሁትን ኪዳን፣ እንዲሁም በፊቴ በክህነት ከሚያገለግሉት ሌዋውያን ጋራ የገባሁትን ኪዳን ማፍረስ ይቻላል፤ ዳዊትም ከእንግዲህ በዙፋኑ ላይ የሚነግሥ ዘር አይኖረውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 11:19

የማያወላውል ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ አዲስ መንፈስ በውስጣቸው አኖራለሁ፤ ድንጋዩን ልብ ከውስጣቸው አወጣለሁ፤ ሥጋ ልብም እሰጣቸዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 16:62

ስለዚህ ከአንቺ ጋራ ቃል ኪዳኔን ዐድሳለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂአለሽ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 4:16

ስለዚህ ተስፋው በእምነት መጥቷል፤ ይኸውም ተስፋው በጸጋ እንዲሆንና ለአብርሃም ዘር ሁሉ ዋስትና ይሆን ዘንድ ነው፤ ይህም በሕግ የርሱ ለሆኑት ብቻ ሳይሆን፣ በእምነት የአብርሃም ለሆኑትም ነው፤ እርሱም የሁላችን አባት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 3:15

ወንድሞች ሆይ፤ ከሰው ዕለታዊ ሕይወት የተለመደውን ምሳሌ አድርጌ ላቅርብ፤ የሰው ኪዳን እንኳ አንድ ጊዜ ከጸደቀ በኋላ ማንም ሊሽረው ወይም በርሱ ላይ ሊጨምርበት እንደማይችል ሁሉ፣ በዚህም ጕዳይ ቢሆን እንደዚሁ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 4:4-5

ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን፣ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ ይህም የሆነው የልጅነትን መብት እናገኝ ዘንድ ከሕግ በታች ያሉትን ለመዋጀት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 105:9

ከአብርሃም ጋራ የገባውን ቃል ኪዳን፣ ለይሥሐቅም የማለውን መሐላ አይረሳም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 103:18

ኪዳኑን በሚጠብቁት ላይ፣ ትእዛዙንም ለመፈጸም በሚተጕት ላይ ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:17

“ሕግንና የነቢያትን ቃል ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ለመፈጸም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:16

“ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእነርሱ ጋራ የምገባው ኪዳን ይህ ነው፤ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልባቸው አኖራለሁ፤ በአእምሯቸውም እጽፈዋለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 34:27

ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እነዚህን ቃሎች ጻፋቸው፤ በእነዚህ ቃሎች መሠረት ከአንተና ከእስራኤል ጋራ ቃል ኪዳን አድርጌአለሁና” አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 4:37-38

አባቶችህን ከመውደዱ የተነሣና ከእነርሱም በኋላ ዘራቸውን ስለ መረጠ፣ ከአንተ ጋራ በመሆን በታላቅ ኀይሉ ከግብጽ አወጣህ፤ ዛሬ እንደ ሆነው ሁሉ ከአንተ ይልቅ ታላቅና ብርቱ የሆኑትን አሕዛብ ከፊትህ በማስወጣት ወደ ምድራቸው አስገብቶህ ለአንተ ርስት አድርጎ ለመስጠት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 89:30-32

“ልጆቹ ሕጌን ቢተዉ፣ ደንቤን ባይጠብቁ፣ ሥርዐቴን ቢጥሱ፣ ትእዛዜንም ባያከብሩ፣ ኀጢአታቸውን በበትር፣ በደላቸውን በጅራፍ እቀጣለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 25:6-7

እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህንና ፍቅርህን ዐስብ፤ እነዚህ ከጥንት የነበሩ ናቸውና። የልጅነቴን ኀጢአት፣ መተላለፌንም አታስብብኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ ብዛት፣ እንደ ምሕረትህም መጠን አስበኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 11:26-27

ስለዚህ እስራኤል ሁሉ ይድናሉ፤ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፤ “አዳኝ ከጽዮን ይወጣል፤ ከያዕቆብም ክፋትን ያስወግዳል። ኀጢአታቸውንም ሳስወግድ፣ ከእነርሱ ጋራ የምገባው ኪዳኔ ይህ ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 4:26

ከላይ የሆነችው ኢየሩሳሌም ግን በነጻነት ትኖራለች፤ እርሷም እናታችን ናት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 133:1

ወንድሞች ተስማምተው በአንድነት ሲኖሩ፣ እንዴት መልካም ነው! ምንኛስ ደስ ያሰኛል!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 136:10-12

የግብጽን በኵር የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። እስራኤልን ከመካከላቸው ያወጣ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ በኀያል እጅና በተዘረጋች ክንድ ይህን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 12:18

“እነሆ፤ የመረጥሁት፣ የምወድደውና ነፍሴ ደስ የተሠኘችበት ብላቴናዬ፣ መንፈሴን በርሱ ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍትሕን ያውጃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 1:18-19

ከቀድሞ አባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከንቱ ከሆነ ሕይወት የተዋጃችሁት በሚጠፋ ነገር፣ በብር ወይም በወርቅ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ፤ ነገር ግን እናንተ የተዋጃችሁት ነውርና እንከን እንደሌለበት በግ ደም፣ በክርስቶስ ክቡር ደም ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:31

ታዲያ ለዚህ ምን እንመልሳለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ከሆነ፣ ማን ሊቃወመን ይችላል?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 111:9

ለሕዝቡ መዳንን ሰደደ፤ ኪዳኑንም ለዘላለም አዘዘ፤ ስሙም የተቀደሰና የተፈራ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 53:10-11

መድቀቁና መሠቃየቱ ግን የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበር፤ እግዚአብሔር ነፍሱን የኀጢአት መሥዋዕት ቢያደርገውም እንኳ፣ ዘሩን ያያል፤ ዕድሜውም ይረዝማል፤ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል። ከነፍሱ ሥቃይ በኋላ፣ የሕይወት ብርሃን ያያል፤ ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬ በዕውቀቱ ብዙዎቹን ያጸድቃል፤ መተላለፋቸውንም ይሸከማል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 9:13

ሄዳችሁ፣ ‘ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወድዳለሁ፤’ የሚለውን ቃል ትርጕም አጢኑ፤ ኀጢአተኞችን እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 22:27

የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስታውሳሉ፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለሳሉ፤ የሕዝቦች ነገዶች ሁሉ፣ በፊቱ ይሰግዳሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 5:1-2

እንግዲህ በእምነት ስለ ጸደቅን፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋራ ሰላም አለን። የእግዚአብሔር ጠላቶች ሳለን በልጁ ሞት ከርሱ ጋራ ከታረቅን፣ ዕርቅን ካገኘን በኋላ፣ በሕይወቱማ መዳናችን እንዴት የላቀ አይሆንም! ይህ ብቻ አይደለም። ነገር ግን አሁን ዕርቅን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ ሐሤት እናደርጋለን። ስለዚህ ኀጢአት በአንድ ሰው በኩል ወደ ዓለም እንደ ገባ ሁሉ፣ ሞትም በኀጢአት በኩል ገብቷል፤ በዚሁ መንገድ ሞት ወደ ሰዎች ሁሉ መጣ፤ ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤ ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ኀጢአት በዓለም ላይ ነበር፤ ነገር ግን ሕግ በሌለበት ኀጢአት አይቈጠርም። ይሁን እንጂ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ባሉት፣ እንደ አዳም ሕግን በመጣስ ኀጢአት ባልሠሩት ላይ እንኳ ሞት ነገሠ፤ አዳም ይመጣ ዘንድ ላለው አምሳሉ ነበረ። ነገር ግን ስጦታው እንደ በደሉ መጠን አይደለም፤ በአንድ ሰው መተላለፍ ብዙዎቹ ከሞቱ፣ የእግዚአብሔር ጸጋና በአንዱ ሰው፣ ይኸውም በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የመጣው ስጦታ ለብዙዎች እንዴት አብልጦ ይትረፈረፍ! ደግሞም የእግዚአብሔር ስጦታ እንደ አንዱ ሰው የኀጢአት ውጤት አይደለም፤ ምክንያቱም ፍርዱ የአንድን ሰው ኀጢአት ተከትሎ ኵነኔን አመጣ፤ ስጦታው ግን አያሌ መተላለፍን ተከትሎ ጽድቅን አመጣ። በአንድ ሰው መተላለፍ ምክንያት ሞት በዚህ ሰው በኩል የነገሠ ከሆነ፣ የእግዚአብሔርን የተትረፈረፈ ጸጋና የጽድቅ ስጦታ የተቀበሉት፣ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንዴት አብልጠው በሕይወት አይነግሡ! ከእንግዲህ በአንድ ሰው መተላለፍ የተነሣ ኵነኔ በሁሉ ሰው ላይ እንደ መጣ፣ እንዲሁም በአንዱ የጽድቅ ሥራ ለሰው ሁሉ ሕይወትን የሚሰጥ ጽድቅ ተገኘ። በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኀጢአተኞች እንደ ሆኑ፣ በአንዱ ሰው መታዘዝ ደግሞ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ። በርሱም በኩል አሁን ወደ ቆምንበት ጸጋ በእምነት መግባት ችለናል፤ የእግዚአብሔርንም ክብር ተስፋ በማድረግ ሐሤት እናደርጋለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 105:8

ኪዳኑን ለዘላለም፣ ያዘዘውንም ቃል እስከ ሺሕ ትውልድ ያስባል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 86:15

ጌታ ሆይ፤ አንተ ግን መሓሪና ርኅሩኅ አምላክ ነህ፤ ለቍጣ የዘገየህ፣ ምሕረትህና ታማኝነትህ የበዛ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 3:3-4

ፍቅርና ታማኝነት ከቶ አይለዩህ፤ በዐንገትህ ዙሪያ እሰራቸው፤ በልብህም ጽላት ላይ ጻፋቸው። ምንም ጕዳት ሳያደርስብህ፣ ያለ ምክንያት ሰውን አትክሰስ። በክፉ ሰው አትቅና፤ የትኛውንም መንገዱን አትምረጥ። እግዚአብሔር ጠማማን ሁሉ ይጸየፋልና፤ ለቅን ሰው ግን ምስጢሩን ይገልጥለታል። የእግዚአብሔር ርግማን በክፉዎች ቤት ላይ ነው፤ የጻድቃንን ቤት ግን ይባርካል። እርሱ በዕቡያን ፌዘኞች ላይ ያፌዛል፤ ለትሑታን ግን ሞገስን ይሰጣል። ጠቢባን ክብርን ይወርሳሉ፤ ሞኞችን ግን ለውርደት ያጋልጣቸዋል። በዚያ ጊዜ ሞገስንና ማስተዋልን፣ በእግዚአብሔርና በሰው ዘንድ ታገኛለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 49:8-9

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በተወደደ ጊዜ እመልስልሃለሁ፤ በድነት ቀን እረዳሃለሁ። ለሕዝቡ ቃል ኪዳን እንድትሆን፣ ምድሪቱን እንደ ገና እንድትሠራት፣ ጠፍ የሆኑትን ርስቶች ለየባለቤታቸው እንድትመልስ፣ እጠብቅሃለሁ፤ እሠራሃለሁም፤ የተማረኩትን፣ ‘ኑ ውጡ’ በጨለማ ያሉትን፣ ‘ነጻ ሁኑ!’ እንድትል አድርጌሃለሁ። “በየመንገዱ ዳር ይመገባሉ፤ በተራቈተውም ኰረብታ ሁሉ ላይ መሰማሪያ ያገኛሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 36:28

ለቀድሞ አባቶቻችሁ በሰጠኋቸው ምድር ትኖራላችሁ፤ ሕዝቤም ትሆናላችሁ፤ እኔም አምላክ እሆናችኋሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:37

ምንም አይለየንም፤ በዚህ ሁሉ በወደደን በርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 100:5

እግዚአብሔር ቸር፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤ ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:142

ጽድቅህ ዘላለማዊ ጽድቅ ነው፤ ሕግህም እውነት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:9

በጎ ነገር ከማድረግ አንታክት፤ ተስፋ ካልቈረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 111:4

ድንቅ ሥራው ሲታወስ እንዲኖር አደረገ፤ እግዚአብሔር ቸር፣ ርኅሩኅም ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 44:3

በተጠማ ምድር ላይ ውሃ፤ በደረቅ መሬት ላይ ወንዞችን አፈስሳለሁና፤ መንፈሴን በዘርህ፣ በረከቴንም በልጅ ልጅህ ላይ አወርዳለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 30:5

ቍጣው ለዐጭር ጊዜ ነው፤ ቸርነቱ ግን እስከ ዕድሜ ልክ ነውና፤ ሌሊቱን በልቅሶ ቢታደርም፣ በማለዳ ደስታ ይመጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:7-8

“ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ በሩም ይከፈትላችኋል። የሚለምን ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ ለሚያንኳኳም ይከፈትለታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:16-17

በወንጌል አላፍርም፤ ምክንያቱም ለሚያምን ሁሉ ለድነት የሚሆን የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ ይህም በመጀመሪያ ለአይሁድ፣ ቀጥሎም ለአሕዛብ ነው። በወንጌል የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጧልና፤ ጽድቁም ከእምነት ወደ እምነት የሆነ ነው፤ “ጻድቅ በእምነት ይኖራል” ተብሎ እንደ ተጻፈው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:90

ታማኝነትህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ሁሉ ይኖራል፤ ምድርን መሠረትሃት፤ እርሷም ጸንታ ትኖራለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 57:15

ከፍ ከፍ ያለውና ልዕልና ያለው እርሱ፣ ስሙም ቅዱስ የሆነው፣ ለዘላለም የሚኖረው እንዲህ ይላል፤ “የተዋረዱትን መንፈሳቸውን ለማነሣሣት፣ የተሰበረ ልብ ያላቸውን ለማነቃቃት፣ ከፍ ባለውና በቅዱሱ ስፍራ እኖራለሁ፤ የተሰበረ ልብ ካለውና በመንፈሱ ከተዋረደው ጋራ እሆናለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:33

ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:20-21

በዘላለም ኪዳን ደም የበጎች ታላቅ እረኛ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስን ከሞት ያስነሣው የሰላም አምላክ፣ ፈቃዱን እንድታደርጉ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ ደስ የሚያሠኘውንም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእኛ ያድርግ፤ ለርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን። አሜን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 147:3

ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል፤ ቍስላቸውንም ይጠግናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:47-48

እኔ እወድደዋለሁና፣ በትእዛዝህ ደስ ይለኛል። እጆቼን ወደምወዳቸው ትእዛዞችህ አነሣለሁ፤ ሥርዐትህንም አሰላስላለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 138:2

ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ ስለ ምሕረትህና ስለ ታማኝነትህ፣ ለስምህ ምስጋና አቀርባለሁ፤ ስምህንና ቃልህን፣ ከሁሉ በላይ ከፍ ከፍ አድርገሃልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 41:10

እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 66:5

ኑና፣ እግዚአብሔር ያደረገውን እዩ፤ በሰዎች መካከል ሥራው አስፈሪ ነው!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 89:34-35

ኪዳኔን አላፈርስም፤ ከአፌ የወጣውንም አላጥፍም። አንድ ጊዜ በቅድስናዬ ምያለሁና፣ ዳዊትን አልዋሸውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:55

እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህን በሌሊት ዐስባለሁ፤ ሕግህንም እጠብቃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 9:6

ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ተሽሯል ማለት አይደለም፤ ከእስራኤል የተወለደ ሁሉ እስራኤላዊ አይደለምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 43:10

“ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ፣ እርሱ እኔ እንደ ሆንሁ ትረዱ ዘንድ፣ እናንተ ምስክሮቼ፣ የመረጥሁትም ባሪያዬ ናችሁ” ይላል እግዚአብሔር። “ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም፤ ከእኔም በኋላ አይኖርም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 106:45

ለእነርሱም ሲል ቃል ኪዳኑን ዐሰበ፤ እንደ ምሕረቱም ብዛት ከቍጣው ተመለሰ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 63:3

ምሕረትህ ከሕይወት ይበልጣልና፤ ከንፈሮቼ ያመሰግኑሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 4:20

ይልቁንም በእምነቱ በመጽናት ለእግዚአብሔር ክብርን ሰጠ እንጂ፣ የእግዚአብሔርን ተስፋ አልተጠራጠረም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 138:8

እግዚአብሔር በእኔ ላይ ያለውን ዐላማ ይፈጽማል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ለዘላለም ነው። የእጅህንም ሥራ ቸል አትበል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 104:1-5

ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤ ክብርንና ግርማን ለብሰሃል። ምንጮችን በሸለቆ ውስጥ እንዲሄዱ አደረግህ፤ በተራሮችም መካከል ይፈስሳሉ፤ የዱር እንስሳትም ከዚያ ይጠጣሉ፤ የሜዳ አህዮችም ጥማቸውን ይቈርጣሉ። የሰማይ ወፎች ጐጇቸውን በወንዞቹ ዳር ይሠራሉ፤ በቅርንጫፎችም መካከል ይዘምራሉ። ከላይ ከእልፍኝህ ተራሮችህን ታጠጣለህ፤ ምድርም በሥራህ ፍሬ ትረካለች። ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣ ለእንስሳት ሣርን፣ ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ፤ የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ ወይን፣ ፊቱን የሚያወዛ ዘይት፣ ልቡን የሚያበረታ እህል በዚህ ይገኛል። ደግሞም የእግዚአብሔር ዛፎች፣ እርሱ የተከላቸውም የሊባኖስ ዝግባዎች ጠጥተው ይረካሉ፤ ወፎች ጐጇቸውን በዚያ ይሠራሉ፤ ሽመላ በጥዶቹ ውስጥ ማደሪያ ታገኛለች። ረዣዥሙ ተራራ የዋሊያ መኖሪያ፣ የዐለቱም ዋሻዎች የሽኮኮ መሸሸጊያ ናቸው። ጨረቃን የወቅቶች መለያ አደረግሃት፤ ፀሓይም የምትጠልቅበትን ጊዜ ታውቃለች። ብርሃንን እንደ ሸማ ተጐናጽፈሃል፤ ሰማያትንም እንደ ድንኳን መጋረጃ ዘረጋህ፤ ጨለማን ታመጣለህ፤ ሌሊትም ይሆናል፤ የዱር አራዊትም ሁሉ በዚህ ጊዜ ወጥተው ይራወጣሉ። የአንበሳ ግልገሎች ምግብ ፍለጋ ይጮኻሉ፤ የሚበሉትንም ከእግዚአብሔር ይሻሉ። ፀሓይ በወጣች ጊዜም ይመለሳሉ፤ በየጐሬያቸውም ገብተው ይተኛሉ። ሰውም ወደ ሥራው ይሄዳል፤ እስኪመሽም በተግባሩ ላይ ይሰማራል። እግዚአብሔር ሆይ፤ ሥራህ እንዴት ብዙ ነው! ሁሉን በጥበብ ሠራህ፤ ምድርም በፍጥረትህ ተሞላች። ይህች ባሕር ሰፊና የተንጣለለች ናት፤ ታላላቅና ታናናሽ እንስሳት፣ ስፍር ቍጥር የሌላቸውም የሚርመሰመሱ ፍጥረታት በውስጧ አሉ። መርከቦች በላይዋ ይመላለሳሉ፤ አንተ የፈጠርኸውም ሌዋታን በውስጧ ይፈነጫል። ምግባቸውን በወቅቱ ትሰጣቸው ዘንድ፣ እነዚህ ሁሉ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ። በሰጠሃቸውም ጊዜ፣ አንድ ላይ ያከማቻሉ፤ እጅህንም ስትዘረጋ፣ በመልካም ነገር ይጠግባሉ። ፊትህን ስትሰውር፣ በድንጋጤ ይሞላሉ፤ እስትንፋሳቸውንም ስትወስድባቸው ይሞታሉ፤ ወደ ዐፈራቸውም ይመለሳሉ። የእልፍኝህን አግዳሚ በውሆች ላይ አኖርህ፤ ደመናትን ሠረገላህ አደረግህ፤ በነፋስ ክንፍ ትሄዳለህ። መንፈስህን ስትልክ፣ እነርሱ ይፈጠራሉ፤ የምድርንም ገጽ ታድሳለህ። የእግዚአብሔር ክብር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤ እግዚአብሔር በሥራው ደስ ይበለው፤ እርሱ ምድርን ሲመለከት፣ ትንቀጠቀጣለች፤ ተራሮችም እርሱ ሲዳስሳቸው ይጤሳሉ። በሕይወት ሳለሁ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ቆሜ እስከ ሄድሁ ድረስም አምላኬን እወድሳለሁ። እኔ በእግዚአብሔር ደስ እንደሚለኝ፣ የልቤ ሐሳብ እርሱን ደስ ያሠኘው። ኃጥኣን ከምድር ገጽ ይጥፉ፤ ዐመፀኞች ከእንግዲህ አይገኙ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ። ሃሌ ሉያ። መላእክትህን መንፈስ፣ አገልጋዮችህንም የእሳት ነበልባል ታደርጋለህ። ለዘላለም እንዳትናወጥ፣ ምድርን በመሠረቷ ላይ አጸናት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 5:22-23

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣ ገርነት፣ ራስን መግዛት ነው። እንደነዚህ ያሉትንም የሚከለክል ሕግ የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ሆይ፥ አልፋና ኦሜጋ ነህ! የሰማይና የምድር ፈጣሪ አባት፥ አንተ የመጀመሪያውና የመጨረሻው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው ነህ። በኢየሱስ ስም፥ ስለ ታማኝነትህና ስለ ቸርነትህ በደስታና በእልልታ ላመሰግንህ እመጣለሁ። ቃልህ «ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል» ይላል። ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ የእምነት ወንድሞቼንና እህቶቼን እንዲሁም የጎረቤቶቼን ፍላጎት እንዳስተውልና ርኅሩኅ እንድሆን እርዳኝ። የፍቅርህ ነጸብራቅ እንድሆን እርዳኝ፥ ይህ ልብህን የሚያስደስትና በፊትህ እንደ መልካም መባ ያለ ነውና። ያንተ የሆነውን ሁሉ ስለሰጠኸኝ፥ ያለኝን ሀብትና የእጄን ሥራ አቅርቤ ላመልክህና ላከብርህ ልቤን አዘጋጃለሁ። ዛሬ ራስ ወዳድነትን፥ እኔ ብቻ ማለትን፥ ስንፍናንና ንፉግነትን እተዋለሁ። አንተ ስለ እኛ ፍቅር ከሁሉ የተሻለውን ስለሰጠህ፥ እኔም ከሁሉ የተሻለውን እሰጥሃለሁ። መባዬን ተቀበል፥ እንደ መልካም መዓዛ ወደ አንተ ይውጣ። ቃልህ «በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ይሰበስባል፥ በብዙ የሚዘራ ግን በብዙ ይሰበስባል» ይላል። ጌታ ሆይ፥ እኔም የበረከት መተላለፊያ እንድሆንና በሌሎች ሕይወት እንድዘራ ፍቀድልኝ። ሕይወቴ ለአንተ ደስ የሚያሰኝ መባ እንዲሆን ለጋስና መስጠት የሚወድ ልብ ስጠኝ። ዋጋዬ ከሰማያት መንግሥት እንደሚመጣና ለችግረኛ የምሰጠው ሁሉ ለአንተ እንደሰጠሁት እንደሆነ ሁልጊዜ አምናለሁ። በኢየሱስ ስም። አሜን!
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች