መዝሙር 119 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)የመዓርግ መዝሙር። 1 አቤቱ፥ በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ አንተ ጮኽሁ፥ ሰማኸኝም። 2 ከዐመፀኛ ከንፈር፥ ከሸንጋይም አንደበት፥ አቤቱ፥ ነፍሴን አድናት። 3 ስለ ሽንገላ አንደበት ምንን ይሰጡሃል? ምንስ ይጨምሩልሃል? 4 እንደ በረሃ ቋያ የኀያል ፍላጾች የተሳሉ ናቸው። 5 መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፤ በዘላን ድንኳኖች አደርሁ። 6 ሰላምን ከሚጠሉ ጋር ነፍሴ ብዙ ጊዜ ታገሠች። 7 እኔ ሰላማዊ ስሆን በተናገርኋቸው ጊዜ በከንቱ ይጠሉኛል። |