Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


ስለ ፍትህ ጥቅሶች

ስለ ፍትህ ጥቅሶች

በዚህ አስቸጋሪ ወቅት፣ ፍትህ በጣም አስፈላጊ ነው። ፍትህ አለመኖር ምድርን በሙሉ እንደሚጎዳና መንፈሳዊ ብክለት እንደሚፈጥር መረዳት አለብን። ፍትህ እጅግ በጣም አስደናቂ የሆነ ጸጋ ሲሆን በፍጥረቱ ላይ ስምምነትን፣ ሥርዓትንና ደህንነትን ለማምጣት መገለጽ አለበት።

ፍትህ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ከእግዚአብሔር በጣም ታዋቂ ከሆኑት ባሕርያት አንዱ ሲሆን፣ ለመረዳት ግን አስቸጋሪ ነው። የእግዚአብሔርን ጽድቅ ከቅድስናው ወይም ከቸርነቱ ለመለየት አስቸጋሪ ይመስላል። መዝሙር 11፥7 "እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፥ ጽድቅንም ይወዳል፤ ቅኖች የፊቱን ያያሉ።"

እንዴት ፍትህን መለማመድ እንችላለን? በጣም ቀላል ነው፤ እግዚአብሔር ለእኛ እንዳደረገው ለሌሎች እናድርግ። ለምሳሌ፣ እግዚአብሔር ይቅር ብሎናል? እኛም ለሌሎች ይቅር እንባል። እግዚአብሔር ይባርከናል? እኛም ሌሎችን እንባርክ።

እንደ ዓለም ባለቤት አናስብ፤ እውነተኛው ባለቤት ሊቆጣ ይችላልና። ጊዜያችንን እንደምንቆጣጠረው አድርገን አናስብ፤ ምንም መለወጥ አንችልምና! ፈጣሪን እናክብር፤ እግዚአብሔርም ይባርከናል። ቆላስይስ 3፥25 "ዐመፀኛ የዐመፀኝነቱን ዋጋ ይቀበላልና፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ለሰው ፊት አያያዝ የለም።"


ሚክያስ 6:8

ሰው ሆይ፤ መልካም የሆነውን አሳይቶሃል፤ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው? ፍትሕን ታደርግ ዘንድ፣ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፣ በአምላክህም ፊት በትሕትና ትራመድ ዘንድ አይደለምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
አሞጽ 5:24

ነገር ግን ፍትሕ እንደ ወንዝ፣ ጽድቅም እንደማይደርቅ ምንጭ ይፍሰስ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:17

መልካም ማድረግን ተማሩ፤ ፍትሕን እሹ፣ የተገፉትን አጽናኑ፤ አባት ለሌላቸው ቁሙላቸው፤ ለመበለቶችም ተሟገቱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 21:3

ከመሥዋዕት ይልቅ ጽድቅንና ፍትሕን ማድረግ፣ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት አለው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:6

ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ብፁዓን ናቸው፤ ይጠግባሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:28

እግዚአብሔር ፍትሕን ይወድዳልና፣ ታማኞቹንም አይጥልም። ለዘላለምም ይጠብቃቸዋል፤ የኀጢአተኛው ዘር ግን ይጠፋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 61:8

“እኔ እግዚአብሔር ፍትሕን ስለምወድድ፣ ዝርፊያንና በደልን እጠላለሁ፤ በታማኝነቴም የሚገባቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ ከእነርሱም ጋራ የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 29:7

ጻድቅ ስለ ድኾች ፍትሕ ያውቃል፤ ክፉ ግን ደንታ የለውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 11:7

እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤ የጽድቅ ሥራም ይወድዳል፤ ቅኖችም ፊቱን ያያሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 106:3

ብፁዓን ናቸው፤ ፍትሕ እንዳይዛነፍ የሚጠብቁ፣ ጽድቅን ሁልጊዜ የሚያደርጉ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 30:18

እግዚአብሔር ግን ምሕረት ሊያደርግላችሁ ይታገሣል፤ ርኅራኄም ሊያሳያችሁ ይነሣል። እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ነውና፣ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁት ብፁዓን ናቸው!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:19

ወዳጆቼ ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ቍጣ ፈንታ ስጡ እንጂ አትበቀሉ፤ ጌታ “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” እንዳለ ተጽፏልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 33:5

እግዚአብሔር ጽድቅንና ፍትሕን ይወድዳል፤ ምድርም በምሕረቱ የተሞላች ናት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 9:7-8

እግዚአብሔር ግን ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ነው፤ መንበሩንም ለፍርድ አጽንቷል። ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤ ሕዝቦችንም በፍትሕ ይገዛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 1:17

በወንጌል የእግዚአብሔር ጽድቅ ተገልጧልና፤ ጽድቁም ከእምነት ወደ እምነት የሆነ ነው፤ “ጻድቅ በእምነት ይኖራል” ተብሎ እንደ ተጻፈው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 4:8

ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ በዚያ ቀን ለእኔ ይሰጠኛል፤ ደግሞም ለእኔ ብቻ ሳይሆን፣ የርሱን መገለጥ ለናፈቁ ሁሉ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 32:4

እርሱ ዐለት፣ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 22:3

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ፍትሕንና ጽድቅን አድርጉ፤ የተበዘበዘውን ከጨቋኙ እጅ አድኑት፤ መጻተኛውን፣ ወላጅ የሌለውንና መበለቲቱን አትበድሉ፤ አትግፏቸውም፤ በዚህም ስፍራ ንጹሕ ደም አታፍስሱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 82:3-4

ለዐቅመ ቢሶችና ለድኻ አደጎች ፍረዱላቸው፤ የችግረኛውንና የምስኪኑን መብት አስከብሩ። ወገን የሌለውንና ድኻውን ታደጉ፤ ከግፈኛውም እጅ አስጥሏቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 89:14

ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረቶች ናቸው፤ ምሕረትና ታማኝነት በፊትህ ይሄዳሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 31:8-9

“ስለ ራሳቸው መናገር ለማይችሉት፣ ለችግረኞችም ሁሉ መብት ተሟገት። ተናገር፤ በጽድቅም ፍረድ፤ የምስኪኖችንና የድኾችን መብት አስከብር።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 56:1

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ፍትሕን ጠብቁ፤ መልካሙን አድርጉ፤ ማዳኔ በቅርብ ነው፤ ጽድቄም ፈጥኖ ይገለጣልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 2:6-8

እግዚአብሔር “ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይሰጠዋል”። በጎ የሆነውን ጸንቶ በማድረግ ክብርን፣ ሞገስንና ዘላለማዊነትን ለሚሹ የዘላለም ሕይወት ይሰጣቸዋል። ነገር ግን በራስ ወዳዶች፣ እውነትን ትተው ክፋትን በሚከተሉ ፍርድና ቍጣ ይደርስባቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:6

ጽድቅህን እንደ ብርሃን፣ ፍትሕህን እንደ ቀትር ፀሓይ ያበራዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:10

ስለ ጽድቅ ብለው የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማይ የእነርሱ ናትና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 1:9

ኀጢአታችንን ብንናዘዝ ኀጢአታችንን ይቅር ሊለን፣ ከዐመፃም ሁሉ ሊያነጻን እርሱ ታማኝና ጻድቅ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 25:9

ዝቅ ያሉትን በፍትሕ ይመራቸዋል፤ ለትሑታንም መንገዱን ያስተምራቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 2:6-9

እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከአንደበቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣል። እርሱ ለቅኖች ትክክለኛ ጥበብ ያከማቻል፤ ያለ ነቀፋ ለሚሄዱትም ጋሻ ይሆናቸዋል፤ የፍትሕን መንገድ ይጠብቃል፤ የታማኞቹንም አካሄድ ያጸናል። በዚያ ጊዜ ጽድቅን፣ ፍትሕን፣ ሚዛናዊነትን፣ መልካሙንም መንገድ ሁሉ ትገነዘባለህ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 3:22-24

ይህ የእግዚአብሔር ጽድቅ ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የሚገኝ ጽድቅ ነው። ልዩነት የለም፤ ምክንያቱም ሁሉም ኀጢአትን ሠርተዋል፤ የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሏቸዋል፤ በኢየሱስ ክርስቶስ በሆነው ቤዛነት እንዲያው በጸጋው ጸድቀዋል፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 1:9

ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከባልንጀሮችህ በላይ አስቀመጠህ፣ የደስታንም ዘይት ቀባህ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 21:15

ፍትሕ ሲሰፍን ጻድቁን ደስ ያሠኘዋል፤ ክፉ አድራጊዎችን ግን ያሸብራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘካርያስ 7:9

“የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እውነተኛ ፍትሕ አስፍኑ፣ እርስ በርሳችሁ ምሕረትና ርኅራኄን አድርጉ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 9:24

የሚመካ ግን፣ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ በማወቁና፣ በምድር ላይ ምሕረትን፣ ፍትሕንና ጽድቅን የማደርግ መሆኔን በመረዳቱ፣ በዚህ ይመካ፤ እኔ በእነዚህ ነገሮች፣ እደሰታለሁና፤” ይላል እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 42:1

“እነሆ፤ ደግፌ የያዝሁት፣ በርሱም ደስ የሚለኝ የመረጥሁት አገልጋዬ፤ መንፈሴን በርሱ ላይ አደርጋለሁ፤ ለአሕዛብም ፍትሕን ያመጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 45:6

አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 103:6

እግዚአብሔር ለተጨቈኑ ሁሉ፣ ቅን ፍርድንና ፍትሕን ይሰጣቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 3:26

በአሁኑ ዘመን እግዚአብሔር ይህን ያደረገው፣ ጽድቁን ይኸውም እርሱ ራሱ ጻድቅ ሆኖ፣ በኢየሱስ የሚያምነውን የሚያጸድቅ መሆኑን ለማሳየት ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 75:7

ነገር ግን የሚፈርድ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱ አንዱን ዝቅ፣ ሌላውን ከፍ ያደርጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መክብብ 3:17

እኔም በልቤ፣ “ለማንኛውም ድርጊት፣ ለማንኛውም ተግባር ጊዜ ስላለው፣ አምላክ ጻድቁንና ኀጢአተኛውን ወደ ፍርድ ያመጣቸዋል” ብዬ አሰብሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 12:18-20

“እነሆ፤ የመረጥሁት፣ የምወድደውና ነፍሴ ደስ የተሠኘችበት ብላቴናዬ፣ መንፈሴን በርሱ ላይ አኖራለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍትሕን ያውጃል። አይጨቃጨቅም ወይም አይጮኽም፤ ድምፁም በአደባባይ አይሰማም። ፈሪሳውያንም ይህን አይተው፣ “እነሆ፣ ደቀ መዛሙርትህ በሰንበት ቀን ያልተፈቀደውን እያደረጉ ነው” አሉት። ፍትሕን ለድል እስኪያበቃ ድረስ፣ የተቀጠቀጠውን ሸንበቆ አይሰብርም፤ የሚጤሰውንም የጧፍ ክር አያጠፋም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 5:16

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን በፍትሕ ከፍ ከፍ ይላል፤ ቅዱሱም አምላክ ቅድስናውን በጽድቅ ይገልጻል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 37:23

ሁሉን ቻይ አምላክ ከአእምሯችን በላይ ነው፤ በኀይልና በፍርድ ታላቅ ነው፣ ጽድቁም ብዙ ነው፤ ማንንም አይጨቍንም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 1:20

የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያመጣምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 6:13

ብልቶቻችሁን የክፋት መሣሪያ አድርጋችሁ ለኀጢአት አታቅርቡ፤ ይልቁንስ ከሞት ወደ ሕይወት እንደ ተሻገሩ ሰዎች አድርጋችሁ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 1:30

በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከርሱ የተነሣ ነው፤ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፣ ጽድቃችንና ቅድስናችን፣ ቤዛችንም ሆኗል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 5:1

እንግዲህ በእምነት ስለ ጸደቅን፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋራ ሰላም አለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 99:4

ፍትሕን የምትወድድ፣ ኀያል ንጉሥ ሆይ፤ አንተ ትክክለኝነትን መሠረትህ፤ ፍትሕንና ቅንነትንም፣ ለያዕቆብ አደረግህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 14:17

የእግዚአብሔር መንግሥት ጽድቅና ሰላም፣ በመንፈስ ቅዱስም የሆነ ሐሤት ነው እንጂ፣ የመብልና የመጠጥ ጕዳይ አይደለም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:15

የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፤ ጆሮዎቹም ለጩኸታቸው ክፍት ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:7

ልጆች ሆይ፤ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ፤ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ፣ ጽድቅን የሚያደርግ ጻድቅ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 51:5

ጽድቄ በፍጥነት እየቀረበ፣ ማዳኔም እየደረሰ ነው፤ ክንዴም ለመንግሥታት ፍትሕን ያመጣል፤ ደሴቶች ወደ እኔ ይመለከታሉ፤ ክንዴንም በተስፋ ይጠብቃሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 18:5-9

“በቅንነትና በትክክል የሚሠራ፣ ጻድቅ ሰው ቢገኝ፣ በኰረብታ ባሉ አብያተ ጣዖት የቀረበውን አይበላም፤ በእስራኤል ቤት ወዳሉት ጣዖታት አይመለከትም የባልንጀራውን ሚስት አያባልግም፤ ከሴት ጋራ በወር አበባዋ ጊዜ አይተኛም። ማንንም አይጨቍንም፤ ነገር ግን በመያዣ የወሰደውን እንኳ ለተበዳሪው ይመልሳል፤ ለተራበ የራሱን እንጀራ፣ ለተራቈተም ልብስ ይሰጣል እንጂ፣ በጕልበት አይቀማም። በዐራጣ አያበድርም፣ ከፍተኛ ወለድም አይቀበልም። እጁን ከበደል ይሰበስባል፤ በሰውና በሰው መካከል በትክክል ይፈርዳል። ሥርዐቴን ይከተላል፤ ሕጌንም በቅንነት ይጠብቃል። ይህ ሰው ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ገላትያ 6:7-8

አትታለሉ፤ እግዚአብሔር አይዘበትበትም። ሰው የሚዘራውን ያንኑ ያጭዳል። ሥጋዊ ምኞቱን ለማርካት የሚዘራ፣ ከሥጋ ጥፋትን ያጭዳል፤ መንፈስን ለማስደሰት የሚዘራ ግን ከመንፈስ የዘላለምን ሕይወት ያጭዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 17:10

“እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፣ እንደ ሥራው ፍሬ ለመስጠት፣ ልብን እመረምራለሁ፤ የአእምሮንም ሐሳብ እፈትናለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 10:2

ያላግባብ የተገኘ ሀብት አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ይታደጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 10:4

ለሚያምን ሁሉ ጽድቅ ይሆን ዘንድ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 5:9

የብርሃኑ ፍሬ በበጎነት፣ በጽድቅና በእውነት ሁሉ ዘንድ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 97:2

ደመናና ጥቅጥቅ ያለ ጭጋግ በዙሪያው አለ፤ ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:30

የጻድቅ አፍ ጥበብን ይናገራል፤ አንደበቱም ፍትሓዊ ነገር ያወራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሶፎንያስ 3:5

በርሷ ውስጥ ያለው እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ አይሳሳትም፤ በየማለዳው ቅን ፍርድ ይሰጣል፤ በየቀኑም አይደክምም፤ ዐመፀኞች ግን ዕፍረት አያውቁም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 3:12

ምክንያቱም የጌታ ዐይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮቹም ጸሎታቸውን ለመስማት የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:1

እግዚአብሔር የተጭበረበረ ሚዛንን ይጸየፋል፤ ትክክለኛ መለኪያ ግን ደስ ያሠኘዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 59:9

ስለዚህ ፍትሕ ከእኛ ርቋል፤ ጽድቅም ወደ እኛ አይመጣም፤ ብርሃንን ፈለግን፤ ነገር ግን ሁሉ ጨለማ ነው፤ የብርሃንን ጸዳል ፈለግን፤ የምንሄደው ግን በድንግዝግዝታ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 8:3

እግዚአብሔር ፍትሕን ያጣምማልን? ሁሉን ቻይ አምላክስ ጽድቅን ያጣምማልን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 16:8

ከጽድቅ ጋራ ጥቂቱ ነገር፣ በግፍ ከሚገኝ ብዙ ትርፍ ይሻላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 10:16

የጻድቃን ደመወዝ ሕይወት ታስገኝላቸዋለች፤ የክፉዎች ትርፍ ግን ቅጣትን ታመጣባቸዋለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ነገሥት 10:9

በአንተ ደስ ተሰኝቶ በእስራኤል ዙፋን ላይ ያስቀመጠህ እግዚአብሔር አምላክህ ቡሩክ ይሁን፤ እግዚአብሔር በዘላለም ፍቅሩም እስራኤልን ከመውደዱ የተነሣ፣ ፍትሕና ጽድቅ እንዲሰፍን አንተን ንጉሥ አደረገህ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 10:17-18

እግዚአብሔር ሆይ፤ የተገፉትን ምኞት ትሰማለህ፤ ልባቸውን ታበረታለህ፤ ጆሮህንም ወደ እነርሱ ጣል ታደርጋለህ፤ ከዐፈር የተፈጠረ ሰው ከእንግዲህ እንዳያስጨንቃቸው፣ አንተ ለድኻ አደጉና ለተገፋው ትሟገታለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:33

ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 11:4

ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤ በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 5:21

እኛ በርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንድንሆን፣ ኀጢአት የሌለበትን እርሱን እግዚአብሔር ስለ እኛ ኀጢአት አደረገው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 92:15

“እግዚአብሔር ትክክለኛ ነው፤ እርሱ ዐለቴ ነው፤ በርሱ ዘንድ እንከን የለም” ይላሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 2:29

እርሱ ጻድቅ መሆኑን ካወቃችሁ፣ ጽድቅን የሚያደርግ ሁሉ ከርሱ እንደ ተወለደ ታውቃላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 24:24-25

በደለኛውን፣ “አንተ ንጹሕ ነህ” የሚለውን፣ ሕዝቦች ይረግሙታል፤ መንግሥታትም ያወግዙታል። በደለኛውን፣ “አንተ ጥፋተኛ ነህ” የሚሉት ግን መልካም ነገር ይገጥማቸዋል፤ የተትረፈረፈ በረከትም ይወርድላቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 72:1-2

እግዚአብሔር ሆይ፤ ፍትሕን ለንጉሥ፣ ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ ዐድል፤ የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት፣ ግብር ያመጡለታል፤ የዐረብና የሳባ ነገሥታት፣ እጅ መንሻ ያቀርባሉ። ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ይገዙለታል። ድኻው በጮኸ ጊዜ፣ ችግረኛውና ረዳት የሌለውን ይታደገዋል። ለድኾችና ለችግረኞች ይራራል፤ ድኾችንም ከሞት ያድናል። ሕይወታቸውን ከጭቈናና ከግፍ ያድናል፤ ደማቸውም በርሱ ፊት ክቡር ነው። ዕድሜው ይርዘም! ወርቅም ከሳባ ይምጣለት፤ ዘወትር ይጸልዩለት፤ ቀኑንም ሙሉ ይባርኩት። በምድሪቱ ላይ እህል ይትረፍረፍ፤ በተራሮችም ዐናት ላይ ይወዛወዝ። ፍሬው እንደ ሊባኖስ ይንዠርገግ፤ በከተማ ያለውም እንደ ሜዳ ሣር እጅብ ብሎ ይውጣ። ስሙ ለዘላለም ጸንቶ ይኑር፤ ዝናው ፀሓይ የምትኖረውን ዘመን ያህል ይዝለቅ። ሕዝቦች ሁሉ በርሱ ይባረኩ፤ ሕዝቡ ሁሉ ቡሩክ ነህ ይበለው። ብቻውን ድንቅ ነገር የሚያደርግ፣ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ። ክቡር ስሙ ለዘላለም ይባረክ፤ ምድርም ሁሉ በክብሩ ትሞላ። አሜን፤ አሜን። እርሱም ሕዝብህን በጽድቅ ይዳኛል፤ ለተቸገሩትም በትክክል ይፈርዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 28:17

ፍትሕን የመለኪያ ገመድ፣ ጽድቅንም ቱንቢ አደርጋለሁ፤ ውሸት መጠጊያችሁን የበረዶ ዝናብ ይጠራርገዋል፤ መደበቂያችሁንም ውሃ ያጥለቀልቀዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 140:12

እግዚአብሔር ለድኻ ፍትሕን እንደሚያስከብር፣ ለችግረኛውም ትክክለኛ ፍርድን እንደሚሰጥ ዐውቃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 58:11

ሰዎችም፣ “በርግጥ ለጻድቃን ብድራት ተቀምጦላቸዋል፤ በእውነትም በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ” ይላሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 16:20

በሕይወት እንድትኖርና አምላክህ እግዚአብሔር የሚሰጥህን ምድር እንድትወርስ፣ የጽድቅ ፍርድን ብቻ ተከተል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 18:7-8

እግዚአብሔርስ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን? ከመጠን በላይስ ችላ ይላቸዋልን? እላችኋለሁ፤ ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል፤ ነገር ግን የሰው ልጅ በሚመጣበት ጊዜ በምድር ላይ እምነትን ያገኝ ይሆንን?”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 51:4-5

“ወገኔ ሆይ፤ አድምጠኝ፤ ሕዝቤ ሆይ፤ ስማኝ፤ ሕግ ከእኔ ይወጣል፤ ፍርዴም ለሕዝቦች ብርሃን ይሆናል። ጽድቄ በፍጥነት እየቀረበ፣ ማዳኔም እየደረሰ ነው፤ ክንዴም ለመንግሥታት ፍትሕን ያመጣል፤ ደሴቶች ወደ እኔ ይመለከታሉ፤ ክንዴንም በተስፋ ይጠብቃሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 21:21

ጽድቅንና ፍቅርን የሚከተል፤ ሕይወትን ብልጽግናንና ክብርን ያገኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 33:5

እግዚአብሔር በአርያም ተቀምጧልና ከፍ ከፍ አለ፤ ጽዮንን በጽድቅና በፍትሕ ይሞላታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 34:12

በእውነት እግዚአብሔር ክፋትን አይሠራም፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ፍትሕን አያጣምምም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 10:34-35

ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መናገር ጀመረ፤ “እግዚአብሔር ለማንም እንደማያዳላ በእውነት ተረድቻለሁ፤ ነገር ግን እርሱን የሚፈሩትንና ጽድቅን የሚያደርጉትን ሁሉ ከየትኛውም ወገን ቢሆኑ ይቀበላቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 10:18

እርሱ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች ይፈርዳል፤ መጻተኛውንም ምግብና ልብስ በመስጠት ይወድዳል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 36:6

ጽድቅህ እንደ ታላላቅ ተራሮች፣ ፍርድህም እጅግ ጥልቅ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሰውንም እንስሳንም ታድናለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 23:23

“እናንተ ግብዞች የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን፤ ወዮላችሁ! ከአዝሙድ፣ ከእንስላልና ከከሙን ዐሥራት እየሰጣችሁ በሕጉ ውስጥ ዋነኛ የሆኑትን ማለትም ፍትሕን፣ ምሕረትንና ታማኝነትን ግን ንቃችኋልና፤ እነዚያን ሳትተዉ እነዚህን ማድረግ በተገባችሁ ነበር፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 24:12

አንተም፣ “ስለዚህ ነገር ምንም አላውቅም” ብትል፣ ልብን የሚመረምር እርሱ አያስተውልምን? ሕይወትህን የሚጠብቃት እርሱ አያውቅምን? ለእያንዳንዱ ሰው እንደ ሥራው መጠን አይከፍለውምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 1:17

በፍርድ አድልዎ አታድርጉ፤ ትልቁንም ትንሹንም እኩል እዩ፤ ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ፣ ማንኛውንም ሰው አትፍሩ። ከዐቅማችሁ በላይ የሆነውን ሁሉ ወደ እኔ አምጡት፤ እኔ አየዋለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 75:2

አንተም እንዲህ አልህ፤ “ለይቼ በወሰንኋት ሰዓት፣ በቅን የምፈርድ እኔ ነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 3:5-6

የእኛ ዐመፃ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አጕልቶ የሚያሳይ ከሆነ፣ ምን ማለት እንችላለን? እንደ ሰው ለመከራከር ያህል እግዚአብሔር በእኛ ላይ ቍጣውን በማምጣቱ ዐመፀኛ ነውን? እንደ ሰው ሲታሰብ ማለቴ ነው። ከቶ አይሆንም! እንዲህ ቢሆንማ ኖሮ እግዚአብሔር በዓለም ላይ እንዴት ሊፈርድ ይችላል?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 2:24

ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በዕንጨት መስቀል ላይ ተሸከመ፤ በርሱ ቍስል እናንተ ተፈውሳችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 32:35-36

በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፤ ጊዜው ሲደርስ እግራቸው ይሰናከላል፤ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቧል፤ የሚመጣባቸውም ፍርድ ፈጥኖባቸዋል።” ኀይላቸው መድከሙን፣ ባሪያም ሆነ ነጻ ሰው አለመቅረቱን በሚያይበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ይፈርዳል፤ ለአገልጋዮቹም ይራራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 50:6

ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤ እግዚአብሔር ራሱ ፈራጅ ነውና። ሴላ

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 1:6

እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ይጠብቃልና፤ የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 2:2

እንደዚህ በሚያደርጉትም ላይ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነተኛ መሆኑን እናውቃለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 94:15

ፍርድ ተመልሶ በጽድቅ አሠራር ላይ ይመሠረታል፤ ልባቸውም ቀና የሆነ ሁሉ ይከተሉታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 40:14

ዕውቀት ለማግኘት እግዚአብሔር ማንን አማከረ? ትክክለኛውንስ መንገድ ማን አስተማረው? ዕውቀትን ያስተማረው፣ የማስተዋልንም መንገድ ያሳየው ማን ነበር?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 28:5

ክፉዎች ፍትሕን አያስተውሉም፤ እግዚአብሔርን የሚሹ ግን ሙሉ በሙሉ ያውቁታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 1:26

ፈራጆችሽን እንደ ጥንቱ፣ አማካሪዎችሽንም እንደ ቀድሞው እመልሳለሁ፤ ከዚያም የጽድቅ መዲና፣ የታመነች ከተማ ተብለሽ ትጠሪያለሽ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:137

እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ፍርድህም ትክክል ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 9:14

እንግዲህ ምን እንላለን? በእግዚአብሔር ዘንድ ዐመፃ አለን? ፈጽሞ!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 5:17

በአንድ ሰው መተላለፍ ምክንያት ሞት በዚህ ሰው በኩል የነገሠ ከሆነ፣ የእግዚአብሔርን የተትረፈረፈ ጸጋና የጽድቅ ስጦታ የተቀበሉት፣ በአንዱ ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እንዴት አብልጠው በሕይወት አይነግሡ!

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 15:9

እግዚአብሔር የክፉዎችን መንገድ ይጸየፋል፤ ጽድቅን የሚከታተሉትን ግን ይወድዳቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 112:5

ለጋስና ያለ ማንገራገር የሚያበድር፣ ሥራውንም በትክክል የሚያከናውን ሰው መልካም ይሆንለታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 3:25

በደሙም በሆነው እምነት፣ እግዚአብሔር የማስተሰረያ መሥዋዕት አድርጎ አቅርቦታል፤ ይህንም ያደረገው ቀድሞ የተፈጸመውን ኀጢአት ሳይቀጣ በትዕግሥት በማለፍ ጽድቁን ለማሳየት ነው፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 29:26

ብዙዎች በገዥ ፊት ተደማጭነት ማግኘት ይሻሉ፤ ሰው ፍትሕ የሚያገኘው ግን ከከእግዚአብሔር ዘንድ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 89:14-15

ጽድቅና ፍትሕ የዙፋንህ መሠረቶች ናቸው፤ ምሕረትና ታማኝነት በፊትህ ይሄዳሉ። ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እልልታን የሚያውቅ፣ በፊትህም ብርሃን የሚሄድ ሕዝብ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 34:10-12

“ስለዚህ፣ እናንተ አስተዋዮች ስሙኝ፤ ክፋትን ማድረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ፣ በደልንም መፈጸም ሁሉን ቻይ አምላክ ይራቅ። ለሰው እንደ ሥራው ይመልስለታል፤ እንደ አካሄዱም ይከፍለዋል። በእውነት እግዚአብሔር ክፋትን አይሠራም፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ፍትሕን አያጣምምም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 12:11

ቅጣት ሁሉ በወቅቱ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰዎች የጽድቅና የሰላም ፍሬ ያስገኝላቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 32:17

የጽድቅ ፍሬ ሰላም፣ የጽድቅ ውጤትም ጸጥታና ለዘላለም ያለ ሥጋት ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 1:6

ሁለቱም የጌታን ትእዛዝና ሥርዐት ሁሉ ጠብቀው ያለ ነቀፋ የሚኖሩ፣ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቃን ነበሩ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 3:18

እንዲሁም ክርስቶስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኀጢአት ሞቷልና፤ ወደ እግዚአብሔር ያቀርባችሁ ዘንድ ጻድቅ የሆነው እርሱ ስለ ዐመፀኞች ሞተ፤ እርሱ በሥጋ ሞተ፤ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 36:6-7

ክፉዎችን በሕይወት አያኖርም፤ ለተቸገሩት ግን በቅን ይፈርዳል። ዐይኖቹን ከጻድቃን ላይ አያነሣም፤ ከነገሥታት ጋራ በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤ ለዘላለምም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 4:5

ነገር ግን ለማይሠራ፣ ሆኖም ኀጥኡን በሚያጸድቀው ለሚያምን፣ እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 59:16-17

ማንም እንደሌለ አየ፤ ወደ እርሱ የሚማልድ ባለመኖሩ ተገረመ፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ ድነት አመጣለት፤ የራሱም ጽድቅ ደግፎ ያዘው። ጽድቅን እንደ ጥሩር አጠለቀ፤ የድነትን ቍር በራሱ ላይ ደፋ፤ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፤ መጐናጸፊያ እንደሚደረብም ቅናትን ደረበ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 21:2

ለሰው መንገዱ ሁሉ ቀና ይመስለዋል፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 42:3

የተቀጠቀጠ ሸንበቆ አይሰብርም፤ የሚጤስም የጧፍ ክር አያጠፋም፤ ፍትሕን በታማኝነት ያመጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ዜና መዋዕል 19:7

አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ ፍርድ ማጣመም፣ አድልዎ ማድረግና መማለጃ መቀበል ስለሌለ ተጠንቅቃችሁ ፍረዱ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 9:7

ለመንግሥቱ ስፋት፣ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ያዕቆብ 2:13

ምክንያቱም ምሕረት ያላደረገ ሁሉ ያለ ምሕረት ይፈረድበታል፤ ምሕረት በፍርድ ላይ ያይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 33:15

“ ‘በዚያ ዘመንና በዚያ ጊዜ፣ ከዳዊት ቤት ጻድቅ ቅርንጫፍ አበቅላለሁ፤ በምድሪቱም ፍትሕንና ጽድቅን ያደርጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:121

ፍትሕና ጽድቅ ያለበትን ሠርቻለሁ፤ ለሚጨቍኑኝ አሳልፈህ አትስጠኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 27:5

እናንተን እንደ ቅኖች መቍጠር፣ የማላደርገው ነገር ነው፤ ጨዋነቴንም እስክሞት ድረስ አልጥልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:9

ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 11:30

የጻድቅ ፍሬ የሕይወት ዛፍ ናት፤ ነፍሳትን የሚማርክም ጠቢብ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:10

የእግዚአብሔር ልጆችና የዲያብሎስ ልጆች ተለይተው የሚታወቁት በዚህ ነው፤ ጽድቅን የማያደርግ፣ ወንድሙንም የማይወድድ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 58:6

“እንግዲህ እኔ የመረጥሁት ጾም፣ የጭቈናን ሰንሰለት እንድትበጥሱ፣ የቀንበርን ገመድ እንድትፈቱ፣ የተጨቈኑትን ነጻ እንድታወጡ፣ ቀንበርን ሁሉ እንድትሰብሩ አይደለምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:30

“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” ያለውን እናውቀዋለንና፤ ደግሞም፣ “ጌታ በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል” ይላል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 20:7

ጻድቅ ነቀፋ የሌለበት ሕይወት ይመራል፤ ከርሱም በኋላ የሚከተሉት ልጆቹ ብፁዓን ናቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 16:5

ዙፋን በፍቅር ይመሠረታል፤ ከዳዊት ቤት የሆነ፣ በፍርድ ፍትሕን የሚሻ፣ ጽድቅንም የሚያፋጥን፣ አንድ ሰው በታማኝነት በላዩ ይቀመጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 82:1-2

እግዚአብሔር በአማልክት ጉባኤ መካከል ተሰየመ፤ በአማልክትም ላይ ይፈርዳል፤ እንዲህም ይላል፤ “ፍትሕን የምታጓድሉት እስከ መቼ ነው? ለክፉዎች የምታደሉትስ እስከ መቼ ነው? ሴላ

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሕዝቅኤል 34:16

የጠፉትን እፈልጋለሁ፤ የባዘኑትንም እመልሳለሁ። የተጐዱትን እጠግናለሁ፤ የደከሙትንም አበረታለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውን ግን አጠፋለሁ። መንጋውን በፍትሕ እጠብቃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 7:9

ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣ ጻድቅ አምላክ ሆይ፤ የክፉዎችን ዐመፅ አጥፋ፤ ጻድቁን ግን አጽና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 12:28

በጽድቅ መንገድ ላይ ሕይወት አለ፤ በዚያ ጐዳና ላይ ሞት የለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 4:18

እንግዲህ፣ “ጻድቅ የሚድነው በጭንቅ ከሆነ፣ ዐመፀኛውና ኀጢአተኛው እንዴት ሊሆን ይሆን?”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 9:8

ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤ ሕዝቦችንም በፍትሕ ይገዛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 11:5-7

እግዚአብሔር ጻድቁንና ክፉውን ይመረምራል፤ ዐመፃን የሚወድዱትን ግን፣ ነፍሱ ትጠላቸዋለች። እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤ የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣ የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው። እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤ የጽድቅ ሥራም ይወድዳል፤ ቅኖችም ፊቱን ያያሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:4

ይኸውም በሥጋ ሳይሆን በመንፈስ በምንመላለስ በእኛ፣ ሕጉ የሚጠይቀው ጽድቅ ሙሉ በሙሉ እንዲፈጸም ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:17-18

የክፉዎች ክንድ ይሰበራልና፣ ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ደግፎ ይይዛቸዋል። እግዚአብሔር የንጹሓንን የሕይወት ዘመን ያውቃል፤ ርስታቸውም ለዘላለም ይኖራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:15-16

የእግዚአብሔር ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፤ ጆሮዎቹም ለጩኸታቸው ክፍት ናቸው። የእግዚአብሔር ፊት ግን፣ መታሰቢያቸውን ከምድር ለማጥፋት በክፉ አድራጊዎች ላይ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 2:7-8

እርሱ ለቅኖች ትክክለኛ ጥበብ ያከማቻል፤ ያለ ነቀፋ ለሚሄዱትም ጋሻ ይሆናቸዋል፤ የፍትሕን መንገድ ይጠብቃል፤ የታማኞቹንም አካሄድ ያጸናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 4:18-19

“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እርሱ ቀብቶኛልና፤ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለታወሩትም ማየትን እንዳውጅ፣ የተጨቈኑትን ነጻ እንዳወጣ፣ የተወደደችውንም የጌታን ዓመት እንዳውጅ ልኮኛል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 17:2

ጽድቄ ከአንተ ዘንድ ይምጣ፤ ዐይኖችህም ፍትሕን ይዩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሐዋርያት ሥራ 17:31

በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ላይ በጽድቅ የሚፈርድበትን ቀን ወስኗልና፤ እርሱንም ከሙታን በማስነሣቱ ለሰዎች ሁሉ ይህን አረጋግጧል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር እውነተኛ እና ታማኝ፣ ልዑል ጌታ! አንተ ጻድቅ፣ ቅዱስ እና ከፍተኛ ውዳሴና አምልኮ የሚገባህ ስለሆንክ አመሰግንሃለሁ። ፈቃድህ ጻድቅ እንድንሆን ስለሆነ በኢየሱስ ስም ወደ አንተ እቀርባለሁ እና አመልክሃለሁ፤ የምዘራውን ሁሉ እ cosecharé ነው፤ ቃልህ «እግዚአብሔር ለተበደሉት ሁሉ ፍትሕንና ጽድቅን የሚያደርግ ነው» ይላል። ጌታ ሆይ፣ በዚህ በክፋትና በበደል በተሞላ ዘመን፣ ፍትሕን ለመፈጸም አስተምረኝ፣ ከሌሎች ጋር በትክክል እንድሠራ እርዳኝ፣ ሙሉ እምነቴን በአንተ ላይ ማድረግ እንድችል፣ አንተ ፈራጅ እና የእኔን ጉዳይ የምትከራከር እንደሆንክ እንዳውቅ እርዳኝ። ጌታ ሆይ፣ አንተ ብቻ ቸር፣ ጻድቅ እና ያለ ክፋት ስለሆንክ፣ እንደ አንተ ፍትሕ የለም። የተወደድክ አምላክ፣ እኔ ኃጢአተኛ እና የፍርድ ዕዳ ቢኖርብኝም፣ ለእኔ እና ያለ አድልዎ ለመላው ዓለም፣ አንድያ ልጅህን በመስቀል ላይ እንዲሞት አሳልፈህ ሰጥተሃል። ጌታ ሆይ፣ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ጉዳት ካደረሱብኝ ሰዎች ላይ የበቀል ስሜትን እና በክፋታቸው መደሰትን እንዳስወግድ እርዳኝ። በኢየሱስ ስም፣ አሜን!
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች