መዝሙር 128:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤል እንዲህ ይበል፥ “ከትንሽነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ተሰለፉብኝ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፣ በመንገዱም የሚሄዱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመዓርግ መዝሙር። ጌታን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርን የሚፈሩና ትእዛዞቹን በመጠበቅ የሚኖሩ ደስ ይበላቸው። |
ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች፤ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤ መታመንንና የጌትነትን ክብር ለበስህ።
እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ቤትን የሚሠሩ በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ የሚጠብቁ በከንቱ ይተጋሉ።
በይሁዳ፥ በሰማርያና በገሊላ ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ በሰላም ኖሩ፤ ታነጹም፤ እግዚአብሔርንም በመፍራት ጸንተው ኖሩ፤ ሕዝቡም በመንፈስ ቅዱስ አጽናኝነት በዙ።
እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! ልትመላለሱ እግዚአብሔርንም ደስ ልታሰኙ እንዴት እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ እንደ ተቀበላችሁ፥ እናንተ ደግሞ እንደምትመላለሱ፥ ከፊት ይልቅ ትበዙ ዘንድ በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችሁማለን።