Biblia Todo Logo
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
- ማስታወቂያዎች -


ስለ ሰላም ጥቅሶች

ስለ ሰላም ጥቅሶች

ይህ ዓለም በብጥብጥ የተሞላ ቢሆንም፣ የዕለት ተዕለት ሕይወታችሁም በጭንቀትና በግርግር የተወጠረ ቢሆንም፣ እግዚአብሔር ከማስተዋል ሁሉ የሚበልጥ ሰላም እንደሚሰጣችሁ ቃል ገብቷል። እንደ እግዚአብሔር ልጆች በየቀኑ ይህንን ሰላም መፈለግና የእርሱን ፍቅር ለሌሎች ማሳየት ይገባናል።

በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ብንሆንም ሰላማችንን እንድንጠብቅ እግዚአብሔር ጠርቶናል። በእግዚአብሔር መታመን ይህንን ሰላም እንድናገኝ ይረዳናል። ቃሉ በኢሳይያስ 26:3 «ሀሳቡን በአንተ ላይ የሚያኖረውን በፍጹም ሰላም ትጠብቀዋለህ፤ በአንተ ስለሚታመን» ይላል።

በእግዚአብሔር ታመኑ ዘንድ ታዘዋል። በመከራና በጭንቀት ጊዜ ይህ ከባድ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እምነታችሁን በሰማያዊው አባታችሁ ላይ ካኖራችሁ ሰላምን ይሰጣችኋል። እግዚአብሔር ዓለምን አሸንፏልና አትፍሩ። ሁሉም ነገር በእጁ ነው፤ እርሱም ያስባልሻል።


መዝሙር 46:10

“ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 30:15

የእስራኤል ቅዱስ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በመመለስና በማረፍ ትድናላችሁ፤ በጸጥታና በመታመን ትበረታላችሁ፤ እናንተ ግን ይህን አላደረጋችሁም፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 11:28-30

“እናንተ ሸክም የከበዳችሁና የደከማችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋለሁ። ቀንበሬን ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ በልቤ የዋህና ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ “ይመጣል ተብሎ የሚጠበቀው አንተ ነህ? ወይስ ሌላ እንጠብቅ?” ሲል ጠየቀ። ቀንበሬ ልዝብ፣ ሸክሜም ቀላል ነውና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 62:1-2

ነፍሴ ዕረፍት የምታገኘው በእግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ድነቴም የሚመጣልኝ ከርሱ ዘንድ ነው። በዝርፊያ አትታመኑ፤ በቅሚያም ተስፋ አታድርጉ፤ በዚህ ብትበለጽጉም፣ ልባችሁ ይህን አለኝታ አያድርግ። እግዚአብሔር አንድ ነገር ተናገረ፤ እኔም ይህን ሁለት ጊዜ ሰማሁ፤ ኀይል የእግዚአብሔር ነው። ጌታ ሆይ፤ ምሕረትም የአንተ ነው፤ አንተ ለእያንዳንዱ፣ እንደ ሥራው ትከፍለዋለህ። ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ ከቶም አልናወጥም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሰቈቃወ 3:25-26

እርሱን ተስፋ ለሚያደርጉት፣ ለሚፈልገውም ሰው እግዚአብሔር መልካም ነው። ሰው የእግዚአብሔርን ማዳን፣ ዝም ብሎ ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 32:17-18

የጽድቅ ፍሬ ሰላም፣ የጽድቅ ውጤትም ጸጥታና ለዘላለም ያለ ሥጋት ይሆናል። ሕዝቤ ሰላማዊ በሆነ መኖሪያ፣ በሚያስተማምን ቤት፣ ጸጥ ባለም ስፍራ ዐርፎ ይኖራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:7

በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግሥትም ተጠባበቀው፤ መንገዱ በተቃናለት፣ ክፋትንም በሚሸርብ ሰው ልብህ አይሸበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘፀአት 14:14

እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፤ እናንተ ያለባችሁ መታገሥ ብቻ ነው።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 4:8

በሰላም እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ያለ ሥጋት የምታሳድረኝ አንተ ብቻ ነህና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 26:3

በአንተ ላይ ታምናለችና፣ በአንተ የምትደገፈውን ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:27

ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጣችሁ አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፤ አይፍራም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 4:6-7

በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ፣ ከምስጋናም ጋራ ልመናችሁን በእግዚአብሔር ፊት አቅርቡ እንጂ ስለ ማንኛውም ነገር አትጨነቁ። ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም፣ ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 23:2-3

በለመለመ መስክ ያሳርፈኛል፤ በዕረፍት ውሃ ዘንድ ይመራኛል፤ ነፍሴንም ይመልሳታል። ስለ ስሙም፣ በጽድቅ መንገድ ይመራኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 131:2

ነገር ግን ነፍሴን ጸጥ፣ ዝም አሠኘኋት፤ ጡት የጣለ ልጅ ዐርፎ እናቱ ላይ እንደሚቀመጥ፣ ነፍሴ ጡት እንዳስተዉት ሕፃን በውስጤ ጸጥ አለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ነገሥት 19:11-12

እግዚአብሔርም፣ “እግዚአብሔር በዚያ ያልፋልና ወደ ተራራው ወጥተህ በእግዚአብሔር ፊት ቁም” አለው። ከዚያም ታላቅና ኀይለኛ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጣጠቀ፤ ዐለቶችንም በእግዚአብሔር ፊት ብትንትናቸውን አወጣ፤ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፤ ከነፋሱም ቀጥሎ የምድር መነዋወጥ ሆነ፤ እግዚአብሔር ግን በምድር መነዋወጡ ውስጥ አልነበረም። ከምድር መነዋወጡም ቀጥሎ እሳት መጣ፤ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም፤ ከእሳቱም ቀጥሎ ለስለስ ያለ ድምፅ ተሰማ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 91:1

በልዑል መጠጊያ የሚኖር፣ በሁሉን ቻይ አምላክ ጥላ ሥር ያድራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 40:31

እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን፣ ኀይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፤ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፤ አይደክሙም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 27:4-5

እግዚአብሔርን አንዲት ነገር እለምነዋለሁ፤ እርሷንም እሻለሁ፤ ይኸውም በሕይወቴ ዘመን ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፣ የእግዚአብሔርን ክብር ውበት አይ ዘንድ፣ በመቅደሱም ሆኜ አሰላስል ዘንድ ነው። በመከራ ቀን፣ በድንኳኑ ውስጥ ይሰውረኛልና፤ በተቀደሰ ድንኳኑም ውስጥ ይሸሽገኛል፤ በዐለቱ ላይ ከፍ ያደርገኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 3:24

ስትተኛ አትፈራም፤ ትተኛለህ እንቅልፍህም ጣፋጭ ይሆናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 63:6

በመኝታዬ ዐስብሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ስለ አንተ አሰላስላለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 41:10

እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና አትፍራ፤ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ። አበረታሃለሁ፤ እረዳሃለሁ፤ በጽድቄም ቀኝ እጄ ደግፌ እይዝሃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 5:7

እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በርሱ ላይ ጣሉት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 55:22

የከበደህን ነገር በእግዚአብሔር ላይ ጣል፤ እርሱ ደግፎ ይይዝሃል፤ የጻድቁንም መናወጥ ከቶ አይፈቅድም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:6

አንተ ግን ስትጸልይ ወደ ክፍልህ ግባ፤ በሩንም ዘግተህ በስውር ወዳለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የተደረገውን የሚያይ አባትህም ዋጋህን ይከፍልሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማርቆስ 6:31

ብዙ ሰዎች ይመጡና ይሄዱ ስለ ነበር ምግብ እንኳ ለመብላት ጊዜ ስላልነበራቸው፣ “እስኪ ብቻችሁን ከእኔ ጋራ ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራ እንሂድና ጥቂት ዕረፉ” አላቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 5:16

ኢየሱስ ግን ብዙ ጊዜ ወደ ገለልተኛ ስፍራ ወጥቶ ይጸልይ ነበር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢዮብ 6:24

“አስተምሩኝ፤ እኔም ዝም እላለሁ፤ ምኑ ላይ እንደ ተሳሳትሁ ጠቍሙኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:165

ሕግህን የሚወድዱ ብዙ ሰላም አላቸው፤ ዕንቅፋትም የለባቸውም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 55:12

በደስታ ትወጣላችሁ፤ በሰላምም ትሸኛላችሁ፤ ተራሮችና ኰረብቶች፣ በፊታችሁ በእልልታ ይዘምራሉ፤ የሜዳ ዛፎች ሁሉ፣ ያጨበጭባሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:6

የሥጋን ነገር ማሰብ ሞት ነው፤ የመንፈስን ነገር ማሰብ ግን ሕይወትና ሰላም ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 25:4-5

እግዚአብሔር ሆይ፤ አካሄድህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ መንገድህንም አስተምረኝ። አንተ አዳኜ፣ አምላኬም ነህና፣ በእውነትህ ምራኝ፤ አስተምረኝም፤ ቀኑን ሙሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 29:13

እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፤ በፍጹም ልባችሁም ከፈለጋችሁኝ ታገኙኛላችሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:15-16

ድንጋጌህን አሰላስላለሁ፤ ልቤን በመንገድህ ላይ ጥያለሁ። ደባ የሚያውጠነጥኑ ወደ እኔ ቀርበዋል፤ ከሕግህ ግን የራቁ ናቸው። እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ግን ቅርብ ነህ፤ ትእዛዞችህም ሁሉ እውነት ናቸው። ለዘላለም እንደ መሠረትሃቸው፣ ከጥንት ምስክርነትህ ተረድቻለሁ። ሕግህን አልረሳሁምና፣ ሥቃዬን ተመልከት፤ ታደገኝም። ተሟገትልኝ፤ አድነኝም፤ እንደ ቃልህም ሕያው አድርገኝ። ሥርዐትህን ስለማይሹ፣ ድነት ከክፉዎች የራቀ ነው። እግዚአብሔር ሆይ፤ ርኅራኄህ ታላቅ ነው፤ እንደ ሕግህ ሕያው አድርገኝ። የሚያሳድዱኝ ጠላቶቼ ብዙዎች ናቸው፤ እኔ ግን ከምስክርህ ዘወር አላልሁም። ቃልህን አይጠብቁምና፣ ከዳተኞችን አይቼ አርቃቸዋለሁ። መመሪያህን እንዴት እንደምወድድ ተመልከት፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ምሕረትህ ሕያው አድርገኝ። በሥርዐትህ ደስ ይለኛል፤ ቃልህንም አልዘነጋም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 50:4

ልዑል እግዚአብሔር የተባ አንደበት ሰጥቶኛል፤ ስለዚህ ደካሞችን ብርቱ ለማድረግ ምን ማለት እንዳለብኝ ዐውቃለሁ፤ በየማለዳው ያነቃኛል፤ በመማር ላይ እንዳለ ተማሪ ለመስማት ጆሮዬን ያነቃዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 46:1-2

አምላካችን መጠጊያችንና ኀይላችን፣ በሚደርስብን መከራ ሁሉ የቅርብ ረዳታችን ነው። “ዕረፉ፤ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ ዕወቁ፤ በሕዝቦች ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፤ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።” የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤ የያዕቆብም አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ ስለዚህ ምድር ብትነዋወጥ እንኳ፣ ተራሮችም ወደ ባሕር ጥልቅ ቢሰምጡ አንፈራም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 18:10

የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ በመሮጥ ተገን ያገኝበታል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:114

አንተ መጠጊያዬና ጋሻዬ ነህ፤ ቃልህን በተስፋ እጠብቃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 14:33

እግዚአብሔር የሰላም አምላክ እንጂ የሁከት አምላክ አይደለም። በቅዱሳን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እንዲሁ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 12:2

እነሆ፣ አምላክ ድነቴ ነው፤ እታመናለሁ፣ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ ድነቴም ሆኗል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 15:13

በርሱ በመታመናችሁ የተስፋ አምላክ ደስታንና ሰላምን ሁሉ ይሙላባችሁ፤ ይኸውም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል ተስፋ ተትረፍርፎ እንዲፈስስላችሁ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 107:29-30

ዐውሎ ነፋሱን ጸጥ አደረገ፤ የባሕሩም ሞገድ ረጭ አለ። ከምሥራቅና ከምዕራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ፣ ከየአገሩ የሰበሰባቸው እንዲህ ይናገሩ። ጸጥ በማለቱም ደስ አላቸው፤ ወዳሰቡትም ወደብ አደረሳቸው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:14

ከክፉ ሽሽ፤ መልካሙንም አድርግ፤ ሰላምን ፈልጋት፤ ተከተላትም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 2:14

ሁለቱን አንድ ያደረገ፣ የሚለያየውንም የጥል ግድግዳ ያፈረሰ ሰላማችን እርሱ ራሱ ነውና፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 29:11

እግዚአብሔር ለሕዝቡ ብርታትን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ተሰሎንቄ 3:16

የሰላም ጌታ ራሱ በሁሉም ነገር ዘወትር ሰላም ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋራ ይሁን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 4:8

በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፤ እውነት የሆነውን ሁሉ፣ ክቡር የሆነውን ሁሉ፣ ትክክል የሆነውን ሁሉ፣ ንጹሕ የሆነውን ሁሉ፣ ተወዳጅ የሆነውን ሁሉ፣ መልካም የሆነውን ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን ወይም ምስጋና እንደ እነዚህ ስላሉት ነገሮች አስቡ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:5-6

ራሳችሁን ከፍቅረ ንዋይ ጠብቁ፤ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር፣ “ከቶ አልተውህም፤ በፍጹም አልጥልህም” ብሏል። ስለዚህ በሙሉ ልብ፣ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም፤ ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” እንላለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 16:7

የሰው መንገድ እግዚአብሔርን ደስ ሲያሠኘው፣ ጠላቶቹ እንኳ ዐብረውት በሰላም እንዲኖሩ ያደርጋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:18

ቢቻላችሁስ በበኩላችሁ ከሰው ሁሉ ጋራ በሰላም ኑሩ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 32:7

አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከመከራ ትጠብቀኛለህ፤ በድል ዝማሬም ትከብበኛለህ። ሴላ

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 26:12

እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ሰላምን መሠረትህልን፤ የሠራነውንም ሁሉ አንተ አከናወንህልን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 85:8

እግዚአብሔር አምላክ የሚናገረውን እሰማለሁ፤ ለሕዝቡ፣ ለቅዱሳኑ ሰላምን ይናገራልና፤ ዳሩ ግን ወደ ከንቱ ምግባራቸው አይመለሱ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:9

ሰላምን የሚያወርዱ ብፁዓን ናቸው፤ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለው ይጠራሉና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 94:12-13

ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የምትገሥጸው፣ ከሕግህም የምታስተምረው ሰው፤ ለኀጢአተኞች ጕድጓድ እስኪማስላቸው ድረስ፣ እርሱን ከመከራ ታሳርፈዋለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 57:2

በቅንነት የሚሄዱ፣ ሰላም ይሆንላቸዋል፤ መኝታቸው ላይ ያርፋሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 3:2

ቀኖችን ይጨምሩልሃል፤ ዓመቶችንም ያረዝሙልሃል፤ ሕይወት፣ ሀብትንና ሰላምን ያበዙልሃል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 55:6

እኔም እንዲህ አልሁ፤ “ምነው የርግብ ክንፍ በኖረኝ! በርሬ በሄድሁና ባረፍሁ ነበር፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 35:4

የሚፈራ ልብ ላላቸው እንዲህ በሉ፤ “በርቱ፤ አትፍሩ፤ አምላካችሁ ይመጣል፤ ሊበቀል ይመጣል፤ እርሱም ብድራቱን ይዞ፣ ሊያድናችሁ ይመጣል።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:17

ጻድቃን ሲጮኹ፣ እግዚአብሔር ይሰማቸዋል፤ ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 61:2-4

ልቤ በዛለ ጊዜ፣ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ። አንተ መጠጊያዬ፣ ከጠላትም የምተገንብህ ጽኑ ግንብ ሆነኸኛልና። በድንኳንህ ለዘላለም ልኑር፤ በክንፎችህም ጥላ ልከለል። ሴላ

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 40:29

ለደከመው ብርታት ይሰጣል፤ ለዛለው ጕልበት ይጨምራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 31:25

የዛለችውን ነፍስ ዐድሳለሁ፤ የደከመችውንም አበረታለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:50

ቃልህ ሕያው ያደርገኛልና፣ ይህች በመከራዬ መጽናኛዬ ናት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 1:3-4

የርኅራኄ አባት፣ የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። እኛ ራሳችን ከእግዚአብሔር በተቀበልነው መጽናናት፣ በመከራ ያሉትን ማጽናናት እንድንችል፣ እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 147:3

ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል፤ ቍስላቸውንም ይጠግናል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 16:33

“በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ ይህን ነግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዟችሁ! እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 94:19

የውስጤ ጭንቀት በበዛ መጠን፣ ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 43:2

በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው፣ አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣ አያቃጥልህም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 23:4

በሞት ጥላ ሸለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ፣ አንተ ከእኔ ጋራ ስለ ሆንህ፣ ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ፣ እነርሱ ያጽናኑኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 51:3

እግዚአብሔር ጽዮንን በርግጥ ያጽናናታል፤ ፍርስራሾቿንም በርኅራኄ ይመለከታል፤ ምድረ በዳዋን እንደ ዔድን፣ በረሓዋንም እንደ እግዚአብሔር ተክል ቦታ ያደርጋል፤ ተድላና ደስታ፣ ምስጋናና የዝማሬ ድምፅ በርሷ ይገኛሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 40:1-2

አጽናኑ፤ ሕዝቤን አጽናኑ፤ ይላል አምላካችሁ። እነሆ፤ ጌታ እግዚአብሔር በኀይል ይመጣል፤ ክንዱ ስለ እርሱ ይገዛል። እነሆ፤ ዋጋው ከርሱ ጋራ ነው፤ የሚከፍለውም ብድራት ዐብሮት አለ። መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፤ ጠቦቶቹን በክንዱ ይሰበስባል፤ በዕቅፉም ይይዛቸዋል፤ የሚያጠቡትንም በጥንቃቄ ይመራል። ውሆችን በዕፍኙ የሰፈረ፣ ሰማያትን በስንዝሩ የለካ፣ የምድርን ዐፈር በመስፈሪያ ሰብስቦ የያዘ፣ ተራሮችን በሚዛን፣ ኰረብቶችንም በመድሎት የመዘነ ማነው? የእግዚአብሔርን መንፈስ የተረዳ፣ አማካሪውስ ሆኖ ያስተማረው ማን ነው? ዕውቀት ለማግኘት እግዚአብሔር ማንን አማከረ? ትክክለኛውንስ መንገድ ማን አስተማረው? ዕውቀትን ያስተማረው፣ የማስተዋልንም መንገድ ያሳየው ማን ነበር? እነሆ፤ አሕዛብ በገንቦ ውስጥ እንዳለች ጠብታ ናቸው፤ በሚዛን ላይ እንዳለ ትቢያ ይቈጠራሉ፤ ደሴቶችንም እንደ ደቃቅ ዐፈር ይመዝናቸዋል። ሊባኖስ ለመሠዊያ እሳት አትበቃም፤ የእንስሶቿም ቍጥር ለሚቃጠል መሥዋዕት ያንሳል። አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንደ ኢምንት ናቸው፤ ከምንም የማይቈጠሩ መና ናቸው። እንግዲህ፣ እግዚአብሔርን ከማን ጋራ ታወዳድሩታላችሁ? ከየትኛውስ ምስል ጋራ ታነጻጽሩታላችሁ? የተቀረጸውንማ ምስል የእጅ ጥበብ ባለሙያ ይቀርጸዋል፤ ወርቅ አንጥረኛም በወርቅ ይለብጠዋል፤ የብር ሰንሰለትም ያበጅለታል። ለኢየሩሳሌም አለዝባችሁ ንገሯት፤ ዐውጁላትም፤ በባርነት ያገለገለችበት ዘመን አብቅቷል፤ የኀጢአቷም ዋጋ ተከፍሏል፤ ስለ ኀጢአቷ ሁሉ ከእግዚአብሔር እጅ ሁለት ዕጥፍ ተቀብላለች።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:35-36

ስለዚህ ታላቅ ዋጋ ያለውን መታመናችሁን አትጣሉ። የእግዚአብሔርን ፈቃድ ፈጽማችሁ የተስፋ ቃሉን እንድትቀበሉ፣ ጸንታችሁ መቆም ያስፈልጋችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 10:29-31

በአንድ ሳንቲም ከሚሸጡት ሁለት ድንቢጦች አንዲቷ እንኳ ያለ አባታችሁ ፈቃድ ምድር ላይ አትወድቅም። ፊልጶስና በርተሎሜዎስ፣ ቶማስና ቀረጥ ሰብሳቢው ማቴዎስ፣ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብና ታዴዎስ የተባለው ልብድዮስ፣ የራስ ጠጕራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር የተቈጠረ ነው። ስለዚህ አትፍሩ፤ ከብዙ ድንቢጦች የበለጠ ዋጋ አላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 12:3

ከድነቴ ምንጮች ውሃ በደስታ ትቀዳላችሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:4

እግዚአብሔርን ፈለግሁት፤ እርሱም መለሰልኝ፤ ከፍርሀቴም ሁሉ አዳነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:76

ለአገልጋይህ በገባኸው ቃል መሠረት፣ ምሕረትህ ለመጽናናት ትሁነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 14:30

ሰላም ያለው ልብ ለሰውነት ሕይወት ይሰጣል፤ ቅናት ግን ዐጥንትን ያነቅዛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 54:10

ተራሮች ቢናወጡ፣ ኰረብቶች ከስፍራቸው ቢወገዱ እንኳ፣ ለአንቺ ያለኝ ጽኑ ፍቅር አይናወጥም፤ የገባሁትም የሰላም ቃል ኪዳን አይፈርስም” ይላል መሓሪሽ እግዚአብሔር።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 94:18-19

እኔ፣ “እግሬ አዳለጠኝ” ባልሁ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ደግፎ ያዘኝ። የውስጤ ጭንቀት በበዛ መጠን፣ ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 41:13

እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀኝ እጅህን እይዛለሁና አትፍራ ይልሃል፤ እረዳሃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዘዳግም 31:8

እግዚአብሔር ራሱ በፊትህ ይሄዳል፤ ከአንተም ጋራ ይሆናል፤ ፈጽሞ አይለይህም፤ አይተውህምም፤ አትፍራ፤ ተስፋም አትቍረጥ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 13:8

ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንት፣ ዛሬም ለዘላለምም ያው ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:31

ታዲያ ለዚህ ምን እንመልሳለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ከሆነ፣ ማን ሊቃወመን ይችላል?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 3:5

እተኛለሁ፤ አንቀላፋለሁ፤ እግዚአብሔር ደግፎ ይዞኛልና እነቃለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 91:2

እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 66:13

እናት ልጇን እሹሩሩ እንደምትል፣ እኔም እናንተን እሹሩሩ እላችኋለሁ፤ በኢየሩሳሌምም ትጽናናላችሁ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 49:13

ሰማያት ሆይ፤ እልል በሉ፤ ምድር ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ ተራሮች ሆይ፤ በደስታ ዘምሩ! እግዚአብሔር ሕዝቡን ያጽናናል፤ ለተቸገሩትም ይራራልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 28:20

ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋራ ነኝ።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 1:6

በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እርሱ እስከ ክርስቶስ ኢየሱስ ቀን ድረስ ከፍጻሜው እንደሚያደርሰው ርግጠኛ ነኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢያሱ 1:9

በምትሄድበት ሁሉ እግዚአብሔር አምላክህ ከአንተ ጋራ ነውና አይዞህ፤ በርታ፤ ጽና፤ አትፍራ፤ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 41:14

አንተ ትል ያዕቆብ፣ ታናሽ እስራኤል ሆይ፤ ‘አትፍራ እኔ እረዳሃለሁ’ ” ይላል እግዚአብሔር፤ የሚቤዥህ የእስራኤል ቅዱስ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 5:1

እንግዲህ በእምነት ስለ ጸደቅን፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋራ ሰላም አለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:105

ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴም ብርሃን ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ጴጥሮስ 4:19

ስለዚህ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ መከራ የሚቀበሉ ሁሉ ነፍሳቸውን ለታመነ ፈጣሪ ዐደራ ሰጥተው መልካም ማድረጋቸውን ይቀጥሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 10:13

በሰዎች ሁሉ ላይ ከደረሰው የተለየ ፈተና አልደረሰባችሁም፤ እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ስለዚህ ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አይተዋችሁም፤ ነገር ግን በምትፈተኑበት ጊዜ ፈተናውን መታገሥ እንድትችሉ፣ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 4:8-9

ከየአቅጣጫው ብንገፋም አንንኰታኰትም፤ ግራ ብንጋባም ተስፋ አንቈርጥም፤ ብንሰደድም ተጥለን አንቀርም፤ መትተው ቢጥሉንም አንጠፋም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 56:3

ፍርሀት በሚይዘኝ ጊዜ፣ መታመኔን በአንተ ላይ አደርጋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:12

በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 18:2

እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤ አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፤ እርሱ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 62:5-6

ነፍሴ ሆይ፤ ዐርፈሽ እግዚአብሔርን ብቻ ጠብቂ፤ ተስፋዬ ከርሱ ዘንድ ነውና። ዐለቴና መድኀኒቴ እርሱ ብቻ ነው፤ መጠጊያዬም እርሱ ነው፤ እኔም አልናወጥም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 58:11

እግዚአብሔር ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ፀሓይ ባቃጠለው ምድር ፍላጎትህን ያሟላል፤ ዐጥንትህን ያበረታል፤ በውሃ እንደ ረካ የአትክልት ቦታ፣ እንደማይቋርጥም ምንጭ ትሆናለህ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 46:7

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ነው፤ የያዕቆብም አምላክ መጠጊያችን ነው። ሴላ

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 119:143

መከራና ሥቃይ ደርሶብኛል፤ ነገር ግን ትእዛዝህ ደስታዬ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 3:14

እግዚአብሔር በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ላይ ስለ ጠራኝ፣ ሽልማት ለመቀዳጀት ወደ ግቡ እፈጥናለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ሳሙኤል 22:31

“የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤ የእግዚአብሔርም ቃል የነጠረ ነው፤ መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ ጋሻ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 30:5

“የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፤ እርሱ ለሚታመኑበት ሁሉ ጋሻቸው ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:1

“ልባችሁ አይጨነቅ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 15:5

ብርታትንና መጽናናትን የሚሰጥ አምላክ፣ ክርስቶስ ኢየሱስን ስትከተሉ፣ በመካከላችሁ አንድ ሐሳብ ይስጣችሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 10:23

የተስፋን ቃል የሰጠን ታማኝ ስለ ሆነ፣ አምነን የምንናገርለትን ተስፋ አጥብቀን እንያዝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 18:30

የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤ የእግዚአብሔርም ቃል የነጠረ ነው። መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ፣ ጋሻ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 37:23-24

የሰው አካሄድ በእግዚአብሔር ይጸናል፤ በመንገዱ ደስ ይለዋል። ቢሰናከልም አይወድቅም፣ እግዚአብሔር በእጁ ደግፎ ይይዘዋልና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 26:8-9

እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕግህ ጐዳና በመሄድ፣ አንተን ተስፋ አድርገናል፤ ስምህና ዝናህ፣ የልባችን ምኞት ነው። ነፍሴ በሌሊት ትናፍቅሃለች፤ መንፈሴም በውስጤ ትፈልግሃለች። ፍርድህ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ፣ የዓለም ሕዝቦች ጽድቅን ይማራሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ፊልጵስዩስ 2:13

እንደ በጎ ፈቃዱ መፈለግንና ማድረግን በእናንተ ውስጥ የሚሠራ እግዚአብሔር ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 19:7-8

የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስንም መልሶ ያለመልማል፤ የእግዚአብሔር ሥርዐት የታመነ ነው፤ አላዋቂውን ጥበበኛ ያደርጋል። የእግዚአብሔር ሕግጋት ትክክል ናቸው፤ ልብን ደስ ያሰኛሉ። የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፤ ዐይንን ያበራል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 16:8

እግዚአብሔርን ሁልጊዜ በፊቴ አድርጌአለሁ፤ እርሱ በቀኜ ስላለ አልናወጥም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 94:22

ለእኔ ግን እግዚአብሔር ምሽግ፣ አምላኬም መጠጊያ ዐለት ሆኖኛል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ምሳሌ 4:23

ከሁሉም በላይ ልብህን ጠብቅ፤ የሕይወት ምንጭ ነውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 25:9

ዝቅ ያሉትን በፍትሕ ይመራቸዋል፤ ለትሑታንም መንገዱን ያስተምራቸዋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 14:13-14

አብ በወልድ እንዲከብር፣ በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ፤ ማንኛውንም ነገር በስሜ ብትለምኑኝ፣ እኔ አደርገዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤርምያስ 31:3

እግዚአብሔር ከሩቅ ተገለጠልን፤ እንዲህም አለን፤ “በዘላለማዊ ፍቅር ወድጄሻለሁ፤ ስለዚህም በርኅራኄ ሳብሁሽ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኤፌሶን 3:12

በርሱና በርሱ ላይ ባለን እምነት አማካይነት፣ በነጻነትና በልበ ሙሉነት ወደ እግዚአብሔር መቅረብ እንችላለን።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ቆሮንቶስ 5:7

ምክንያቱም የምንኖረው በእምነት እንጂ በማየት አይደለም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 43:18-19

“የቀደመውን ነገር አታስቡ፤ ያለፈውን እርሱ። እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ! እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን? በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤ በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 34:5

ወደ እርሱ የሚመለከቱ ያበራሉ፤ ፊታቸውም ከቶ አያፍርም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:34

ስለዚህ ለነገ በማሰብ አትጨነቁ፤ የነገ ጭንቀት ለነገ ይደር፤ እያንዳንዱ ዕለት የራሱ የሆነ በቂ ችግር አለውና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 55:6

እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፤ ቀርቦም ሳለ ጥሩት።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ቆሮንቶስ 2:9

ይሁን እንጂ እንደ ተጻፈው፣ “ዐይን ያላየውን፣ ጆሮ ያልሰማውን፣ የሰውም ልብ ያላሰበውን፣ እግዚአብሔር ለሚወድዱት አዘጋጅቷል፤”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዕብራውያን 12:2

የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፣ የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 28:7

እግዚአብሔር ብርታቴና ጋሻዬ ነው፤ ልቤ በርሱ ይታመናል፤ እርሱም ዐግዞኛል፤ ልቤ ሐሤት አደረገ፤ በዝማሬም አመሰግነዋለሁ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 7:7

“ለምኑ፣ ይሰጣችኋል፤ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ፣ በሩም ይከፈትላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 40:4-5

ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፤ ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማው ምድር ይስተካከላል፤ ወጣ ገባውም ለጥ ያለ ሜዳ ይሆናል። የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፤ የሰውም ዘር ሁሉ በአንድነት ያየዋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሯልና።”

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሉቃስ 12:32

“እናንተ አነስተኛ መንጋ የሆናችሁ፤ መንግሥትን ሊሰጣችሁ የአባታችሁ መልካም ፈቃድ ነውና አትፍሩ፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 5:3-4

በዚህ ብቻ ሳይሆን በመከራችንም ሐሤት እናደርጋለን፤ ምክንያቱም መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝ እናውቃለን። ትዕግሥት ጽናትን፣ ጽናት የተፈተነ ባሕርይን፣ የተፈተነ ባሕርይ ተስፋን፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 16:11

የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ፤ በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሓ አለ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 6:33

ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፤ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 30:21

ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዘወር ብትል ጆሮህ ከኋላህ፣ “መንገዱ ይህ ነው፤ በርሱ ሂድ” የሚል ድምፅ ይሰማል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 12:1-2

እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ሰውነታችሁን ቅዱስና እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሕያው መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፤ ይህም እንደ ባለ አእምሮ የምታቀርቡት አምልኳችሁ ነው። እርስ በርሳችሁ በወንድማማች መዋደድ አጥብቃችሁ ተዋደዱ፤ አንዱ ሌላውን ከራሱ በማስበለጥ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ። ጌታን ለማገልገል በመንፈስ የጋላችሁ ሁኑ እንጂ ከዚህ ትጋት ወደ ኋላ አትበሉ። በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ። ችግረኛ ለሆኑ ቅዱሳን ካላችሁ አካፍሉ፤ እንግዶችን ተቀበሉ። የሚያሳድዷችሁን መርቁ፤ መርቁ እንጂ አትርገሙ። ደስ ከሚላቸው ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያዝኑም ጋራ ዕዘኑ። እርስ በርሳችሁ በአንድ ሐሳብ በመስማማት ኑሩ። ዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ካሉ ጋራ ዐብራችሁ ለመሆን ፍቀዱ እንጂ አትኵራሩ፤ በራሳችሁም አትመኩ። ለማንም ክፉን በክፉ አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት በጎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ትጉ። ቢቻላችሁስ በበኩላችሁ ከሰው ሁሉ ጋራ በሰላም ኑሩ። ወዳጆቼ ሆይ፤ ለእግዚአብሔር ቍጣ ፈንታ ስጡ እንጂ አትበቀሉ፤ ጌታ “በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ” እንዳለ ተጽፏልና። መልካም፣ ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ዮሐንስ 15:7

በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ፣ የምትፈልጉትን ማንኛውንም ነገር ለምኑ፤ ይሰጣችኋልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
2 ጢሞቴዎስ 1:7

እግዚአብሔር የኀይልና የፍቅር፣ ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሀት መንፈስ አልሰጠንምና።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 61:1-2

እግዚአብሔር ሆይ፤ ጩኸቴን ስማ፤ ጸሎቴንም አድምጥ። ልቤ በዛለ ጊዜ፣ ከምድር ዳርቻ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ከእኔ ይልቅ ከፍ ወዳለው ዐለት ምራኝ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 73:26

ሥጋዬና ልቤ ሊደክሙ ይችላሉ፤ እግዚአብሔር ግን የልቤ ብርታት፣ የዘላለም ዕድል ፈንታዬ ነው።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ኢሳይያስ 58:6

“እንግዲህ እኔ የመረጥሁት ጾም፣ የጭቈናን ሰንሰለት እንድትበጥሱ፣ የቀንበርን ገመድ እንድትፈቱ፣ የተጨቈኑትን ነጻ እንድታወጡ፣ ቀንበርን ሁሉ እንድትሰብሩ አይደለምን?

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
1 ዮሐንስ 3:18-19

ልጆች ሆይ፤ በተግባርና በእውነት እንጂ በቃልና በአንደበት ብቻ አንዋደድ። እኛ ከእውነቱ መሆናችንን በዚህ እናውቃለን፤ ልባችንንም በፊቱ እናሳርፋለን፤

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ሮሜ 8:37-39

ምንም አይለየንም፤ በዚህ ሁሉ በወደደን በርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን። ይህን ተረድቻለሁ፤ ሞትም ይሁን ሕይወት፣ መላእክትም ይሁኑ አጋንንት፣ ያለውም ይሁን የሚመጣው፣ ወይም ማንኛውም ኀይል፣ ከፍታም ይሁን ጥልቀት ወይም የትኛውም ፍጥረት፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካለው ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን አይችልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 145:18-19

እግዚአብሔር ለሚጠሩት ሁሉ፣ በእውነት ለሚጠሩት ሁሉ ቅርብ ነው። ለሚፈሩት ፍላጎታቸውን ይፈጽማል፤ ጩኸታቸውን ይሰማል፤ ያድናቸዋልም።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
ማቴዎስ 5:14-16

“እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፤ በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትደበቅ አትችልም፤ ሰዎችም መብራት አብርተው ከእንቅብ በታች አያስቀምጡትም፤ በቤት ውስጥ ላሉት ሁሉ እንዲያበራ በመቅረዝ ላይ ያስቀምጡታል እንጂ። እንደዚሁም ሰዎች መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማይ ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ በሰዎች ፊት ይብራ።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ
መዝሙር 121:1-2

ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረድኤቴ ከወዴት ይመጣል? ረድኤቴ ሰማይንና ምድርን ከፈጠረ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል።

ምዕራፍ    |  ስሪቶች ቅዳ

ወደ እግዚአብሔር ጸሎት

እግዚአብሔር ቸርና ዘላለማዊ፣ ልዑል ጌታ፣ በኢየሱስ ስም ወደ አንተ እመጣለሁ፤ አንተ ብቻ ለከፍተኛ ምስጋናና አለማዊ አምልኮ ብቁ ነህ። የክርስቶስን ደም በሕይወቴ ላይ እገልጻለሁ፣ እናም አሁኑኑ ከልቤ ውስጥ ማንኛውንም ጭንቀት፣ አለመረጋጋትና ፍርሃት አስወግዳለሁ። ጌታ ሆይ፣ በእጅህ ከመሆን የተሻለ ዋስትና እንደሌለ አመሰግንሃለሁ፤ ምክንያቱም ከአንተ ጋር ስሄድ በትክክለኛው መንገድ እሄዳለሁ፤ ቃልህን ስለማታፈርስና አእምሮዬንና ልቤን ፍጹም ሰላም እንደምትጠብቅ ቃል ስለገባህልኝ አመሰግንሃለሁ። ጌታ ሆይ፣ በእጅህ ከመሆን የተሻለ ዋስትና እንደሌለ አመሰግንሃለሁ፤ ምክንያቱም ከአንተ ጋር ስሄድ በትክክለኛው መንገድ እሄዳለሁ፤ ቃልህን ስለማታፈርስና አእምሮዬንና ልቤን ፍጹም ሰላም እንደምትጠብቅ ቃል ስለገባህልኝ አመሰግንሃለሁ። ቃልህ «ከክፉ ራቁ፣ መልካምንም አድርጉ፤ ሰላምንም ፈልጉ፣ ተከተሉትም» ይላል። የመንፈስ ቅዱስህ መገኘትና ፍሬ በሕይወቴና በቤተሰቦቼ ላይ እንዲሰፍን እለምንሃለሁ። በሕይወቴ ነጻነት እገልጻለሁ፤ ከዚህ ቅጽበት ጀምሮም ለማንኛውም ድብርት፣ ሀዘን፣ ትዕግስት ማጣትና ጭንቀት እቃወማለሁ። የዚህ ዓለም ጫናና ውጥረት ከአንተ ጋር ያለኝን ግንኙነት ወይም በዙሪያዬ ያሉትን ሰዎች እንዲጎዳ አትፍቀድ፤ ከሁሉም ጋር ሰላም እንዳለኝ እንዳደርግና ያለሱ ማንም እንደማያይህ ያለውን ቅድስና እንድፈጽም እርዳኝ። መንፈስህን በእኔ ውስጥ አድስ፤ አእምሮዬ ፍጹም ሰላም እንዲያገኝ ከማንኛውም ትዝታና ህመም ፈውሰኝ። በኢየሱስ ስም። አሜን።
ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች