Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


ስለ በረከት

ስለ በረከት

የእግዚአብሔር በረከት በሕይወታችን ላይ ሁልጊዜ በብዛትና በተገቢው ጊዜ ይመጣል፤ ፈጽሞ አይዘገይም። እግዚአብሔር በጸሎት ለምንከለክለው በረከት የሚመጣበትን ትክክለኛ ጊዜ ያውቃል። በእግዚአብሔር ውብ በረከት የተከበብን ነን፤ ጤና አለን፣ መጠለያ አለን፣ ምግብ አለን፣ የአእምሮ ጤና አለን፣ የሚወዱን ሰዎች አሉን ከሁሉም በላይ ደግሞ እግዚአብሔር በሕይወታችን አለ፤ እጅግ ድንቅ የሆነውን የመዳን ስጦታ አግኝተናል። እነዚህ አንዳንዴ የማናስተውላቸው ነገር ግን ለብዙ ሰዎች የጎደሉ በረከቶች ናቸው። ለእነዚህ ነገሮች አመስጋኝ ልንሆንና በየማለዳው የሚታደሰው የእግዚአብሔር ምሕረት ሊያስደስተን ይገባል። እግዚአብሔርም በክርስቶስ ኢየሱስ ክብር ሁሉንም ጉድለታችንን ይሞላልና። እግዚአብሔር በቃሉ የሚነግረን ከእርሱ የሚመጣው በረከት እንደሚያበለጽግና ኀዘን እንደማይጨምር ነው። እግዚአብሔር የሚያስፈልገንን ያውቃል፤ ያስብልናልም። ታጋሽ እንሁን፤ በረከቱ የማንጠብቀው ጊዜ ይመጣል። እግዚአብሔር አምላክህን አምልክ፤ እርሱም እንጀራህንና ውኃህን ይባርካል። ደዌንም ሁሉ ከአንተ አርቃለሁ (ዘጸ. ፳፫፥፳፭)። ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ኑር፤ በረከቱም ከእሱ ጋር ይመጣል።


ማቴዎስ 9:37-38

ደቀ መዛሙርቱንም እንዲህ አላቸው፤ “መከሩ ብዙ ነው፤ ሠራተኞቹ ግን ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህ የመከሩ ጌታ፣ ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንዲልክ ለምኑት።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 9:10

ለዘሪ ዘርን፣ ለመብላት እንጀራን የሚሰጥ እርሱ የምትዘሩትን አትረፍርፎ ይሰጣችኋል፤ የጽድቃችሁንም ፍሬ ያበዛላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 9:37

ደቀ መዛሙርቱንም እንዲህ አላቸው፤ “መከሩ ብዙ ነው፤ ሠራተኞቹ ግን ጥቂቶች ናቸው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 4:35

እናንተ፣ ‘ከአራት ወር በኋላ መከር ይደርሳል’ ትሉ የለምን? እነሆ፣ አዝመራው ለመከር እንደ ደረሰ ቀና ብላችሁ ማሳውን ተመልከቱ እላችኋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 9:6

ይህን አስታውሱ፤ ጥቂት የዘራ ጥቂት ያጭዳል፤ ብዙ የዘራ ብዙ ያጭዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 67:6

ምድር ፍሬዋን ሰጠች፤ እግዚአብሔር፣ አምላካችን ይባርከናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 10:5

ሰብሉን በበጋ የሚሰበስብ ጠቢብ ልጅ ነው፤ በመከር ጊዜ የሚተኛ ግን ውርደት ይከተለዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 107:37

በዕርሻውም ዘሩበት፤ ወይንም ተከሉ፤ ብዙ ፍሬም አመረቱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 85:12

እግዚአብሔር በጎ ነገር ይለግሳል፤ ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 10:2

እንዲህም አላቸው፤ “መከሩ ብዙ ነው፤ ሠራተኞቹ ግን ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህ የመከሩ ጌታ ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንዲልክ ለምኑት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 126:5-6

በእንባ የሚዘሩ፣ በእልልታ ያጭዳሉ። ዘር ቋጥረው፣ እያለቀሱ የተሰማሩ፣ ነዷቸውን ተሸክመው፣ እልል እያሉ ይመለሳሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዩኤል 1:11

እናንተ ገበሬዎች፣ ዕዘኑ፤ እናንተ የወይን ገበሬዎች፣ ዋይ በሉ፤ ስለ ገብሱና ስለ ስንዴው አልቅሱ፤ የዕርሻው መከር ጠፍቷልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 26:3-4

“ ‘በሥርዐቴ ብትሄዱ፣ ትእዛዜንም በጥንቃቄ ብትጠብቁ፣ የኰረብታ መስገጃዎቻችሁን እደመስሳለሁ፤ የዕጣን መሠዊያዎቻችሁን አፈርሳለሁ፤ በድኖቻችሁን በድን በሆኑት ጣዖቶቻችሁ ላይ እጥላለሁ፤ ነፍሴም ትጸየፋችኋለች። ከተሞቻችሁን አፈራርሳለሁ፤ መቅደሶቻችሁንም ወና አደርጋለሁ፤ ጣፋጭ ሽታ ያለውን መሥዋዕታችሁንም አልቀበልም። በዚያ የሚኖሩ ጠላቶቻችሁ እስኪደነቁ ድረስ፣ ምድሪቱን ባድማ አደርጋታለሁ። በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ ሰይፌን መዝዤም አሳድዳችኋለሁ። ምድራችሁ ባድማ፣ ከተሞቻችሁም ፍርስራሽ ይሆናሉ። ምድሪቱ ባድማ በሆነችበት ጊዜ ሁሉና እናንተም በጠላቶቻችሁ ምድር በምትኖሩበት ወቅት ምድሪቱ በሰንበት ዓመቷ ትደሰታለች፤ ምድሪቱም በሰንበቷ ታርፋለች፤ ትደሰታለችም። ምድሪቱ እናንተ በነበራችሁባት ጊዜ በሰንበት ያላገኘችውን ዕረፍት፣ ባድማ በምትሆንበት ጊዜ ሁሉ ታገኛለች። “ ‘ከእናንተ በሕይወት የተረፉትን፣ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ ድንጋጤ እሰድድባቸዋለሁ፤ ነፋስ የሚያንቀሳቅሰው የቅጠል ድምፅ ያስበረግጋቸዋል፤ የሚያሳድዳቸውም ሳይኖር ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሮጣሉ፤ ይወድቃሉም። የሚያሳድዳቸው ሳይኖር ከሰይፍ እንደሚሸሹ እርስ በርሳቸው ይሰነካከላሉ፤ በጠላቶቻችሁም ፊት መቆም አትችሉም። በአሕዛብ መካከል ታልቃላችሁ፤ የጠላቶቻችሁም ምድር ትውጣችኋለች። ከእናንተ የተረፉት በጠላቶቻቸው ምድር በራሳቸው ኀጢአትና በአባቶቻቸው ኀጢአት ምክንያት መንምነው ያልቃሉ። ዝናብን በወቅቱ እሰጣችኋለሁ፤ ምድሪቱ እህሏን፣ የሜዳ ዛፎችም ፍሬአቸውን ይሰጣሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 5:5

ከእሾኽ መካከል እንኳ አውጥቶ፣ ራብተኛ ሰብሉን ይበላበታል፤ ጥማተኛም ሀብቱን ይመኝበታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 15:5

“እኔ የወይን ተክል ነኝ፤ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ማንም በእኔ ቢኖር እኔም በርሱ ብኖር፣ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል፤ ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:9

በጎ ነገር ከማድረግ አንታክት፤ ተስፋ ካልቈረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 62:8-9

እግዚአብሔር በቀኝ እጁ፣ በኀያል ክንዱም እንዲህ ሲል ምሏል፤ “ከእንግዲህ እህልሽን፣ ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤ ከእንግዲህ የደከምሽበትን፣ አዲስ የወይን ጠጅ ባዕዳን አይጠጡትም። ነገር ግን መከሩን የሰበሰቡ ይበሉታል፤ እግዚአብሔርንም ያመሰግናሉ፤ የወይኑን ፍሬ የለቀሙም በመቅደሴ አደባባዮች ይጠጡታል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 5:24

በልባቸውም፣ ‘የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ በጊዜው የሚያዘንበውን፣ መከርን በወቅቱ የሚያመጣልንን፣ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንፍራ’ አላሉም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:39

ዘርቶት የሄደው ጠላትም ዲያብሎስ ነው፤ መከሩ የዓለም መጨረሻ ሲሆን፣ ዐጫጆቹም መላእክት ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሆሴዕ 10:12

ለራሳችሁ ጽድቅን ዝሩ፤ የጽኑ ፍቅርን ፍሬ ዕጨዱ፤ ዕዳሪውንም መሬት ዕረሱ፤ እርሱም መጥቶ፣ ጽድቅን በላያችሁ እስኪያዘንብ ድረስ፣ እግዚአብሔርን የምትፈልጉበት ጊዜ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 25:4-5

በሰባተኛው ዓመት ግን ምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት ታድርግ፤ ይህም የእግዚአብሔር ሰንበት ነው። በዕርሻህ ላይ አትዝራ፤ ወይንህንም አትግረዝ። በመካከልህ እንዳለ ቅጥር ሠራተኛ ወይም እንደ እንግዳ አድርገህ ቍጠረው፤ እስከ ኢዮቤልዩ ዓመትም ይሥራልህ፤ ከዚያም በኋላ እርሱና ልጆቹ በነጻ ይለቀቁ፤ ወደ ቤተ ሰቡና ወደ አባቶቹ ንብረት ይመለስ። እስራኤላውያን ከግብጽ ያወጣኋቸው አገልጋዮቼ ስለ ሆኑ እንደ ባሪያ አይሸጡ። በጭካኔ አትግዛቸው፤ ነገር ግን አምላክህን ፍራ። “ ‘የሚኖሩህ ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችህ፣ በዙሪያህ ካሉት አሕዛብ መካከል የገዛሃቸው ባሪያዎች ይሁኑ። እንደዚሁም በመካከላችሁ ከሚኖሩት መጻተኞችና ከተወለዱት ወገናቸው ባሪያዎችን ግዙ፤ ንብረታችሁም ይሁኑ። እነርሱንም እንደ ንብረት ለልጆቻችሁ አውርሷቸው፤ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ ባሪያዎች ይሁኗችሁ፤ እስራኤላውያን ወገኖቻችሁን ግን በጭካኔ አትግዟቸው። “ ‘በመካከላችሁ የሚኖር መጻተኛ ወይም እንግዳ ሀብታም ቢሆንና ከወገናችሁ አንዱ ደኽይቶ በመካከላችሁ ለሚኖር መጻተኛ ወይም ከመጻተኛው ወገን ለአንዱ ራሱን ቢሸጥ፣ ከተሸጠ በኋላ ሊዋጅ ይችላል። ከዘመዶቹም አንዱ፣ አጎቱ ወይም የአጎቱ ልጅ ወይም ከወገኖቹ ማንኛውም የሥጋ ዘመዱ ይዋጀው፤ ሀብት ካገኘም ራሱን መዋጀት ይችላል። ሳይዘራ የበቀለውን አትጨደው፤ ካልተገረዘው የወይን ተክልህ ፍሬ አትሰብስብ። ምድሪቱ የአንድ ዓመት ዕረፍት ታድርግ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘኍል 18:12-13

“እስራኤላውያን የመከር በኵራት አድርገው ለእግዚአብሔር የሚሰጡትን ምርጥ የወይራ ዘይት በሙሉ፣ ምርጥ የሆነውን አዲስ የወይን ጠጅና እህል ሁሉ ለእናንተ ሰጥቻችኋለሁ። ለእግዚአብሔር የሚያመጡት የምድሪቱ በኵር ፍሬ ሁሉ የአንተ ይሆናል። ከቤተ ሰዎችህ በሥርዐቱ መሠረት ንጹሕ የሆነ ማንኛውም ሰው ይህን መብላት ይችላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 23:16

“በማሳህ ላይ በዘራኸው እህል በኵራት የመከርን በዓል አክብር። “በዓመቱ መጨረሻ በማሳህ ላይ ያለውን እህልህን ስትሰበስብ የመክተቻውን በዓል አክብር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 24:19

የዕርሻህን ሰብል በምታጭድበት ጊዜ፣ ተረስቶ የቀረ ነዶ ቢኖር፣ ያን ለመውሰድ ተመልሰህ አትሂድ። አምላክህ እግዚአብሔር በእጅህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነዶውን ለመጻተኛው፣ አባት ለሌለውና ለመበለቲቱ ተወው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 34:22

“የሰባቱን ሱባዔ የመከር በዓል ከስንዴው መከር በኵራት ጋራ፣ እንዲሁም የመክተቻ በዓልን በዓመቱ መጨረሻ ላይ አክብር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 4:29

ፍሬው እንደ በሰለም መከር በመድረሱ፣ ሰውየው ወዲያው ማጭዱን አንሥቶ ዐጨዳ ይጀምራል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 9:3

ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፣ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፣ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 22:8

ክፋትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፤ የቍጣውም በትር ይጠፋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዩኤል 3:13

ማጭዱን ስደዱ፤ መከሩ ደርሷልና፤ ኑ ወይኑን ርገጡ፤ የወይን መጭመቂያው ሞልቶ፣ ከጕድጓዶቹም ተርፎ ፈስሷልና፤ ክፋታቸው እንደዚህ ታላቅ ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 8:22

“ምድር እስካለች ድረስ፣ የዘር ወቅትና መከር፣ ሙቀትና ቅዝቃዜ በጋና ክረምት፣ ቀንና ሌሊት፣ አይቋረጡም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 25:13

በመከር ጊዜ የበረዶ ቅዝቃዜ ለሰስ እንደሚያደርግ ሁሉ፣ ታማኝ መልእክተኛም ለላኩት እንደዚሁ ነው፤ የጌቶቹን መንፈስ ያሳርፋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሆሴዕ 6:11

“ይሁዳ ሆይ፤ ለአንተም፣ መከር ተመድቦብሃል። “ሕዝቤን ከምርኮ አገር በመለስሁ ጊዜ፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:30

ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ ዐብረው ይደጉ። በዚያ ጊዜ ዐጫጆቹን እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ንቀሉ፤ በእሳትም እንዲቃጠል በየነዶው እሰሩት፤ ስንዴውን ግን ሰብስባችሁ በጐተራዬ ክተቱ እላቸዋለሁ’ አላቸው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ራእይ 14:15

ሌላም መልአክ ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው፣ “የዐጨዳው ሰዓት ስለ ደረሰ፣ ማጭድህን ይዘህ ዕጨድ፤ የምድር መከር ደርሷልና” ሲል በታላቅ ድምፅ ጮኸ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 3:18

የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉ በሰላም ይዘራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 34:21-22

“ስድስት ቀን ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ዕረፍ፤ በዕርሻና በመከር ወቅት እንኳ ቢሆን ማረፍ አለብህ። “የሰባቱን ሱባዔ የመከር በዓል ከስንዴው መከር በኵራት ጋራ፣ እንዲሁም የመክተቻ በዓልን በዓመቱ መጨረሻ ላይ አክብር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 8:20

“መከሩ ዐለፈ፤ በጋው አበቃ፤ እኛም አልዳንም።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:18

ክፉ ሰው የሚያገኘው ትርፍ መቅኖ የለውም፤ ጽድቅን የሚዘራ ግን አስተማማኝ ዋጋ ያገኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 17:11

በተከልህበት ቀን እንዲበቅል፣ በዘራህበትም ማግስት እንዲያብብ ብታደርግ እንኳ፣ መከሩ በደዌና በማይሽር ሕመም ቀን፣ እንዳልነበረ ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:8

ሌላውም ዘር ደግሞ በጥሩ መሬት ላይ ወደቀ፤ ፍሬም አፈራ፤ አንዱ መቶ፣ አንዱ ስድሳ፣ አንዱም ሠላሳ ፍሬ ሰጠ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 15:16

እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ፣ ፍሬያችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ። ስለዚህም አብ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 16:15

እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በዓሉን ሰባት ቀን አክብር፤ አምላክህ እግዚአብሔር በእህል ምርትህና በእጅህ ሥራ ሁሉ ይባርክሃል፤ ደስታህም ፍጹም ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 5:7

እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ጌታ እስከሚመጣ ድረስ ታገሡ። ገበሬ መሬቱ መልካምን ፍሬ እስከሚሰጥ ድረስ እንዴት እንደሚታገሥ፣ የፊተኛውንና የኋለኛውን ዝናብ እንዴት እንደሚጠባበቅ አስተውሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 3:6-8

እኔ ተከልሁ፤ አጵሎስ ውሃ አጠጣ፤ ያሳደገው ግን እግዚአብሔር ነው። ስለዚህ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ፣ የሚተክልም ሆነ ውሃ የሚያጠጣ ምንም አይደለም። የሚተክልም ሆነ የሚያጠጣ አንድ ናቸው፤ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን የራሱን ሽልማት ይቀበላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:23

በጥሩ መሬት ላይ የተዘራው ዘር ግን ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውለውን ሰው ይመስላል፤ በርግጥም ፍሬ ያፈራል፤ አንዱ መቶ፣ አንዱ ስድሳ፣ አንዱም ሠላሳ ፍሬ ሰጠ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 2:6

ትጉህ ገበሬም ከሰብሉ ለመጠቀም የመጀመሪያው ሊሆን ይገባዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:17

እንዲሁም ጥሩ ዛፍ ሁሉ ጥሩ ፍሬ፣ መጥፎ ዛፍ ግን መጥፎ ፍሬ ያፈራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 8:15

በመልካም መሬት ላይ የወደቀውም ቃሉን ቅንና በጎ በሆነ ልብ ሰምተው የሚጠብቁ፣ ታግሠውም በመጽናት ፍሬ የሚያፈሩ ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፍጥረት 26:12

ይሥሐቅም በዚያች ምድር ዘር ዘራ፣ እግዚአብሔርም ባረከለትና በዚያ ዓመት መቶ ዕጥፍ አመረተ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 55:10-11

ዝናምና በረዶ ከሰማይ ወርዶ፣ ምድርን በማራስ፣ እንድታበቅልና እንድታፈራ ለዘሪው ዘር፣ ለበላተኛም እንጀራ እንድትሰጥ ሳያደርግ፣ ወደ ላይ እንደማይመለስ ሁሉ፣ ከአፌ የሚወጣውም ቃሌ፣ በከንቱ ወደ እኔ አይመለስም፤ ነገር ግን የምሻውን ያከናውናል፤ የተላከበትንም ዐላማ ይፈጽማል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 31:5

እንደ ገናም በሰማርያ ኰረብቶች ላይ፣ ወይን ትተክያለሽ፤ አትክልተኞች ይተክሏቸዋል፤ በፍሬውም ደስ ይላቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
አሞጽ 9:13

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ዐጫጁ ዐጭዶ ሳይጨርስ፣ ዐራሹ በላዩ የሚደርስበት፣ ችግኝ ተካዩም ገና ተክሎ ሳይጨርስ፣ ወይን ጨማቂው የሚደርስበት ጊዜ ይመጣል፤ አዲስ የወይን ጠጅ ከተራሮች ይንጠባጠባል፤ ከኰረብቶችም ሁሉ ይፈስሳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 7:13

ይወድድሃል፤ ይባርክሃል፤ ያበዛሃልም። ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር የማሕፀንህን ፍሬ፣ የምድርህን ሰብል፣ እህልህን፣ አዲሱን ወይንና ዘይት፤ የከብት መንጋህን ጥጆች፣ የበግና የፍየል መንጋህን ግልገሎች ይባርካል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 12:24

ቍራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ ማከማቻ ወይም ጐተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል። እናንተማ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 4:8

ሌላውም ዘር ደግሞ በመልካም መሬት ላይ ስለ ወደቀ በቅሎ አደገ፤ ፍሬም ሰጠ፤ አንዱ ሠላሳ፣ አንዱ ስድሳ፣ ሌላውም መቶ ፍሬ አፈራ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:24-30

ኢየሱስም ሌላ ምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፤ “መንግሥተ ሰማይ በዕርሻው ቦታ ጥሩ ዘር የዘራን ሰው ትመስላለች። ነገር ግን ሰው ሁሉ ተኝቶ ሳለ፣ ጠላቱ መጥቶ በስንዴው መካከል እንክርዳድ ዘርቶ ሄደ። ስንዴው በቅሎ ማፍራት ሲጀምር እንክርዳዱም ዐብሮ ብቅ አለ። “የዕርሻው ባለቤት ባሪያዎችም ወደ እርሱ ቀርበው፣ ‘ጌታ ሆይ፤ በዕርሻህ ቦታ ጥሩ ዘር ዘርተህ አልነበረምን? እንክርዳዱ ከየት መጣ?’ አሉት። “እርሱም፣ ‘የጠላት ሥራ ነው’ አላቸው። “ባሮቹም፣ ‘እንክርዳዱን ሄደን እንድንነቅለው ትፈልጋለህ?’ ብለው ጠየቁት። “እርሱ ግን፣ ‘አይሆንም፤ ምክንያቱም እንክርዳዱን እንነቅላለን ስትሉ ስንዴውንም ዐብራችሁ ልትነቅሉ ትችላላችሁ፤ ብዙ ነገሮችን በምሳሌ እንዲህ ሲል ነገራቸው፤ “አንድ ገበሬ ዘር ሊዘራ ወጣ። ተዉአቸው፤ እስከ መከር ጊዜ ዐብረው ይደጉ። በዚያ ጊዜ ዐጫጆቹን እንክርዳዱን አስቀድማችሁ ንቀሉ፤ በእሳትም እንዲቃጠል በየነዶው እሰሩት፤ ስንዴውን ግን ሰብስባችሁ በጐተራዬ ክተቱ እላቸዋለሁ’ አላቸው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 6:38

ስጡ፤ ይሰጣችኋል፤ በምትሰፍሩበት መስፈሪያ ተመልሶ ስለሚሰፈርላችሁ፣ ጫን በተደረገ፣ በተነቀነቀና በተትረፈረፈ መልካም መስፈሪያ ተሰፍሮ በዕቅፋችሁ ይሰጣችኋል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 32:20

በየወንዙ ዳር ዘር የምትዘሩ፣ በሬዎቻችሁንና አህዮቻችሁን በነጻነት የምታሰማሩ፣ ምንኛ ብፁዓን ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚክያስ 6:15

ትዘራለህ፤ ነገር ግን አታጭድም፤ የወይራ ዘይት ትጨምቃለህ፤ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፤ ወይንን ትቈርጣለህ፤ ነገር ግን የወይን ጠጅ አትጠጣም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዩኤል 2:23-24

የጽዮን ሰዎች ሆይ፤ ደስ ይበላችሁ፤ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ሐሤት አድርጉ፤ የበልግን ዝናብ፣ በጽድቅ ሰጥቷችኋልና፤ እንደ ቀድሞውም፣ የበልግንና የጸደይን ዝናብ በብዛት ልኮላችኋል። ዐውድማዎቹ በእህል ይሞላሉ፤ መጥመቂያ ጕድጓዶችም በአዲስ የወይን ጠጅና በዘይት ተሞልተው ያፈስሳሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 12:11

መሬቱን የሚያርስ የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል፤ ከንቱ ተስፋን የሚያሳድድ ግን ልበ ቢስ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 9:36-38

ሕዝቡም እረኛ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀውና ተመልካች የለሽ ሆነው ባየ ጊዜ ዐዘነላቸው። ደቀ መዛሙርቱንም እንዲህ አላቸው፤ “መከሩ ብዙ ነው፤ ሠራተኞቹ ግን ጥቂቶች ናቸው፤ ስለዚህ የመከሩ ጌታ፣ ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንዲልክ ለምኑት።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:8

ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 20:4

ሰነፍ ሰው በወቅቱ አያርስም፤ ስለዚህ በመከር ወራት ይፈልጋል፤ አንዳችም አያገኝም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 3:12

መንሹ በእጁ ነው፤ ዐውድማውን ፈጽሞ ያጠራል፤ ስንዴውን በጐተራ ይከትታል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 27:12

በዚያ ቀን ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝ፣ እግዚአብሔር እህሉን ይወቃል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፤ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 12:24

እውነት እላችኋለሁ፤ የስንዴ ቅንጣት መሬት ላይ ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 23:10-11

“ስድስት ዓመት በዕርሻህ ላይ ዝራ፤ አዝመራንም ሰብስብ፤ ነገር ግን በሰባተኛው ዓመት ምድሪቱን ሳትጠቀምባትና ሳታርሳት እንዲሁ ተዋት፤ ከዚያም በወገንህ መካከል ያሉት ድኾች ከርሷ ምግብ ያገኛሉ፤ የዱር አራዊትም ከእነርሱ የተረፈውን ይበላሉ። በወይን ቦታህና በወይራ ዛፎችህም ላይ እንዲሁ አድርግ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 14:4

በሬዎች በሌሉበት በረቱ ባዶ ይሆናል፤ በበሬ ጕልበት ግን ብዙ ምርት ይገኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:49

በዓለም መጨረሻም ልክ እንደዚሁ ይሆናል፤ መላእክት መጥተው ኀጢአተኞችን ከጻድቃን በመለየት፣

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጢሞቴዎስ 5:18

መጽሐፍም፣ “እህል እያበራየ ያለውን በሬ አፉን አትሰር፤” ደግሞም፣ “ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል” ይላልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 13:6-9

ደግሞም እንዲህ ሲል ይህን ምሳሌ ተናገረ፤ “አንድ ሰው በወይኑ ዕርሻ ቦታ የተተከለች አንዲት የበለስ ተክል ነበረችው፤ እርሱም ፍሬ ሊፈልግባት መጥቶ ምንም አላገኘም። የወይን አትክልት ሠራተኛውንም፣ ‘እነሆ፤ ፍሬ ለማግኘት ልፈልግባት ሦስት ዓመት ወደዚህች በለስ መጥቼ ምንም አላገኘሁም፤ ስለዚህ ቍረጣት፤ ለምን ዐፈሩን በከንቱ ታሟጥጣለች?’ አለው። “እርሱ ግን እንዲህ ሲል መለሰለት፤ ‘ጌታ ሆይ፤ ዙሪያዋን እስክኰተኵትላትና ፍግ እስከማደርግላት ድረስ ለዘንድሮ ብቻ ተዋት፤ ለከርሞ ካፈራች መልካም ነው፤ አለዚያ ትቈርጣታለህ።’ ”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 5:1-2

ስለ ወዳጄ፣ ደግሞም ስለ ወይን ቦታው ልዘምር፤ ወዳጄ በለምለም ኰረብታ ላይ የወይን ቦታ ነበረው። ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።” የሚያሰክር መጠጥ ፍለጋ ማልደው ለሚነሡ፣ እስኪያነድዳቸውም ወይን በመጠጣት ሌሊቱን ለሚያነጉ ወዮላቸው! በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፣ ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም። ስለዚህ ሕዝቤ ዕውቀት በማጣቱ ይማረካል፤ መኳንንቱም በራብ ይሞታሉ፤ ሕዝቡም በውሃ ጥም ይቃጠላል። ስለዚህ ሲኦል ሆዷን አሰፋች፣ አፏንም ያለ ልክ ከፈተች፤ መኳንንቱና ሕዝቡ ከረብሸኞቻቸውና ከጨፋሪዎቻቸው ጋራ ወደዚያ ይወርዳሉ። ሰው ይዋረዳል፤ የሰው ልጅም ዝቅ ዝቅ ይላል፤ የእብሪተኛውም ዐይን ይሰበራል። የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን በፍትሕ ከፍ ከፍ ይላል፤ ቅዱሱም አምላክ ቅድስናውን በጽድቅ ይገልጻል። በጎችም በገዛ መሰማሪያቸው እንደሚሰማሩ ሆነው ይግጣሉ፤ የበግ ጠቦቶችም በባለጠጎች ፍርስራሽ ላይ ሣር ይበላሉ። ኀጢአትን በማታለል ገመድ ለሚስቡ፣ በደልንም በሠረገላ ማሰሪያ ለሚጐትቱ ወዮላቸው! “በዐይናችን እንድናይ እግዚአብሔር ይቸኵል፤ ሥራውንም ያፋጥን፤ የእስራኤልን ቅዱስ፣ የርሱን ዕቅድ እንድናውቃት ትቅረብ፤ ትምጣም” ለሚሉ ወዮላቸው! መሬቱን ቈፈረ፤ ድንጋይንም ለቅሞ አወጣ፤ ምርጥ የሆነውንም ወይን ተከለበት። በመካከሉ መጠበቂያ ማማ ሠራ፤ የወይን መጭመቂያ ጕድጓድም አበጀ፤ ከዚያ መልካም ፍሬ ያፈራል ብሎ ዐሰበ፤ ነገር ግን ኮምጣጣ ፍሬ አፈራ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
አሞጽ 4:7

“መከር ሊደርስ ሦስት ወር ሲቀረውም፣ ዝናብ ከለከልኋችሁ፤ በአንዱ ከተማ ላይ አዘነብሁ፤ በሌላው ላይ ግን እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ አንዱ ዕርሻ ሲዘንብለት፣ ሌላው ዝናብ ዐጥቶ ደረቀ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 11:14

ከዚያም ዛፏን፣ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ” አላት። ደቀ መዛሙርቱም ይህን ሲናገር ሰሙ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 12:13

ስንዴን ይዘራሉ፤ እሾኽን ያጭዳሉ፤ ይደክማሉ፤ የሚያገኙት ግን የለም። ከእግዚአብሔርም ጽኑ ቍጣ የተነሣ፣ በመኸራችሁ ውጤት ታፍራላችሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 10:7

ያቀረቡላችሁን ሁሉ እየበላችሁና እየጠጣችሁ በዚያ ቤት ተቀመጡ፤ ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል። ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው ቤት አትዘዋወሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሚክያስ 7:1

ለእኔ ወዮልኝ! የወይን ዕርሻ በሚቃረምበት ጊዜ፣ የበጋ ፍራፍሬ እንደሚለቅም ሰው ሆኛለሁ፤ የሚበላ የወይን ዘለላ የለም፤ የምንጓጓለት፣ ቶሎ የሚደርሰው በለስም አልተገኘም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 22:29

“የእህልህን ወይም የወይን ጠጅህን በኵራት ለእኔ ከማቅረብ ወደ ኋላ አትበል። “የወንድ ልጆችህን በኵር ለእኔ ስጠኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 20:11

ሕፃን እንኳ ጠባዩ ንጹሕና ቅን መሆኑ፣ ከአድራጎቱ ይታወቃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 16:9

እህልህን ማጨድ ከምትጀምርበት ዕለት አንሥቶ ሰባት ሳምንት ቍጠር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 25:24-26

“አንድ ታላንት የተቀበለው አገልጋይ ቀርቦ፣ ‘ጌታ ሆይ፤ አንተ ካልዘራህበት የምታጭድ፣ ካልበተንህበትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን ዐውቃለሁ፤ ስለዚህ ፈራሁህ፤ ሄጄም መሬት ቈፍሬ ታላንትህን ጕድጓድ ውስጥ ደበቅሁት፤ ገንዘብህ ይኸውልህ’ አለው። “ጌታውም መልሶ፣ ‘አንተ ክፉ፣ ሰነፍ ባሪያ፤ ካልዘራሁበት የማጭድ፣ ካልበተንሁበትም የምሰበስብ መሆኔን ታውቅ ኖሯል?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 40:24

ተተክለው ምንም ያህል ሳይቈዩ፣ ተዘርተው ምንም ያህል ሳይሰነብቱ፣ ገና ሥር መስደድ ሳይጀምሩ አነፈሰባቸው፤ እነርሱም ደረቁ፤ ዐውሎ ነፋስም እንደ ገለባ ጠራርጎ ወሰዳቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 4:36-38

ዐጫጁ አሁንም ቢሆን እንኳ ደመወዙን እየተቀበለ ነው፤ ለዘላለም ሕይወት ይሆን ዘንድ አዝመራውን ይሰበስባል፤ ይህም ዘሪውና ዐጫጁ በጋራ ደስ እንዲላቸው ነው። ስለዚህ፣ ‘አንዱ ይዘራል፤ ሌላውም ያጭዳል’ የተባለው ምሳሌ እውነት ነው። ያልደከማችሁበትን እንድታጭዱ ላክኋችሁ፤ አድካሚውን ሥራ ሌሎች ሠሩ፤ እናንተም የድካማቸውን ፍሬ ሰበሰባችሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 9:10

ይህን የተናገረው በርግጥ ስለ እኛ አይደለምን? የተጻፈው በትክክል ስለ እኛ ነው፤ ዐራሹ የሚያርሰው፣ አበራዩ የሚያበራየው ከምርቱ ድርሻ እንዳለው ተስፋ በማድረግ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 3:2

ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀልም ጊዜ አለው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 6:9

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የወይን ፍሬ ተሟጦ እንደሚቃረም፣ ከእስራኤል የተረፉትን እንዲሁ ይቃርሟቸው። ወይን ለቃሚ እንደሚለቅም፣ እጅህን ወደ ቅርንጫፎቹ ደጋግመህ ዘርጋ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 23:10

“ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘እኔ ወደምሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ መከር በምትሰበስቡበት ጊዜ ከሰበሰባችሁት እህል የመጀመሪያውን ነዶ ለካህኑ አቅርቡ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 19:21-23

አንተ ያላስቀመጥኸውን የምትወስድ፣ ያልዘራኸውን የምታጭድ ጨካኝ ሰው ስለ ሆንህ ፈራሁህ።’ “ጌታውም እንዲህ አለው፤ ‘አንተ ክፉ ባሪያ! በራስህ ቃል እፈርድብሃለሁ፤ ያላስቀመጥሁትን የምወስድ፣ ያልዘራሁትን የማጭድ፣ ጨካኝ ሰው መሆኔን ካወቅህ፣ መጥቼ ገንዘቤን ከነትርፉ እንድወስድ፣ ለምን ለሚሠሩበት ሰዎች አልሰጠህም?’

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 5:4

ልብ በሉ፤ ዕርሻችሁን ሲያጭዱ ለዋሉ ሠራተኞች ያልከፈላችሁት ደመወዝ በእናንተ ላይ ይጮኻል፤ የዐጫጆቹም ጩኸት ሁሉን ቻይ ወደ ሆነው ጌታ ጆሮ ደርሷል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 7:20

“ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ቍጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ በሰውና በእንስሳ ላይ፣ በዱር ዛፍና በምድር ፍሬ ላይ ይፈስሳል፤ ይነድዳል፤ አይጠፋምም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 37:30

“ሕዝቅያስ ሆይ፤ ይህ ምልክት ይሆንልሃል፤ “በዚህ ዓመት የገቦውን፣ በሚቀጥለው ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁ፤ ወይን ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 19:17

ለድኻ የሚራራ ለእግዚአብሔር ያበድራል፤ ስላደረገውም ተግባር ዋጋ ይከፍለዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 9:41

እውነት እላችኋለሁ፣ የክርስቶስ በመሆናችሁ በስሜ አንድ ኩባያ ውሃ የሚሰጣችሁ ሁሉ ዋጋውን አያጣም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 13:44

“መንግሥተ ሰማይ በዕርሻ ውስጥ የተደበቀ ሀብት ትመስላለች፤ አንድ ሰው ባገኛት ጊዜ መልሶ ሸሸጋት፤ ከመደሰቱም የተነሣ፣ ሄዶ ያለውን ሁሉ በመሸጥ ያን የዕርሻ ቦታ ገዛ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 72:16

በምድሪቱ ላይ እህል ይትረፍረፍ፤ በተራሮችም ዐናት ላይ ይወዛወዝ። ፍሬው እንደ ሊባኖስ ይንዠርገግ፤ በከተማ ያለውም እንደ ሜዳ ሣር እጅብ ብሎ ይውጣ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 22:36

እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “አሁን ግን ኰረጆም፣ ከረጢትም ያለው ሰው ይያዝ፤ ሰይፍ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ይግዛ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 28:8

እግዚአብሔር በጐተራህና እጅህ በነካው ሁሉ በረከቱን ይልካል። አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህም ምድር ላይ ይባርክሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 11:6

ጧት ላይ ዘርህን ዝራ፤ ማታም ላይ እጅህ ሥራ አይፍታ፤ ይህ ወይም ያ፣ ወይም ሁለቱ መልካም ይሁኑ፣ የቱ እንደሚያፈራ አታውቅምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 20:1-16

“መንግሥተ ሰማይ ለወይኑ ቦታ ሠራተኞችን ለመቅጠር ማልዶ የወጣን የአትክልት ስፍራ ባለቤት ትመስላለች። በመጀመሪያ የተቀጠሩት ሲቀርቡ ብልጫ ያለው ክፍያ የሚያገኙ መስሏቸው ነበር፤ ነገር ግን እነርሱም አንዳንድ ዲናር ተከፈላቸው። ክፍያውን ሲቀበሉ በባለቤቱ ላይ በማጕረምረም፣ ‘እነዚህ በመጨረሻ የተቀጠሩት አንድ ሰዓት ብቻ ሲሠሩ፣ ቀኑን ሙሉ በሥራ ስንደክምና በፀሓይ ስንንቃቃ ከዋልነው ጋራ እንዴት እኩል ትከፍለናለህ?’ አሉት። “እርሱም አንደኛውን ሠራተኛ እንዲህ አለው፤ ‘ወዳጄ ሆይ፤ በደል አላደረስሁብህም፤ በአንድ ዲናር ለመሥራት ከእኔ ጋራ ተስማምተህ አልነበረምን? በል ድርሻህን ይዘህ ሂድ፤ ለአንተ የሰጠሁትን ያህል በመጨረሻ ለመጣውም ሰው መስጠት እፈልጋለሁ። ታዲያ በራሴ ገንዘብ የፈለግሁትን ማድረግ አልችልምን? ወይስ ቸር በመሆኔ ምቀኛነት ያዘህን?’ “ስለዚህ ኋለኞች ፊተኞች፣ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 28:24-25

ገበሬ ሊዘራ መሬቱን ሲያዘጋጅ ያለ ማቋረጥ ያርሳልን? ጓሉን ሲከሰክስ፣ ዐፈሩን ሲያለሰልስ ይከርማልን? ዕርሻውን አስተካክሎ፣ ጥቍር አዝሙድና ከሙን አይዘራምን? ስንዴውንስ በትልሙ፣ ገብሱን በተገቢ ቦታው፣ አጃውንም በተመደበው ስፍራ አይዘራምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 23:14-16

“በዓመት ሦስት ጊዜ ለእኔ በዓልን ታከብራላችሁ። “የቂጣ በዓልን አክብር፤ እንዳዘዝሁህ ሰባት ቀን እርሾ የሌለውን ቂጣ ብላ፤ ይህንም በአቢብ ወር በተወሰነ ቀን አድርግ፤ በዚያ ወር ከግብጽ ወጥተሃልና። “ማንም በፊቴ ባዶ እጁን አይቅረብ። “በማሳህ ላይ በዘራኸው እህል በኵራት የመከርን በዓል አክብር። “በዓመቱ መጨረሻ በማሳህ ላይ ያለውን እህልህን ስትሰበስብ የመክተቻውን በዓል አክብር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘሌዋውያን 19:23-25

“ ‘ወደ ምድሪቱ ገብታችሁ ማንኛውንም ዐይነት ፍሬ የሚሰጥ ዛፍ በምትተክሉበት ጊዜ፣ ፍሬው ለመብላት ያልተገረዘ መሆኑን ዕወቁ፤ ለሦስት ዓመትም የተከለከለ በመሆኑ አይበላ። በአራተኛውም ዓመት ፍሬው ሁሉ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የምስጋና መሥዋዕት ይሆናል። በዐምስተኛው ዓመት ግን ፍሬውን ትበላላችሁ፤ በዚህም ሁኔታ ፍሬው ይበዛላችኋል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 107:37-38

በዕርሻውም ዘሩበት፤ ወይንም ተከሉ፤ ብዙ ፍሬም አመረቱ። ይባርካቸዋል፤ እነርሱም እጅግ ይበዛሉ፤ የከብቶቻቸውም ብዛት እንዲያንስ አያደርግም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ሆይ፥ የዘላለም አምላክ፥ ልዑል ጌታ! አንተ ጻድቅ፥ ቅዱስ እና ለማንኛውም ከፍተኛ ምስጋናና አምልኮ የተገባህ ስለሆንክ አመሰግንሃለሁ። ዛሬ በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ወደ አንተ መጥቼ ለቸርነትህና በሕይወቴ ላደረግኸው ለእያንዳንዱ በረከት አመሰግንሃለሁ። ፈቃድህ በሁሉም ነገር እንድበለጽግ ነው፥ በዚህም በሕይወቴ ውስጥ በሁሉም ዘርፍ መገኘትህ በእኔ ውስጥ ይንጸባረቃል። በመልካምም ሆነ በመጥፎ ጊዜ በመንፈስ ቅዱስህ አማካኝነት ብቻ ድል እንደምቀዳጅና የተባረከ ሕይወት እንደምኖር እንድገነዘብ እርዳኝ። አንተ በቃልህ "እንዲህ ይላል፥ እግዚአብሔር ጻድቁን ይባርከዋል፤ እንደ ጋሻ በሞገስ ይከብበዋል።" ስትል ተናግረሃል። በሕይወቴ ውስጥ ፈውስን፥ አቅርቦትንና ጥበቃን በማምጣት በተለየ መንገድ ስለባረክኸኝ አመሰግንሃለሁ። በትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛ ሰዎችን በመንገዴ ላይ በማስቀመጥ ባርከኸኛል። በእያንዳንዱ ውጊያዬ ድል እንድቀዳጅ በማድረግ፥ ድልን ስለሰጠኸኝ፥ ለዚህና ለሌሎችም ብዙ ነገሮች ክብርና ምስጋና ሁሉ ላንተ ይሁን። ጌታ ሆይ፥ ከሁሉም በላይ ልቤን ከትዕቢትና ከእኔነት እንድጠብቅ እርዳኝ። በኢየሱስ ስም። አሜን!
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች