Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 128 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


1 የመዓርግ መዝሙር።

1 የመዓርግ መዝሙር። ጌታን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች ናቸው።

2 የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ፥ ምስጉን ነህ፤ መልካምም ይሆንልሃል።

3 ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፥ ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።

4 እነሆ፥ ጌታን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል።

5 ጌታ ከጽዮን ይባርክህ፥ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢየሩሳሌምን መልካምነትዋን ታያለህ።

6 የልጆችህንም ልጆች ታያለህ። በእስራኤል ላይ ሰላም ይሁን።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos