Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




2 ሳሙኤል 22:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጠብ​ቄ​አ​ለ​ሁና፥ በአ​ም​ላ​ኬም አላ​መ​ፅ​ሁ​ምና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ አምላኬንም በመተው ክፉ አላደረግሁም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የጌታን መንገድ ጠብቄአለሁና፤ ከአምላኬ ክፋት በማድረግ አልተለየሁም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እኔ የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትያለሁ፤ ፊቴን ከአምላኬ በመመለስ ክፉ ነገር አላደረግሁም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፥ በአምላኬም አላመፅሁምና።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 22:22
15 Referencias Cruzadas  

አሁንም ልጄ ሆይ፥ ስማኝ፥ መንገዴን የሚጠብቁ ብፁዓን ናቸው።


ጽድ​ቅ​ንና ፍር​ድን በማ​ድ​ረግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ይጠ​ብቁ ዘንድ፥ ልጆ​ቹ​ንና ቤቱን ያዝ​ዛ​ቸው ዘንድ እን​ዳ​ለው አው​ቃ​ለ​ሁና፤ ይህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ር​ሃም የተ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ያደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ ነው።”


እስ​ራ​ኤል እን​ዲህ ይበል፥ “ከት​ን​ሽ​ነቴ ጀምሮ ሁል​ጊዜ ተሰ​ለ​ፉ​ብኝ፤


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቸር​ነ​ትና ይቅ​ርታ መመ​ኪ​ያ​ች​ንና የነ​ፃ​ነ​ታ​ችን ምስ​ክር ይህቺ ናትና፥ በሥ​ጋዊ ጥበብ ሳይ​ሆን፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ በዚህ ዓለም፥ ይል​ቁ​ንም በእ​ና​ንተ ዘንድ ተመ​ላ​ለ​ስን።


የም​ት​ወ​ዱኝ ብት​ሆኑ ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ፤ እኔ የአ​ባ​ቴን ትእ​ዛዝ እንደ ጠበ​ቅሁ፥ በፍ​ቅ​ሩም እን​ደ​ም​ኖር እና​ን​ተም ትእ​ዛ​ዜን ብት​ጠ​ብቁ በፍ​ቅሬ ትኖ​ራ​ላ​ችሁ።


እግዚአብሔርንም ከመከተል የተመለሱትን፥ እግዚአብሔርንም ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።


በል​ቅሶ የሚ​ዘሩ በደ​ስታ ይሰ​በ​ስ​ባሉ።


አቤቱ፥ በተ​ጨ​ነ​ቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ሰማ​ኸ​ኝም።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታመን፥ መል​ካ​ም​ንም አድ​ርግ፥ በም​ድ​ርም ያሳ​ድ​ር​ሃል፥ በሀ​ብ​ት​ዋም ያሰ​ማ​ር​ሃል።


እነ​ሆኝ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና እርሱ በቀ​ባው ፊት መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ የማ​ንን በሬ ወሰ​ድሁ? የማ​ን​ንስ አህያ ወሰ​ድሁ? ማን​ንስ ሸነ​ገ​ልሁ? በማ​ንስ ላይ ግፍ አደ​ረ​ግሁ? ነጠላ ጫማ እን​ኳን ቢሆን ከማን እጅ መማ​ለጃ ተቀ​በ​ልሁ? መስ​ክ​ሩ​ብኝ፤ እኔ እመ​ል​ስ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።”


ሙሴም እጅግ አዘነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አለው፥ “ወደ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው አት​መ​ል​ከት፤ እኔ ከእ​ነ​ርሱ አን​ዳ​ችም ተመ​ኝቼ አል​ወ​ሰ​ድ​ሁም፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው አል​በ​ደ​ል​ሁም።”


ዳዊ​ትም አባ​ትህ በጽ​ድቅ፥ በን​ጹሕ ልብና በቅ​ን​ነት እንደ ሄደ አንተ ደግሞ በፊቴ ብት​ሄድ፥ ያዘ​ዝ​ሁ​ህ​ንም ሁሉ ብታ​ደ​ርግ፥ ሥር​ዐ​ቴ​ንም ሕጌ​ንም ብት​ጠ​ብቅ፥


ሰማ​ያት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር ይና​ገ​ራሉ፥ የሰ​ማ​ይም ጠፈር የእ​ጁን ሥራ ያወ​ራል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios