የአክቦር ልጅ በአልሐናንም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ አዳር ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፎጎር ነው፤ ሚስቱም የሜዛአብ ልጅ መጥሬድ የወለደቻት ምኤጠብኤል ትባላለች።
ነህምያ 6:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም ወደ መሔጣብኤል ልጅ ወደ ዶልያ ልጅ ወደ ሴሜይ ቤት ገባሁ፤ እርሱም ተዘግቶ ነበርና፥ “በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ ውስጥ እንግባ፤ የመቅደሱንም ደጆች እንዝጋ፤ እነርሱ በሌሊት ይገድሉህ ዘንድ ይመጣሉና” አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ቀን ቤቱ በላዩ ላይ ተዘግቶበት ወደ ነበረው ወደ መሄጣብኤል ልጅ ወደ ድላያ ልጅ ወደ ሸማያ ሄድሁ፤ እርሱም፣ “ሰዎች ሊገድሉህ ይመጣሉ፤ በርግጥም በሌሊት ሊገድሉህ ይመጣሉ፤ በእግዚአብሔር ቤት ባለው በቤተ መቅደሱ ውስጥ እንገናኝ፤ የቤተ መቅደሱንም በሮች እንዝጋቸው” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም ወደ ሜሔጣብኤል ልጅ፥ ወደ ዴላያ ልጅ፥ ወደ ሼማዕያ ቤት ሄድሁ፤ እርሱም ተዘግቶ ነበርና፦ “በእግዚአብሔር ቤት፥ በመቅደሱ ውስጥ እንገናኝ፥ የመቅደሱንም በሮች እንዝጋ፤ ሊገድሉህ ይመጣሉና፥ በሌሊት ሊገድሉህ ይመጣሉና” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ጊዜ ከቤቱ እንዳይወጣ ተዘግቶበት ወደነበረው የመሄጣብኤል የልጅ ልጅ ወደ ሆነው ወደ ደላያ ልጅ ሸማዕያ ዘንድ ሄድኩ፤ እርሱም “በሌሊት ሊገድሉህ ስለሚመጡ አንተና እኔ ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ገብተን በሮቹን በመዝጋት እንደበቅ” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም ወደ መሔጣብኤል ልጅ ወደ ድላያ ልጅ ወደ ሸማያ ቤት ገባሁ፥ እርሱም ተዘግቶ ነበርና፦ በእግዚአብሔር ቤት በመቅደሱ ውስጥ እንገናኝ የመቅደሱንም ደጆች እንዝጋ፥ እነርሱ መጥተው ይገድሉሃልና፥ በሌሊትም ይገድሉህ ዘንድ ይመጣሉና አለ። |
የአክቦር ልጅ በአልሐናንም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ አዳር ነገሠ፤ የከተማውም ስም ፎጎር ነው፤ ሚስቱም የሜዛአብ ልጅ መጥሬድ የወለደቻት ምኤጠብኤል ትባላለች።
የአክዓብን ቤት ሁሉ ታጠፋለህ፤ በእስራኤልም ዘንድ አጥር ተጠግቶ እስከሚሸን የቀረበውን ሁሉና ከእነርሱ የቀረውን ሁሉ ታጠፋለህ።
አካዝም የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃዎች ሁሉ ወስዶ ሰባበራቸው፤ የእግዚአብሔርንም ቤት ደጆች ዘጋ፤ በኢየሩሳሌምም ማዕዘን ሁሉ ለራሱ መሠዊያ ሠራ።
ደግሞም የእግዚአብሔርን ቤት ደጆች ዘግተዋል፤ መብራቶቹንም አጥፍተዋል፤ በመቅደሱም ውስጥ ለእስራኤል አምላክ አላጠኑም፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አላቀረቡም።
ወደ አለቆቹም ወደ አልዓዛር፥ ወደ አርኤል፥ ወደ ሰማአያ፥ ወደ ሀሎናም፥ ወደ ያሪብ፥ ወደ ሄልናታን፥ ወደ ናታን፥ ወደ ዘካርያስ፥ ወደ ሜሱላም፥ ደግሞም ወደ ዐዋቂዎቹ ወደ ዮያሪብና ወደ ሄልናታን ላክሁ።
እግዚአብሔርም ልኮት እንዳልነበረ፥ በእኔ ላይ ግን ትንቢት እንደ ተናገረ፥ እነሆ፥ ዐወቅሁ፤ ጦብያና ሰንባላጥም ገዝተውት ነበር።
ነፍሴንም የሚሹአት በረቱብኝ፥ መከራዬንም የሚፈልጉ ከንቱን ተናገሩ፥ ሁልጊዜም ያጠፉኝ ዘንድ በሽንገላ ይመክራሉ።
በመሠዊያዬ ላይ እሳትን በከንቱ እንዳታቃጥሉ ከእናንተ ዘንድ ደጅ የሚዘጋ ሰው ምነው በተገኘ! በእናንተ ደስ አይለኝም፥ ቍርባንንም ከእጃችሁ አልቀበልም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።