እግዚአብሔር የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ ነው። ሰማይን፣ ምድርን፣ ዓለምንና በውስጧ ያለውን ሁሉ የፈጠረ እርሱ ነው። ዘጸአት 20:11 "እግዚአብሔር ሰማያትንና ምድርን፣ ባሕርንም በውስጡ ያለውንም ሁሉ በስድስት ቀን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር የሰንበትን ቀን ባረከው ቀደሰውም" ይላል። ሁሉን ፍጹም አድርጎ የፈጠረ እርሱ ስለፈጠረው ድንቅ ሥራ ሁሉ ምስጋና የሚገባው እርሱ ብቻ ነው። የፍርዱ ሰዓት እየቀረበ ስለሆነ እግዚአብሔርን ፍሩት ክብርንም ስጡት። ሰማይንና ምድርን፣ ባሕርንና የውኃ ምንጮችን የፈጠረውን አምልኩት። በተፈጥሮ ውበት፣ በባሕር ዳርቻዎች፣ በዛፎች፣ በተራሮች ሲደሰቱ ፈጣሪያችን ውብና ፍጹም አድርጎ እንደፈጠረው አስቡት። ለእግዚአብሔር ክብር መስጠት አይዘንጉ።
እግዚአብሔር፣ “ሰውን በመልካችን፣ በአምሳላችን እንሥራ፤ በባሕር ዓሦች፣ በሰማይ ወፎች፣ በከብቶች፣ በምድር ሁሉ ላይ፣ እንዲሁም በምድር ላይ በሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራቸው” አለ።
እስኪ የሰማይ ወፎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል። እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?
ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው። በዚያ ቀን አንተም ሆንህ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ አገልጋይህ ሆነ ሴት አገልጋይህ፣ ወይም እንስሳትህ፣ ወይም በደጅህ ያለ መጻተኛ ምንም ሥራ አትሠሩም።
ተኵላና የበግ ጠቦት በአንድነት ይበላሉ፤ አንበሳ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤ እባብ ትቢያ ይልሳል፤ በተቀደሰው ተራራዬም፣ ጕዳት አያደርሱም፤ ጥፋት አያመጡም፤” ይላል እግዚአብሔር።
አንተ ሰነፍ፤ ወደ ጕንዳን ሂድ፤ ዘዴውን አስተውለህ ጠቢብ ሁን፤ አዛዥ የለውም፤ አለቃም ሆነ ገዥ የለውም፤ ሆኖም ግን በበጋ ምግቡን ያከማቻል፤ በመከርም ወቅት ቀለቡን ይሰበስባል።
በዚያ ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች፣ በምድርም ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ጋራ፣ ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ፤ ሁሉም ያለ ሥጋት እንዲኖሩ፣ ቀስትን፣ ሰይፍንና ጦርነትን፣ ከምድሪቱ አስወግዳለሁ።
ታዲያ፣ እኔ ቀኝና ግራቸውን ለይተው መናገር የማይችሉ፣ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሰዎችና አያሌ እንስሳት ለሚኖሩባት ለታላቋ ከተማ ለነነዌ ማዘን አይገባኝምን?”
በመንገድ ስታልፍ፣ አንዲት ወፍ ጫጩቶቿን ወይም ዕንቍላሎቿን የታቀፈችበትን ጐጆ በዛፍ ወይም በመሬት ላይ ብታገኝ፣ እናቲቱን ከነጫጩቶቿ አትውሰድ፤ ጫጩቶቿን መውሰድ ትችላለህ፤ እናቲቱን ግን መልካም እንዲሆንልህና ዕድሜህም እንዲረዝም ልቀቃት።
ተኵላ ከበግ ጠቦት ጋራ ይኖራል፤ ነብርም ከፍየል ግልገል ጋራ ይተኛል፤ ጥጃ፣ የአንበሳ ደቦልና የሠባ ከብት በአንድነት ይሰማራሉ፤ ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።
ነገር ግን በሰባተኛው ዓመት ምድሪቱን ሳትጠቀምባትና ሳታርሳት እንዲሁ ተዋት፤ ከዚያም በወገንህ መካከል ያሉት ድኾች ከርሷ ምግብ ያገኛሉ፤ የዱር አራዊትም ከእነርሱ የተረፈውን ይበላሉ። በወይን ቦታህና በወይራ ዛፎችህም ላይ እንዲሁ አድርግ።
አንተ ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ነህና የሞተውን ሁሉ አትብላ፤ ከከተሞችህ በአንዲቱ ለሚኖር መጻተኛ ስጠው፤ ይብላውም፤ ለውጭ አገር ሰው ሽጠው። የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።
የዱር አራዊት ሁሉ፣ በሺሕ ተራሮች ላይ ያለውም እንስሳ የእኔ ነውና። በየተራራው ያለውን ወፍ ሁሉ ዐውቃለሁ፤ በሜዳ የሚገኘው ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ የእኔ ነው።
በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፤ በጎችንና ላሞችን ሁሉ፣ የዱር አራዊትንም፣ የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሦችን፣ በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትንም ሁሉ አስገዛህለት።
ቀርቦም ቍስሎቹ ላይ ዘይትና የወይን ጠጅ አፍስሶ አሰረለት፤ በራሱም አህያ ላይ አስቀምጦት ወደ እንግዶች ማረፊያ ቤት ወሰደው፤ በዚያም ተንከባከበው።
ስለ መሥዋዕትህ አልነቀፍሁህም፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህማ ሁልጊዜ በፊቴ ነው። እኔ ግን ኰርማህን ከበረት፣ ፍየሎችህንም ከጕረኖ የምፈልግ አይደለሁም፤
የሰው ዕድል ፈንታ እንደ እንስሳት ነው፤ ሁለቱም ዕጣ ፈንታቸው አንድ ነው፤ አንዱ እንደሚሞት፣ ሌላውም እንዲሁ ይሞታል። ሁሉ አንድ ዐይነት እስትንፋስ አላቸው፤ ሰውም ከእንስሳ ብልጫ የለውም፤ ሁሉም ከንቱ ነው።
ጕጕት በዚያ ጐጆ ሠርታ ዕንቍላል ትጥላለች፤ ትቀፈቅፋለች፤ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ትታቀፋቸዋለች፤ ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው፣ ለርቢ በዚያ ይሰበሰባሉ።
እርሱም፣ “ከእናንተ መካከል የአንዱ ሰው በግ በሰንበት ቀን ጕድጓድ ቢገባበት፣ በጉን ከገባበት ጕድጓድ ጐትቶ አያወጣውምን? ታዲያ ሰው ከበግ እጅግ አይበልጥምን? ስለዚህ በሰንበት ቀን በጎ ማድረግ ተፈቅዷል” አላቸው።
“አንድ ሰው ጕድጓድን ከፍቶ ቢተው፣ ወይም ጕድጓድ ቈፍሮ ሳይከድነው ቢቀርና በሬ ወይም አህያ ቢገባበት፣ የጕድጓዱ ባለቤት ኪሳራ ይክፈል፤ ለባለቤቱ መክፈል አለበት፤ የሞተውም እንስሳ ለርሱ ይሆናል።
በመልካሙ ስፍራ አሰማራቸዋለሁ፤ የእስራኤል ተራሮች ከፍታም የግጦሽ መሬት ይሆናቸዋል። በመልካሙ ግጦሽ መሬት ላይ ይተኛሉ፤ እዚያም በእስራኤል ተራሮች ለምለም መስክ ላይ ይመገባሉ።
እግዚአብሔር አምላክ የዱር አራዊትንና የሰማይ ወፎችን ከምድር ሠርቶ ነበር፤ ለእያንዳንዳቸውም ምን ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው። አዳም ሕይወት ላላቸው ፍጥረታት ሁሉ ያወጣላቸው ስም መጠሪያቸው ሆነ።
ቍራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ ማከማቻ ወይም ጐተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል። እናንተማ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?
እግዚአብሔርም፣ “ብዙ ተባዙ፤ ምድርን ሙሏት፤ ግዟትም፤ የባሕርን ዓሦች፣ የሰማይን ወፎች፣ እንዲሁም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ግዟቸው” ብሎ ባረካቸው።
አንተንና በወንዞችህ ያለውን ዓሣ ሁሉ፣ በምድረ በዳ እጥላለሁ። በገላጣ መሬት ላይ ትወድቃለህ፤ የሚሰበስብህ፣ የሚያነሣህም አይኖርም። ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች፣ ምግብ እንድትሆን አሳልፌ እሰጥሃለሁ።
ንጉሤና አምላኬ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ መሠዊያህ ባለበት ስፍራ፣ ድንቢጥ እንኳ መኖሪያ ቤት፣ ዋኖስም ጫጩቶቿን የምታኖርበት ጐጆ አገኘች።
እግዚአብሔር ኖኅንና በመርከቧ ውስጥ ከርሱ ጋራ የነበሩትን የዱርና የቤት እንስሳት ሁሉ ዐሰበ፤ በምድር ላይ ነፋስ እንዲነፍስ አደረገ፤ ውሃውም ጐደለ።
የእግዚአብሔርም መልአክ እንዲህ ሲል ጠየቀው፤ “አህያህን እንዲህ አድርገህ ሦስት ጊዜ የመታሃት ስለ ምንድን ነው? መንገድህ በፊቴ ጠማማ ስለ ሆነ ልቃወምህ መጥቻለሁ። አህያዪቱ አይታኝ ሦስቱንም ጊዜ ከፊቴ ዞር ባትልማ ኖሮ በእውነት እስካሁን አንተን በገደልሁህ፣ አህያዪቱን ግን በሕይወት በተውኋት ነበር።”
ከአንተ ጋራ በሕይወት እንዲቈዩ ከሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ተባዕትና እንስት እያደረግህ ሁለት ሁለቱን ወደ መርከቧ ታስገባለህ። የእግዚአብሔር ወንዶች ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች ውብ ሆነው አዩአቸው፤ ከመካከላቸውም የመረጧቸውን አገቡ። ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቈዩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይመጣሉ።
ሰማይን በደመናት የሚሸፍን እርሱ ነው፤ ለምድርም ዝናብን ይሰጣል፤ በተራሮችም ላይ ሣር ያበቅላል። ለእንስሳት ምግባቸውን፣ የቍራ ጫጩቶችም ሲንጫጩ የሚበሉትን ይሰጣቸዋል።
“እስራኤላውያንን እንዲህ በሏቸው፤ ‘በየብስ ከሚኖሩ እንስሳት ሁሉ የምትበሏቸው እነዚህ ናቸው፦ “ ‘ክንፍ ኖሯቸው በአራት እግር የሚንቀሳቀሱ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ አስጸያፊዎች ይሁኑ። ነገር ግን ክንፍ ኖሯቸው በአራት እግር ከሚንቀሳቀሱ ነፍሳት መካከል ከምድር በሚፈናጠሩበት እግራቸው አንጓ ያለባቸውን መብላት ትችላላችሁ። ከእነዚህ ማንኛውንም ዐይነት አንበጣ፣ ፌንጣና ኵብኵባ መብላት ትችላላችሁ። ነገር ግን ክንፍ ኖሯቸው በአራት እግር የሚንቀሳቀሱትን ፍጥረታት ተጸየፏቸው። “ ‘ከእነዚህ የተነሣ ትረክሳላችሁ፤ የእነዚህን በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። የእነዚህንም በድን የሚያነሣ ሰው ሁሉ ልብሱን ይጠብ፤ ሆኖም እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው። “ ‘ሰኰና ያለው፣ ነገር ግን ሰኰናው ያልተሰነጠቀና የማያመሰኳ ማንኛውም እንስሳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን። የእነዚህንም በድን የሚነካ ሰው ሁሉ ይረክሳል። አራት እግር ካላቸው እንስሳት ሁሉ በመዳፋቸው የሚሄዱት በእናንተ ዘንድ ርኩሳን ናቸው፤ በድናቸውንም የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። የእነዚህን በድን የሚያነሣ ሰው ልብሱን ይጠብ፤ ሆኖም እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እንስሳቱም በእናንተ ዘንድ ርኩሳን ናቸው። “ ‘ምድር ለምድር ከሚንቀሳቀሱ እንስሳት መካከል እነዚህ በእናንተ ዘንድ ርኩሳን ናቸው፦ ሙጭልጭላ፣ ዐይጥ፣ እንሽላሊት በየወገኑ፣ ሰኰናው የተሰነጠቀውን የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ መብላት ትችላላችሁ።
“በምድር ላይ አራት ነገሮች ትንንሽ ናቸው፤ ሆኖም እጅግ ጠቢባን ናቸው፤ ጕንዳኖች ደካማ ፍጥረታት ናቸው፤ ሆኖም ምግባቸውን በበጋ ያከማቻሉ።
ከንጹሕ እንስሳት ሁሉ ሰባት ሰባት ተባዕትና እንስት፣ ንጹሕ ካልሆኑት እንስሳት ደግሞ ሁለት ሁለት ተባዕትና እንስት ውሰድ፤ ውሃው ከተራሮቹ ጫፍ በላይ 7 ሜትር ያህል ከፍ አለ። በምድር ላይ የነበሩ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ፦ ወፎች፣ የቤት እንሰሳት፣ የዱር እንስሳት በምድር የሚርመሰመሱ ፍጥረታት፣ ሰዎችም በሙሉ ጠፉ። በአፍንጫቸው የሕይወት እስትንፋስ ያላቸው በየብስ የነበሩ ፍጥረታት ሁሉ ሞቱ። ሕይወት ያላቸው ፍጥረታት ሁሉ ከምድር ገጽ ጠፉ፤ ሰዎችና እንስሳት በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትና የሰማይ ወፎች ከምድር ላይ ጠፉ፤ ኖኅና ከርሱ ጋራ በመርከቧ ውስጥ የነበሩት ብቻ ተረፉ። ውሃውም ምድርን ሸፍኖ መቶ ዐምሳ ቀን ቈየ። እንዲሁም ከወፎች ወገን ሁሉ ሰባት ተባዕትና ሰባት እንስት፣ በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፉ ከአንተ ጋራ ታስገባለህ።
የእናቱን ማሕፀን የሚከፍተውን ሁሉ ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ፤ እንደዚሁም እንስሶቻችሁ በመጀመሪያ የወለዷቸው ወንዶች ሁሉ ለእግዚአብሔር ይሆናሉ።
ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው። በዚያ ቀን አንተም ሆንህ ወንድ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ አገልጋይህም ሆነ ሴት አገልጋይህ በሬህ፣ አህያህ ወይም ማንኛውም እንስሳህ ወይም ደግሞ በደጅህ ያለ እንግዳ ምንም ዐይነት ሥራ አትሥሩ። ይህም አንተ እንዳረፍህ ሁሉ ወንድ አገልጋይህም ሆነ ሴት አገልጋይህ እንዲያርፉ ነው።
በሐሳብህ ስፍራ ትሰጠው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ትጠነቀቅለትም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድን ነው? ከመላእክት በጥቂት አሳነስኸው፤ ክብርንና ግርማን አጐናጸፍኸው። በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፤ በጎችንና ላሞችን ሁሉ፣ የዱር አራዊትንም፣ የሰማይ ወፎችንና የባሕር ዓሦችን፣ በባሕር ውስጥ የሚርመሰመሱትንም ሁሉ አስገዛህለት።
ሕያውና ተንቀሳቃሽ ፍጡር ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ፤ ለምለሙን ዕፀዋት እንደ ሰጠኋችሁ፣ አሁን ደግሞ ሁሉን ሰጠኋችሁ። “ነገር ግን ሕይወቱ፣ ማለት ደሙ ገና በውስጡ ያለበትን ሥጋ አትብሉ።
“ለፈረስ ጕልበትን ትሰጠዋለህን? ዐንገቱንስ ጋማ ታለብሰዋለህን? የእርግዝናቸው ወራት ምን ያህል እንደ ሆነ ትቈጥራለህን? የሚወልዱበትንስ ጊዜ ታውቃለህን? እንደ አንበጣ የምታስዘልለው አንተ ነህን? የማንኰራፋቱም ገናናነት አስፈሪ ነው። በጕልበቱ እየተመካ በብርቱ ይጐደፍራል፤ ጦርነት ሊገጥም ይወጣል። ያለ አንዳች ሥጋት፣ በፍርሀት ላይ ይሥቃል፤ ሰይፍ ቢመዘዝበትም ወደ ኋላ አይልም። ከሚብረቀረቀው ጦርና ዐንካሴ ጋራ፣ የፍላጻው ኰረጆ ጐኑ ላይ ይንኳኳል። በወኔ መሬቱን እየጐደፈረ ወደ ፊት ይሸመጥጣል፤ የመለከት ድምፅ ሲሰማ ያቅበጠብጠዋል። መለከቱ ሲያንባርቅ፣ ‘ዕሠይ’ ይላል፤ የአዛዦችን ጩኸትና የሰራዊቱን ውካታ፣ ጦርነትንም ከሩቅ ያሸትታል።
“ ‘ሥርዐቴን ጠብቁ። “ ‘የተለያዩ እንስሳትን አታዳቅል። “ ‘በዕርሻህ ላይ ሁለት ዐይነት ዘር አትዝራ። “ ‘ከሁለት ዐይነት ነገር የተሠራ ልብስ አትልበስ።
“አረማመዳቸው ግርማዊ የሆነ ሦስት ነገሮች አሉ፤ እንዲያውም በሞገስ የሚጐማለሉ አራት ናቸው፤ ጥበብን አልተማርሁም፤ ስለ ቅዱሱም ዕውቀት የለኝም። ከአራዊት መካከል ኀይለኛ የሆነው፣ ከምንም ነገር ፊት ግንባሩን የማያጥፈው አንበሳ፤ ጐርደድ ጐርደድ የሚል አውራ ዶሮ፣ አውራ ፍየል፣ እንዲሁም በሰራዊቱ የታጀበ ንጉሥ ናቸው።
እግዚአብሔር፣ “ምድር ሕያዋን ፍጥረታትን እንደየወገናቸው፣ ከብቶችን፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ፍጥረታትንና የዱር እንስሳትን እያንዳንዱን እንደ ወገኑ ታስገኝ” አለ፤ እንዳለውም ሆነ።
የማንኛውም ፍጡር ሕይወት ደሙ ነውና። ስለዚህ እስራኤላውያንን፣ “የፍጡር ሁሉ ሕይወት ደሙ ነውና የማንኛውንም ፍጡር ደም አትብሉ፤ የበላው ሰው ሁሉ ተለይቶ ይጥፋ” አልኋቸው።
ነገር ግን ወይፈን የሚሠዋልኝ፣ ሰው እንደሚገድል ነው፤ የበግ ጠቦት የሚያቀርብልኝ፣ የውሻ ዐንገት እንደሚሰብር ሰው ነው፤ የእህል ቍርባን የሚያዘጋጅልኝ፣ የዕሪያ ደም እንደሚያቀርብልኝ ሰው ነው፤ የመታሰቢያን ዕጣን የሚያጥንልኝም፣ ጣዖትን እንደሚያመልክ ሰው ነው፤ የገዛ መንገዳቸውን መርጠዋል፤ ነፍሳቸውም በርኩሰታቸው ደስ ይላታል።
ከምድር ምግብን ታወጣ ዘንድ፣ ለእንስሳት ሣርን፣ ለሰው ልጆች ሥራ ዕፀዋትን ታበቅላለህ፤ የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ ወይን፣ ፊቱን የሚያወዛ ዘይት፣ ልቡን የሚያበረታ እህል በዚህ ይገኛል።
“ሰጎን ክንፎቿን በደስታ ታራግባለች፤ ነገር ግን እንደ ሽመላ ላባዎች ሊሆኑ አይችሉም። ዕንቍላሏን መሬት ላይ ትጥላለች፤ እንዲሞቅም በአሸዋ ውስጥ ትተወዋለች። እግር እንደሚሰብረው፤ የዱር አውሬም እንደሚረግጠው አታስብም። የእርሷ እንዳልሆኑ ሁሉ በልጆቿ ትጨክናለች፤ ድካሟም በከንቱ ቢቀር ደንታ የላትም፤ እግዚአብሔር ጥበብ ነሥቷታልና፤ ማስተዋልንም አልሰጣትም። ለመሸምጠጥም ክንፎቿን ስትዘረጋ፣ በፈረስና በጋላቢው ትሥቃለች።
ወደ ሸለቆ እንደሚወርድ የከብት መንጋ፣ በእግዚአብሔር መንፈስ ዕረፍት ተሰጣቸው። ሕዝብህን በዚህ ሁኔታ የመራሃቸው፣ ስምህን የከበረ ለማድረግ ነው።