መዝሙር 128 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የመዓርግ መዝሙር። 1 እስራኤል እንዲህ ይበል፥ “ከትንሽነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ተሰለፉብኝ፤ 2 ከትንሽነቴ ጀምሮ ሁልጊዜ ተሰለፉብኝ፤ ነገር ግን አልቻሉኝም። 3 ኃጥኣን በጀርባዬ ላይ መቱኝ፥ ኀጢአታቸውንም አበዙአት።” 4 እግዚአብሔር ጻድቅ ነው፤ የኃጥኣንን አንገታቸውን ቈረጠ። 5 ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ። 6 በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥ ሳይነቀል እንደሚደርቅ፥ 7 ለሚያጭደው እጁን፥ ነዶዎቹን ለሚሰበስብም እቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ። 8 በመንገድም የሚያልፉ፥ “የእግዚአብሔር በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በእግዚአብሔር ስም እንመርቃችኋለን” አይበሉ። |