Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 127 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የመ​ዓ​ርግ መዝ​ሙር።

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈ​ሩት ሁሉ፥ በመ​ን​ገ​ዶ​ቹም የሚ​ሄዱ ብፁ​ዓን ናቸው።

2 የድ​ካ​ም​ህን ፍሬ ትመ​ገ​ባ​ለህ፤ ብፁዕ ነህ፥ መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ል​ሃል።

3 ሚስ​ትህ በቤ​ትህ እል​ፍኝ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ያ​ፈራ ወይን ትሆ​ና​ለች፤ ልጆ​ች​ህም በማ​ዕ​ድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወ​ይራ ተክል ይሆ​ናሉ።

4 እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው እን​ዲህ ይባ​ረ​ካል።

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ይባ​ር​ክህ፤ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መል​ካ​ም​ነት ታያ​ለህ።

6 የል​ጆ​ች​ህ​ንም ልጆች ታያ​ለህ። በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ሰላም ይሁን።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos