የገና በዓል እግዚአብሔር ልጁን ኢየሱስን ወደ ዓለም በመላክ ላሳየን ታላቅ ፍቅር ለማሰብ እጅግ በጣም ጥሩ ጊዜ ነው። ይህንንም መልእክትና ፍቅር ከእኛ ጋር ላሉት ለማካፈል ድንቅ ወቅት ነው።
ገና የክርስትና እምነት ከሚያከብራቸው በጣም አስፈላጊ በዓላት አንዱ መሆኑን እናስታውስ፤ ከትንሣኤና ከጰንጠቆስጤ በዓላት ጋር እኩል ነው፤ የኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም መወለድ። በዚህ ወቅት ባለን ነገር እና በምንሰማው ስሜት የበለጠ ንቁ እንሆናለን፤ እግዚአብሔር ዓመቱን ሙሉ ለሰጠን በረከቶች ሁሉ እናመስግን። "ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።" (ኢሳይያስ 9:6)
ይህ የገና በዓል የእግዚአብሔር ተስፋዎች በተለየ መንገድ እንድንኖር ያበረታቱን፤ በመስቀል ላይ የፈሰሰውን ደሙን ዋጋ እንድናደንቅ፣ ዓለማዊ ዝንባሌዎችን እንድንተው፣ የቸርነትና የልግስና መንፈስ በውስጣችን ያብብ፣ በፍቅር የበለፀገ እና በጥምቀት የተቀበልነውን ትዕግስት ሁሉ እንድንጠቀም ያድርገን። በሕይወት ውስጥ ቀጥ ብለን ለመቆም፣ በእግዚአብሔር ፊት ተንበርክከን መገኘት እንዳለብን እናስታውስ።
በንጉሡ በሄሮድስ ዘመን፣ ኢየሱስ በቤተ ልሔም ይሁዳ ከተወለደ በኋላ፣ ጠቢባን ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው፣ ኮከቡንም ሲያዩ ከመጠን በላይ ተደሰቱ። ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋራ አዩ፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት። ሣጥኖቻቸውን ከፍተው ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤም አቀረቡለት። እግዚአብሔርም ወደ ሄሮድስ እንዳይመለሱ በሕልም ባስጠነቀቃቸው መሠረት፣ መንገድ አሳብረው ወደ አገራቸው ተመለሱ። ጠቢባኑ ከሄዱ በኋላ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ፣ “ተነሥ! የምትመለስበትን ጊዜ እስካስታውቅህ ድረስ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ በመሸሽ በዚያ ቈይ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ይሻልና” አለው። ስለዚህም ዮሴፍ ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብጽ ሄደ፤ በዚያም ሄሮድስ እስከ ሞተበት ጊዜ ድረስ ኖረ። በዚህም፣ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት” በማለት ጌታ በነቢዩ አንደበት የተናገረው ቃል ተፈጸመ። ሄሮድስ ጠቢባኑ እንዳታለሉት በተረዳ ጊዜ በጣም ተናደደ። ከጠቢባኑ በተነገረው መሠረት፣ ዕድሜያቸው ሁለት ዓመትና ከዚያም በታች የሆኑትን የቤተ ልሔምንና የአካባቢዋን መንደሮች ወንድ ልጆች ሁሉ ልኮ አስገደለ። በዚህም በነቢዩ በኤርምያስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ፤ “የልቅሶና የታላቅ ዋይታ ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፤ መጽናናትም እንቢ አለች፤ ልጆቿ ዐልቀዋልና።” ሄሮድስ ከሞተ በኋላ የጌታ መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ፣ “የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው? በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንሰግድለት መጥተናልና” ሲሉ ጠየቁ።
መልአኩም እንዲህ አላት፤ “ማርያም ሆይ፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሞገስ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆ፤ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።
ዮሴፍም ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ፣ በገሊላ አውራጃ ከምትገኘው ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ የዳዊት ከተማ ወደሆነችው፣ ቤተ ልሔም ወደምትባል ከተማ ወደ ይሁዳ ወጣ። ሕፃኑም እያደገ፣ እየጠነከረም ሄደ፤ በጥበብ ተሞላ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በርሱ ላይ ነበረ። ወላጆቹም በየዓመቱ ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር። ልጁም ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ፣ እንደተለመደው ወደ በዓሉ ወጡ። በዓሉን ከፈጸሙ በኋላ፣ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀረ፤ ወላጆቹ ግን መቅረቱን አላወቁም ነበር። ዐብሯቸው ያለ መስሏቸው የአንድ ቀን መንገድ ተጓዙ፤ በኋላ ግን ከዘመዶቻቸውና ከወዳጆቻቸው ዘንድ ይፈልጉት ጀመር፤ ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ከሦስት ቀንም በኋላ፣ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲያደምጣቸውና ጥያቄ ሲያቀርብላቸው በቤተ መቅደስ ውስጥ አገኙት፤ የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ይደነቁ ነበር። ወላጆቹም ባዩት ጊዜ ተገረሙ፤ እናቱም፣ “ልጄ ሆይ፤ ለምን እንዲህ አደረግኸን? አባትህና እኔ እኮ ተጨንቀን ስንፈልግህ ነበር” አለችው። እርሱም፣ “ለምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት መገኘት እንደሚገባኝ አላወቃችሁምን?” አላቸው። ወደዚያም ለመመዝገብ የተጓዘው፣ የመውለጃ ጊዜዋ ከተቃረበው ከዕጮኛው ከማርያም ጋራ ነበር።
በዚያም እንዳሉ የምትወልድበት ጊዜ ደረሰ፤ የበኵር ልጇ የሆነውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ በጨርቅም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማረፊያ ቦታ ስላላገኙ በግርግም አስተኛችው።
መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፤ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑልም ኀይል ይጸልልሻል፤ ስለዚህ የሚወለደው ቅዱሱ ሕፃን፣ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል።
ወንድ ልጅ ትወልዳለች፤ ስሙንም ኢየሱስ ብለህ ትጠራዋለህ፤ ሕዝቡን ከኀጢአታቸው ያድናቸዋልና።” ጌታ በነቢዩ እንዲህ ሲል የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆነ፤ “እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ይሉታል፤” ትርጕሙም፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ” ማለት ነው።
መልአኩ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፤ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች አምጥቼላችኋለሁና። ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኅን ተወልዶላችኋልና፤ እርሱም ጌታ ክርስቶስ ነው።
ነገር ግን የተወሰነው ዘመን በደረሰ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን፣ ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ፤ ይህም የሆነው የልጅነትን መብት እናገኝ ዘንድ ከሕግ በታች ያሉትን ለመዋጀት ነው።
ጌታ በነቢዩ እንዲህ ሲል የተናገረው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆነ፤ “እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ይሉታል፤” ትርጕሙም፣ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ” ማለት ነው።
ሕፃን ተወልዶልናል፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል። ለመንግሥቱ ስፋት፣ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል።
ዮሴፍም ከዳዊት ቤትና ወገን ስለ ነበረ፣ በገሊላ አውራጃ ከምትገኘው ከናዝሬት ከተማ ተነሥቶ የዳዊት ከተማ ወደሆነችው፣ ቤተ ልሔም ወደምትባል ከተማ ወደ ይሁዳ ወጣ። ሕፃኑም እያደገ፣ እየጠነከረም ሄደ፤ በጥበብ ተሞላ፤ የእግዚአብሔርም ጸጋ በርሱ ላይ ነበረ። ወላጆቹም በየዓመቱ ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ይሄዱ ነበር። ልጁም ዐሥራ ሁለት ዓመት በሆነው ጊዜ፣ እንደተለመደው ወደ በዓሉ ወጡ። በዓሉን ከፈጸሙ በኋላ፣ ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ብላቴናው ኢየሱስ በኢየሩሳሌም ቀረ፤ ወላጆቹ ግን መቅረቱን አላወቁም ነበር። ዐብሯቸው ያለ መስሏቸው የአንድ ቀን መንገድ ተጓዙ፤ በኋላ ግን ከዘመዶቻቸውና ከወዳጆቻቸው ዘንድ ይፈልጉት ጀመር፤ ባጡትም ጊዜ እየፈለጉት ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። ከሦስት ቀንም በኋላ፣ በመምህራን መካከል ተቀምጦ ሲያደምጣቸውና ጥያቄ ሲያቀርብላቸው በቤተ መቅደስ ውስጥ አገኙት፤ የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ይደነቁ ነበር። ወላጆቹም ባዩት ጊዜ ተገረሙ፤ እናቱም፣ “ልጄ ሆይ፤ ለምን እንዲህ አደረግኸን? አባትህና እኔ እኮ ተጨንቀን ስንፈልግህ ነበር” አለችው። እርሱም፣ “ለምን ፈለጋችሁኝ? በአባቴ ቤት መገኘት እንደሚገባኝ አላወቃችሁምን?” አላቸው። ወደዚያም ለመመዝገብ የተጓዘው፣ የመውለጃ ጊዜዋ ከተቃረበው ከዕጮኛው ከማርያም ጋራ ነበር። እነርሱ ግን የተናገራቸው ነገር አልገባቸውም። ከዚያም ዐብሯቸው ወደ ናዝሬት ወረደ፤ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ሁሉ ነገር በልቧ ትጠብቀው ነበር። ኢየሱስም በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት አደገ። በዚያም እንዳሉ የምትወልድበት ጊዜ ደረሰ፤ የበኵር ልጇ የሆነውን ወንድ ልጅ ወለደች፤ በጨርቅም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማረፊያ ቦታ ስላላገኙ በግርግም አስተኛችው።
ድንገትም ብዙ የሰማይ ሰራዊት ከመልአኩ ጋራ ታዩ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፣ እንዲህ አሉ፤ “ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም፣ ሰላምም እርሱ ለሚወድዳቸው ሰዎች በምድር ይሁን!”
“አንቺ ግን፣ ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፤ ከይሁዳ ነገዶች መካከል ትንሿ ብትሆኚም፣ አመጣጡ ከጥንት፣ ከቀድሞ ዘመን የሆነ፣ የእስራኤል ገዥ፣ ከአንቺ ይወጣልኛል።”
የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት ታሪክ እንዲህ ነው፤ እናቱ ማርያም ለዮሴፍ ታጭታ ሳይገናኙ፣ በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች። ዕጮኛዋ ዮሴፍ ጻድቅ ሰው ስለ ነበርና ማርያምን በሰው ፊት ሊያጋልጣት ስላልፈለገ በስውር ሊተዋት ወሰነ።
መላእክቱ ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ ከወጡ በኋላ እረኞቹ፣ “ጌታ የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንድናይ ወደ ቤተ ልሔም እንሂድ” ተባባሉ። እነርሱም ፈጥነው ሄዱ፤ ማርያምንና ዮሴፍን፣ ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ።
ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ ውዳሴን አፍልቁ፤ በደስታና በዝማሬ አመስግኑ፤ ለእግዚአብሔር በገና ደርድሩለት፤ በበገናና በዝማሬ ድምፅ ዘምሩለት፤ በእንቢልታና በመለከት ድምፅ፣ በንጉሡ በእግዚአብሔር ፊት እልል በሉ።
ከእሴይ ግንድ ቍጥቋጥ ይወጣል፤ ከሥሮቹም አንዱ ቅርንጫፍ ፍሬ ያፈራል። በዚያም ቀን፣ የእሴይ ሥር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ አሕዛብ እርሱን ይፈልጋሉ፤ ማረፊያውም የከበረ ይሆናል። በዚያ ቀን፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደ ገና የተረፈውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦር፣ ከግብጽ፣ ከጳትሮስ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኤላም፣ ከባቢሎን፣ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል። ለመንግሥታት ምልክትን ያቆማል፤ ከእስራኤልም የተሰደዱትን መልሶ ያመጣቸዋል፤ የተበተኑትን የይሁዳ ሕዝብ፣ ከአራቱ የምድር ማእዘን ይሰበስባል። የኤፍሬም ምቀኛነት ያከትማል፤ የይሁዳ ጠላቶችም ይቈረጣሉ፤ ኤፍሬም በይሁዳ አይቀናም፤ ይሁዳም ኤፍሬምን አይጠላም። በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤም ተረተር ላይ ይወርዳሉ፤ ሁለቱም ተባብረው በምሥራቅ ያለውን ሕዝብ ይዘርፋሉ፤ በኤዶምና በሞዓብ ላይ እጃቸውን ያነሣሉ፤ አሞናውያንም ይገዙላቸዋል። እግዚአብሔር በሚጋረፍም ነፋስ፣ የግብጽን ባሕረ ሰላጤ ያደርቃል፤ እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ይዘረጋል፤ ሰባት ታናናሽ ጅረትም አድርጎ ይለያየዋል፤ ስለዚህ ሰዎች ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ። እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ እንደ ሆነው ሁሉ፣ ከአሦር ለተረፈው ቅሬታ ሕዝብ፣ እንዲሁ ጐዳና ይዘጋጅለታል። የእግዚአብሔር መንፈስ፣ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፣ የምክርና የኀይል መንፈስ፣ የዕውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
እነሆ፤ ትፀንሻለሽ፤ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። እርሱም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑል ልጅም ይባላል፤ ጌታ አምላክ የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ በያዕቆብም ቤት ላይ ለዘላለም ይነግሣል፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።”
ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፤ “ይህ ሕፃን በእስራኤል ለብዙዎች መውደቅና መነሣት ምክንያት እንዲሆን፣ ደግሞም ክፉ ለሚያስወሩበት ምልክት እንዲሆን ተወስኗል፤ የብዙዎችም የልብ ሐሳብ የተገለጠ እንዲሆን፣ የአንቺም ነፍስ ደግሞ በሰይፍ ይወጋል።”
ልጆቹ በሥጋና በደም እንደሚካፈሉ፣ እርሱ ራሱ ደግሞ ያንኑ ተካፈለ፤ ይኸውም በሞት ላይ ኀይል ያለውን ዲያብሎስን በሞቱ ኀይል እንዲደመስስ ነው፤ እንዲሁም በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ በሞት ፍርሀት ባርነት የታሰሩትን ነጻ እንዲያወጣ ነው።
ለእግዚአብሔር አዲስ ዝማሬ ዘምሩ፤ ምድር ሁሉ፤ ለእግዚአብሔር ዘምሩ። በሕዝቦች መካከል፣ “እግዚአብሔር ነገሠ” በሉ፤ ዓለም በጽኑ ተመሥርታለች፤ አትናወጥምም፤ እርሱ ለሕዝቦች በእኩልነት ይፈርዳል። ሰማያት ደስ ይበላቸው፤ ምድርም ሐሤት ታድርግ፤ ባሕርና በውስጧ ያለው ሁሉ ያስተጋባ፤ መስኩና በላዩ ያለው ሁሉ ይፈንጥዝ፤ ያን ጊዜ የዱር ዛፎች ሁሉ በደስታ ይዘምራሉ፤ እርሱ ይመጣልና በእግዚአብሔር ፊት ይዘምራሉ፤ በምድር ላይ ሊፈርድ ይመጣል፤ በዓለም ላይ በጽድቅ፣ በሕዝቦችም ላይ በእውነት ይፈርዳል። ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ስሙንም ባርኩ፤ ማዳኑንም ነጋ ጠባ አውሩ። ክብሩን ለአሕዛብ ተናገሩ፣ ድንቅ ሥራዎቹን ለሕዝቦች ሁሉ ንገሩ።
“የእስራኤል አምላክ፣ ጌታ ይመስገን፤ መጥቶ ሕዝቡን ተቤዥቷልና። በብላቴናው በዳዊት ቤት፣ የድነት ቀንድ አስነሥቶልናል፤ ይሁን እንጂ ኤልሳቤጥ መካን በመሆኗ ልጅ አልነበራቸውም፤ ሁለቱም በዕድሜ የገፉ ነበሩ። ይህም ጥንት በቅዱሳን ነቢያቱ አፍ እንደ ተናገረው፣
“ብርሃንሽ መጥቷልና ተነሺ አብሪ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻል። “ባዕዳን ቅጥሮችሽን ይሠራሉ፤ ነገሥታቶቻቸው ያገለግሉሻል፤ በቍጣዬ ብመታሽም፣ ርኅራኄዬን በፍቅር አሳይሻለሁ። በሮችሽ ምን ጊዜም የተከፈቱ ይሆናሉ፤ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቶ አይዘጉም፤ ይህም ሰዎች የመንግሥታትን ብልጽግና ወደ አንቺ እንዲያመጡ፣ ነገሥታታቸውም በድል ወደ አንቺ እንዲገቡ ነው። ለአንቺ የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፤ ፈጽሞም ይደመሰሳል። “የመቅደሴን ቦታ ለማስጌጥ፣ የሊባኖስ ክብር፣ ጥዱ፣ አስታውና ባርሰነቱ በአንድነት ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ እግሬ የሚያርፍበትንም ስፍራ አከብራለሁ። የአስጨናቂዎችሽ ወንዶች ልጆች እየሰገዱ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ እግርሽ ላይ ይደፋሉ፤ የእግዚአብሔር ከተማ፣ የእስራኤል ቅዱስ ገንዘብ የሆንሽው ጽዮን ብለው ይጠሩሻል። “የተተውሽና የተጠላሽ፣ ማንም ሰው የማያልፍብሽ ብትሆኝም እንኳ፣ እኔ የዘላለም ትምክሕት፣ የትውልድም ሁሉ ደስታ አደርግሻለሁ። የመንግሥታትን ወተት ትጠጪያለሽ፤ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽ፣ ቤዛሽም እኔ የያዕቆብ ኀያል እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ። በናስ ፈንታ ወርቅ፣ በብረትም ፈንታ ብር አመጣልሻለሁ። በዕንጨት ፈንታ ናስ በብረትም ፈንታ ድንጋይ አመጣልሻለሁ። ሰላምን ገዥሽ፣ ጽድቅንም አለቃሽ አደርጋለሁ። ከእንግዲህ በምድርሽ ሁከት፣ በጠረፎችሽም ጥፋትና መፈራረስ አይሰማም፤ ነገር ግን ቅጥሮችሽን ድነት፣ በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያቸዋለሽ። ከእንግዲህ በቀን የፀሓይ ብርሃን አያስፈልግሽም፤ በሌሊትም የጨረቃ ብርሃን አያበራልሽም፤ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃን፣ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና። እነሆ፤ ጨለማ ምድርን፣ ድቅድቅ ጨለማም ሕዝቦችን ይሸፍናል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ወጥቶልሻል፤ ክብሩንም ይገልጥልሻል። ፀሓይሽ ከእንግዲህ አትጠልቅም፤ ጨረቃሽም ብርሃን መስጠቷን አታቋርጥም፤ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናል፤ የሐዘንሽም ቀን ያከትማል። ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ ምድሪቱንም ለዘላለም ይወርሳሉ፤ ለክብሬ መግለጫ ይሆኑ ዘንድ፣ የእጆቼ ሥራ፣ እኔ የተከልኋቸው ቍጥቋጦች ናቸው። ከአንቺ ታናሽ የሆነው ሺሕ፣ ከሁሉም የመጨረሻው ታናሽ ኀያል መንግሥት ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ጊዜውም ሲደርስ ይህን በፍጥነት አደርጋለሁ።” ሕዝቦች ወደ ብርሃንሽ፣ ነገሥታትም ወደ ንጋትሽ ጸዳል ይመጣሉ።
ዮሴፍም ከእንቅልፉ ነቃ፤ ከዚያም የጌታ መልአክ እንዳዘዘው ማርያምን ወደ ቤቱ ወሰዳት። ይሁን እንጂ የበኵር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም፣ “ኢየሱስ” ብሎ ጠራው።
“ደግሞም አንተ ሕፃን ሆይ፤ የልዑል ነቢይ ትባላለህ፤ የጌታን መንገድ ለማዘጋጀት በፊቱ ትሄዳለህና፤ የኀጢአታቸውን ስርየት ከማግኘታቸው የተነሣ፤ ለሕዝቡ የመዳንን ዕውቀት ትሰጥ ዘንድ፣ ከአምላካችንም ጥልቅ ምሕረት የተነሣ፣ የንጋት ፀሓይ ከሰማይ ወጣችልን፤ ይኸውም በጨለማ ለሚኖሩት፣ በሞት ጥላ ውስጥም ላሉት እንዲያበራና፣ እግሮቻችንንም ወደ ሰላም መንገድ እንዲመራ ነው።”
ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን ከሰማያት አመስግኑት፤ በላይ በአርያም አመስግኑት። የዱር አራዊትና የቤት እንስሳት ሁሉ፣ በምድር የሚሳቡ ፍጥረታትና የሚበርሩ ወፎችም፣ የምድር ነገሥታትና ሕዝቦች ሁሉ፣ መሳፍንትና የምድር ገዦች ሁሉ፣ ወጣት ወንዶችና ደናግል፣ አረጋውያንና ልጆች ያመስግኑት። ስሙ ብቻውን ከፍ ያለ ነውና፣ ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ነውና፣ እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ። እርሱ ለሕዝቡ ቀንድን አስነሥቷል፤ ለቅዱሳኑ ሁሉ ምስጋና፣ እጅግ ቅርቡ ለሆነው ሕዝቡ፣ ለእስራኤል ልጆች። ሃሌ ሉያ። መላእክቱ ሁሉ አመስግኑት፤ ሰራዊቱ ሁሉ አመስግኑት፤ ፀሓይና ጨረቃ አመስግኑት፤ የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት። ሰማየ ሰማያት አመስግኑት፤ ከሰማያትም በላይ ያላችሁ ውሆች አወድሱት።
በዚያ ጊዜ ጻድቅና ትጉህ የሆነ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው በኢየሩሳሌም ይኖር ነበር፤ እርሱም የእስራኤልን መጽናናት የሚጠባበቅና መንፈስ ቅዱስ በላዩ ያደረ ሰው ነበር። ደግሞም የጌታን መሲሕ ሳያይ እንደማይሞት በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ነበር፤ እርሱም በዚህ ጊዜ በመንፈስ ተመርቶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ የልጁም ወላጆች በሕጉ ልማድ መሠረት ተገቢውን ሊፈጽሙለት ሕፃኑን ኢየሱስን ይዘው በገቡ ጊዜ፣ ስምዖን ተቀብሎ ዐቀፈው፤ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እንዲህ አለ፤ “ጌታ ሆይ፤ ቃል በገባኸው መሠረት፣ አሁን ባሪያህን በሰላም አሰናብተው፤ ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ለመመዝገብ ወደየራሱ ከተማ ሄደ። ዐይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን፣
እንግዲህ ከአብርሃም እስከ ዳዊት ዐሥራ አራት ትውልድ፣ ከዳዊት እስከ ባቢሎን ምርኮ ዐሥራ አራት ትውልድ፣ ከባቢሎን ምርኮ እስከ ክርስቶስ ልደት ዐሥራ አራት ትውልድ ይሆናል።
በፊቱ እንደ ቡቃያ፣ ከደረቅም መሬት እንደ ወጣ ሥር በቀለ፤ የሚስብ ውበት ወይም ግርማ የለውም፤ እንድንወድደውም የሚያደርግ መልክ አልነበረውም።
የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት፣ ግብር ያመጡለታል፤ የዐረብና የሳባ ነገሥታት፣ እጅ መንሻ ያቀርባሉ። ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ይገዙለታል።
“ ‘በይሁዳ ምድር የምትገኚው አንቺ ቤተ ልሔም፣ ከሌሎቹ ከይሁዳ ገዦች በምንም አታንሺም፤ የሕዝቤ የእስራኤል ጠባቂ የሚሆን፣ ከአንቺ ይወጣልና።’ ”
“ተነሣ፤ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ምድር ተመለስ፤ ሕፃኑን ለመግደል የሚሹት ሞተዋልና” አለው። ዮሴፍም ተነሥቶ ሕፃኑንና እናቱን በመያዝ ወደ እስራኤል ምድር ተመለሰ፤
ምድር ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፤ እግዚአብሔርን በደስታ አገልግሉት፤ በፍሥሓ ዝማሬ ፊቱ ቅረቡ። እግዚአብሔር አምላክ መሆኑን ዕወቁ፤ እርሱ ፈጠረን፤ እኛም የርሱ ነን፤ እኛ ሕዝቡ የማሰማሪያው በጎች ነን። በምስጋና ወደ ደጆቹ፣ በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፤ አመስግኑት፤ ስሙንም ባርኩ፤ እግዚአብሔር ቸር፣ ምሕረቱም ለዘላለም ነውና፤ ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።
እርሱም፣ “ባሪያዬ መሆንህ፣ የያዕቆብን ነገዶች እንደ ገና መመለስህ፣ የጠበቅኋቸውን እስራኤል መልሰህ ማምጣት ለአንተ ቀላል ነገር ነው፤ ድነቴን እስከ ምድር ዳርቻ እንድታመጣ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አደርግሃለሁ” አለኝ።
ከዚያም ሄሮድስ ጠቢባኑን በምስጢር አስጠርቶ በማነጋገር ኮከቡ የታየበትን ትክክለኛ ጊዜ ተረዳ። ጠቢባኑንም ወደ ቤተ ልሔም ልኮ፣ “ሂዱና ሕፃኑን ፈልጉ፤ እኔም ደግሞ ሄጄ እንድሰግድለት፣ እንዳገኛችሁት ወደ እኔ ተመልሳችሁ የት እንዳለ ንገሩኝ” አላቸው።
ኀያል የሆነው እርሱ ታላቅ ነገር አድርጎልኛልና፤ ስሙም ቅዱስ ነው፤ በይሁዳ ንጉሥ በሄሮድስ ዘመን፣ ከአብያ የክህነት ምድብ የሆነ ዘካርያስ የሚባል አንድ ካህን ነበረ፤ ሚስቱም ከአሮን ነገድ ስትሆን፣ ስሟም ኤልሳቤጥ ነበረ። ምሕረቱም ለሚፈሩት ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል።
ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ፣ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ፤ ሰው ሆኖ ተገልጦም፣ ራሱን ዝቅ አደረገ፤ እስከ ሞት፣ ያውም በመስቀል ላይ እስከ መሞት ድረስ ታዛዥ ሆነ።
የግመል መንጋ፣ የምድያምና የጌፌር ግልገል ግመሎች ምድርሽን ይሞላሉ፤ ወርቅና ዕጣን ይዘው፣ የእግዚአብሔርን ምስጋና እያወጁ፣ ሁሉም ከሳባ ይመጣሉ።
ዐይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን፣ ማዳንህን አይተዋልና። ይህም ለአሕዛብ መገለጥን የሚሰጥ ብርሃን፣ ለሕዝብህ ለእስራኤልም ክብር ነው።”
ሁላችሁም በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ፤ ከክርስቶስ ጋራ አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁላችሁ ክርስቶስን ለብሳችሁታልና።
በዚያ ዘመን፣ የዓለሙ ሁሉ ሕዝብ እንዲቈጠርና እንዲመዘገብ ከአውግስጦስ ቄሳር ትእዛዝ ወጣ። መልአኩ ግን እንዲህ አላቸው፤ “አትፍሩ፤ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች አምጥቼላችኋለሁና። ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኅን ተወልዶላችኋልና፤ እርሱም ጌታ ክርስቶስ ነው። ይህ ምልክት ይሁናችሁ፤ ሕፃን ልጅ በጨርቅ ተጠቅልሎ በግርግም ተኝቶ ታገኛላችሁ።” ድንገትም ብዙ የሰማይ ሰራዊት ከመልአኩ ጋራ ታዩ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገኑ፣ እንዲህ አሉ፤ “ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም፣ ሰላምም እርሱ ለሚወድዳቸው ሰዎች በምድር ይሁን!” መላእክቱ ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ ከወጡ በኋላ እረኞቹ፣ “ጌታ የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንድናይ ወደ ቤተ ልሔም እንሂድ” ተባባሉ። እነርሱም ፈጥነው ሄዱ፤ ማርያምንና ዮሴፍን፣ ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ። ካዩም በኋላ፣ ስለ ሕፃኑ የተነገራቸውን ገልጠው አወሩ። ይህንም የሰሙ ሁሉ እረኞቹ በነገሯቸው ነገር ተደነቁ፤ ማርያም ግን ይህን ሁሉ ነገር በልቧ ይዛ ታሰላስል ነበር። ይህም ቄሬኔዎስ የሶርያ ገዥ በነበረበት ጊዜ የተደረገ የመጀመሪያው የሕዝብ ቈጠራ ነበር። እረኞቹም ሁሉም ነገር እንደ ተነገራቸው ሆኖ በማግኘታቸው፣ ስለ ሰሙትና ስላዩት ሁሉ እግዚአብሔርን እያከበሩና እያመሰገኑ ተመለሱ። ስምንት ቀን ሆኖት የመገረዣ ጊዜው ሲደርስ፣ ከመፀነሱ በፊት መልአኩ ባወጣለት ስም ኢየሱስ ተባለ። በሙሴ ሕግ መሠረት የመንጻታቸው ወቅት በተፈጸመ ጊዜ፣ ዮሴፍና ማርያም ሕፃኑን ለጌታ ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም ይዘውት ወጡ፤ ይኸውም በጌታ ሕግ፣ “ተባዕት የሆነ በኵር ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይሆናል” ተብሎ እንደ ተጻፈ ለመፈጸምና ደግሞም በጌታ ሕግ፣ “ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች እንደ ተባለ፣” መሥዋዕት ለማቅረብ ነበር። በዚያ ጊዜ ጻድቅና ትጉህ የሆነ ስምዖን የሚባል አንድ ሰው በኢየሩሳሌም ይኖር ነበር፤ እርሱም የእስራኤልን መጽናናት የሚጠባበቅና መንፈስ ቅዱስ በላዩ ያደረ ሰው ነበር። ደግሞም የጌታን መሲሕ ሳያይ እንደማይሞት በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ነበር፤ እርሱም በዚህ ጊዜ በመንፈስ ተመርቶ ወደ ቤተ መቅደስ ገባ፤ የልጁም ወላጆች በሕጉ ልማድ መሠረት ተገቢውን ሊፈጽሙለት ሕፃኑን ኢየሱስን ይዘው በገቡ ጊዜ፣ ስምዖን ተቀብሎ ዐቀፈው፤ እግዚአብሔርን እያመሰገነ እንዲህ አለ፤ “ጌታ ሆይ፤ ቃል በገባኸው መሠረት፣ አሁን ባሪያህን በሰላም አሰናብተው፤ ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው ለመመዝገብ ወደየራሱ ከተማ ሄደ።
ነገር ግን እርሱ ስለ መተላለፋችን ተወጋ፤ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ በርሱ ላይ የወደቀው ቅጣት ለእኛ ሰላም አመጣልን፤ በርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
ምሕረቱን በማስታወስ፣ ብላቴናውን እስራኤልን ረድቷል፤ ይህም ለአባቶቻችን እንደ ተናገረ፣ ለአብርሃምና ለዘሩ ያለውን ለዘላለም ለመጠበቅ ነው።”
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድኾች ወንጌልን እንድሰብክ፣ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና። ልባቸው የተሰበረውን እንድጠግን፣ ለምርኮኞች ነጻነትን፣ ለእስረኞች መፈታትን እንዳውጅ ልኮኛል።
እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። የግብጽን በኵር የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። እስራኤልን ከመካከላቸው ያወጣ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤ በኀያል እጅና በተዘረጋች ክንድ ይህን ያደረገ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ቀይ ባሕር ለሁለት የከፈለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። እስራኤልን በመካከሉ ያሳለፈ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ፈርዖንንና ሰራዊቱን በቀይ ባሕር ያሰጠመ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ሕዝቡን በምድረ በዳ የመራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ታላላቅ ነገሥታትን የመታ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ኀያላን ነገሥታትን የገደለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። የአሞራውያንን ንጉሥ ሴዎንን የገደለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። የባሳንን ንጉሥ ዐግን የገደለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ምድራቸውን ርስት አድርጎ የሰጠ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ለባሪያው ለእስራኤል ርስት አድርጎ የሰጠ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። በውርደታችን ጊዜ ያሰበን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ከጠላቶቻችን እጅ ያዳነን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። ለፍጡር ሁሉ ምግብን የሚሰጥ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። የጌቶችን ጌታ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
በተራሮች ላይ የቆሙ፣ የምሥራችን የሚያመጡ እግሮች፣ ሰላምን የሚናገሩ፣ መልካም ዜና የሚያበሥሩ፣ ድነትን የሚያውጁ፣ ጽዮንንም፣ “አምላክሽ ነግሧል!” የሚሉ እንዴት ያማሩ ናቸው።
በዚህ ሐሳብ ሳለ፣ የጌታ መልአክ በሕልም ተገለጠለት፤ እንዲህም አለው፤ “የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ፤ ዕጮኛህን ማርያምን ወደ ቤትህ ለመውሰድ አትፍራ፤ የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ነውና።
ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን ከሰማያት አመስግኑት፤ በላይ በአርያም አመስግኑት። የዱር አራዊትና የቤት እንስሳት ሁሉ፣ በምድር የሚሳቡ ፍጥረታትና የሚበርሩ ወፎችም፣ የምድር ነገሥታትና ሕዝቦች ሁሉ፣ መሳፍንትና የምድር ገዦች ሁሉ፣ ወጣት ወንዶችና ደናግል፣ አረጋውያንና ልጆች ያመስግኑት። ስሙ ብቻውን ከፍ ያለ ነውና፣ ክብሩም ከምድርና ከሰማይ በላይ ነውና፣ እነዚህ ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑ። እርሱ ለሕዝቡ ቀንድን አስነሥቷል፤ ለቅዱሳኑ ሁሉ ምስጋና፣ እጅግ ቅርቡ ለሆነው ሕዝቡ፣ ለእስራኤል ልጆች። ሃሌ ሉያ። መላእክቱ ሁሉ አመስግኑት፤ ሰራዊቱ ሁሉ አመስግኑት፤ ፀሓይና ጨረቃ አመስግኑት፤ የምታበሩ ከዋክብት ሁሉ አመስግኑት። ሰማየ ሰማያት አመስግኑት፤ ከሰማያትም በላይ ያላችሁ ውሆች አወድሱት። እርሱ ስላዘዘ ተፈጥረዋልና፣ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑት።
እናንተን ባስታወስሁ ቍጥር አምላኬን አመሰግናለሁ። ቀድሞ እንዳያችሁትና አሁንም በእኔ እንዳለ በምትሰሙት በዚያው ዐይነት ተጋድሎ እናንተም እያለፋችሁ ነውና። ሁልጊዜ ስለ ሁላችሁ ስጸልይ፣ በደስታ እጸልያለሁ፤ ከመጀመሪያው ቀን አንሥቶ እስካሁን ድረስ በወንጌል አገልግሎት ተካፋይ ሆናችኋልና።
“ብርሃንሽ መጥቷልና ተነሺ አብሪ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻል። “ባዕዳን ቅጥሮችሽን ይሠራሉ፤ ነገሥታቶቻቸው ያገለግሉሻል፤ በቍጣዬ ብመታሽም፣ ርኅራኄዬን በፍቅር አሳይሻለሁ። በሮችሽ ምን ጊዜም የተከፈቱ ይሆናሉ፤ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቶ አይዘጉም፤ ይህም ሰዎች የመንግሥታትን ብልጽግና ወደ አንቺ እንዲያመጡ፣ ነገሥታታቸውም በድል ወደ አንቺ እንዲገቡ ነው። ለአንቺ የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፤ ፈጽሞም ይደመሰሳል። “የመቅደሴን ቦታ ለማስጌጥ፣ የሊባኖስ ክብር፣ ጥዱ፣ አስታውና ባርሰነቱ በአንድነት ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ እግሬ የሚያርፍበትንም ስፍራ አከብራለሁ። የአስጨናቂዎችሽ ወንዶች ልጆች እየሰገዱ ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ የናቁሽም ሁሉ እግርሽ ላይ ይደፋሉ፤ የእግዚአብሔር ከተማ፣ የእስራኤል ቅዱስ ገንዘብ የሆንሽው ጽዮን ብለው ይጠሩሻል። “የተተውሽና የተጠላሽ፣ ማንም ሰው የማያልፍብሽ ብትሆኝም እንኳ፣ እኔ የዘላለም ትምክሕት፣ የትውልድም ሁሉ ደስታ አደርግሻለሁ። የመንግሥታትን ወተት ትጠጪያለሽ፤ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽ፣ ቤዛሽም እኔ የያዕቆብ ኀያል እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ። በናስ ፈንታ ወርቅ፣ በብረትም ፈንታ ብር አመጣልሻለሁ። በዕንጨት ፈንታ ናስ በብረትም ፈንታ ድንጋይ አመጣልሻለሁ። ሰላምን ገዥሽ፣ ጽድቅንም አለቃሽ አደርጋለሁ። ከእንግዲህ በምድርሽ ሁከት፣ በጠረፎችሽም ጥፋትና መፈራረስ አይሰማም፤ ነገር ግን ቅጥሮችሽን ድነት፣ በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያቸዋለሽ። ከእንግዲህ በቀን የፀሓይ ብርሃን አያስፈልግሽም፤ በሌሊትም የጨረቃ ብርሃን አያበራልሽም፤ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃን፣ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና። እነሆ፤ ጨለማ ምድርን፣ ድቅድቅ ጨለማም ሕዝቦችን ይሸፍናል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ወጥቶልሻል፤ ክብሩንም ይገልጥልሻል።
ከአምላካችንም ጥልቅ ምሕረት የተነሣ፣ የንጋት ፀሓይ ከሰማይ ወጣችልን፤ ይኸውም በጨለማ ለሚኖሩት፣ በሞት ጥላ ውስጥም ላሉት እንዲያበራና፣ እግሮቻችንንም ወደ ሰላም መንገድ እንዲመራ ነው።”
ማርያምም እንዲህ አለች፤ “ነፍሴ ጌታን ከፍ ከፍ ታደርገዋለች፤ መንፈሴም በመድኀኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ትሠኛለች፤ እርሱ የባሪያውን መዋረድ ተመልክቷልና። ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ምስጉን ይሉኛል፤
ሕፃን ተወልዶልናል፤ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል። ስሙም፣ ድንቅ መካር፣ ኀያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም ልዑል ይባላል።