መዝሙር 120 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የመዓርግ መዝሙር። 1 ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ፤ ረድኤቴ ከወዴት ይምጣ? 2 ረድኤቴ ሰማይና ምድርን ከፈጠረ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። 3 ለእግሮችህ ሁከትን አይሰጣቸውም፤ የሚጠብቅህም አይተኛም። 4 እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም፥ አያንቀላፋምም። 5 እግዚአብሔር ይጠብቅህ፥ እግዚአብሔርም በቀኝ እጁ ይጋርድህ። 6 ፀሐይ በቀን አያቃጥልህ፤ ጨረቃም በሌሊት። 7 እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅህ፥ እግዚአብሔር ነፍስህንም ይጠብቃት። 8 ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እግዚአብሔር መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቅ። |