Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 6:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በቤ​ቱም ግንብ ዙሪያ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ግንብ ዙሪያ ደርብ ሠራ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ጓዳ​ዎች አደ​ረገ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በዋናው ቤተ መቅደስና በቅድስተ ቅዱሳኑ ግድግዳ ዙሪያ ልዩ ክፍሎች ያሉት ተቀጥላ ግንብ ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የቤተ መቅደሱን ሕንጻ አስጠግቶ በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ ዙሪያ ደርብ ሠራ፤ በዙሪያውም ክፍሎችን አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የቤተ መቅደሱን ሕንጻ አስጠግቶ በቅድስቱና በቅድስተ ቅዱሳኑ ዙሪያ ደርብ ሠራ፤ በዙሪያውም ክፍሎችን አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 በቤቱም ግንብ ዙሪያ፥ በመቅደሱና በቅድስተ ቅዱሳኑ ግንብ ዙሪያ፥ ደርብ ሠራ፤ በዙሪያውም ጓዳዎች አደረገ።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 6:5
26 Referencias Cruzadas  

ከቤተ መቅ​ደሱ አያ​ይዞ ከመ​ሠ​ረቱ ጀምሮ እስከ ጣራው ድረስ ሃያ​ውን ክንድ በዝ​ግባ ጠርብ ሠራ፤ ከመ​ቅ​ደ​ሱም ከፍሎ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑን አደ​ረገ።


ለቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም መግ​ቢያ ከወ​ይራ እን​ጨት ሳን​ቃ​ዎ​ችን ሠራ፤ መድ​ረ​ኩ​ንና መቃ​ኖ​ቹን፥ ደፉ​ንም አም​ስት ማዕ​ዘን አደ​ረገ።


የታ​ች​ኛ​ውም ደርብ ወርዱ አም​ስት ክንድ፥ የመ​ካ​ከ​ለ​ኛ​ውም ደርብ ወርዱ ስድ​ስት ክንድ፥ የሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ደርብ ወርዱ ሰባት ክንድ ነበረ። ሰረ​ገ​ሎቹ በቤቱ ግንብ ውስጥ እን​ዳ​ይ​ገቡ ከቤቱ ግንብ ውጭ አረ​ፍ​ቶ​ችን አደ​ረገ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዩና በየ​መ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ ለማ​ገ​ል​ገል፥ ቅዱ​ሱ​ንም ዕቃ ሁሉ ለማ​ን​ጻት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ለመ​ሥ​ራት ከአ​ሮን ልጆች እጅ በታች ሹሞ​አ​ቸው ነበር።


ዳዊ​ትም ለመ​ቅ​ደሱ ወለል፥ ለቤ​ቱም፥ ለቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም፥ ለደ​ር​ቡና ለው​ስ​ጡም ጓዳ​ዎች፥ ለስ​ር​የ​ቱም መክ​ደኛ መቀ​መጫ ምሳ​ሌ​ውን ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን ሰጠው።


እነ​ዚህ አራቱ ኀያ​ላን ሰዎች ለአ​ራቱ በሮች ኀላ​ፊ​ዎች ነበሩ። ሌዋ​ው​ያ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ባሉ ጓዳ​ዎ​ችና ቤተ መዛ​ግ​ብት ላይ የተ​ሾሙ ነበሩ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ጎተራ ያዘ​ጋጁ ዘንድ አዘዘ፤ እነ​ር​ሱም አዘ​ጋጁ።


በመ​ቅ​ደሱ ፊት እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው የሚ​ያ​በሩ መቅ​ረ​ዞ​ች​ንና ቀን​ዲ​ሎ​ች​ንም ከጥሩ ወርቅ ሠራ።


ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳን ታቦት ወደ ቤትዋ አም​ጥ​ተው በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳን ውስጥ ከኪ​ሩ​ቤል ክንፍ በታች በነ​በ​ረው መቅ​ደስ አኖ​ሯት።


መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹም ረጃ​ጅ​ሞች ነበ​ሩና በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ ፊት ከመ​ቅ​ደሱ ውስጥ ጫፎ​ቻ​ቸው ይታዩ ነበር፤ ነገር ግን ከውጭ አይ​ታ​ዩም ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ እዚያ አሉ።


የእ​ህ​ላ​ች​ን​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ የዛ​ፉን ሁሉ ፍሬ፥ የወ​ይ​ኑ​ንና የዘ​ይ​ቱ​ንም ፍሬ ወደ ካህ​ናቱ ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ጓዳ​ዎች እና​መጣ ዘንድ፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑም ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችን እርሻ ሁሉ ዐሥ​ራት ይቀ​በ​ላ​ሉና የመ​ሬ​ታ​ች​ንን ዐሥ​ራት ወደ ሌዋ​ው​ያን እና​መጣ ዘንድ ማልን።


የይ​ሁ​ዳም ሕዝብ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን ደስ ስላ​ላ​ቸው፥ የካ​ህ​ና​ቱ​ንና የሌ​ዋ​ው​ያ​ኑን ዕድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከ​ተ​ሞች እር​ሻ​ዎች ያከ​ማቹ ዘንድ ለቀ​ዳ​ም​ያት፥ ለዐ​ሥ​ራ​ትም በየ​ዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎ​ችን ሾሙ።


የስ​ሙን ክብር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥ በቅ​ድ​ስ​ናው ስፍራ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስገዱ።


በዚ​ያም እገ​ለ​ጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የማ​ዝ​ዝ​ህን ሁሉ፥ በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁ​ለት ኪሩ​ቤል መካ​ከል፥ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ ሆኜ እነ​ጋ​ገ​ር​ሃ​ለሁ።


ከወደ ኋላ​ህም ሳቡህ፥ በሽ​ቱህ መዓ​ዛም እን​ሮ​ጣ​ለን፤ ንጉሡ ወደ እል​ፍኙ አገ​ባኝ፤ በአ​ንቺ ደስ ይለ​ኛል፥ ሐሤ​ትም እና​ደ​ር​ጋ​ለን፤ ከወ​ይን ጠጅ ይልቅ ጡቶ​ች​ሽን እን​ወ​ዳ​ለን፤ አን​ቺ​ንም መው​ደድ የተ​ገባ ነው።


“ወደ ሬካ​ባ​ው​ያን ቤት ሄደህ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አም​ጥ​ተህ ከክ​ፍ​ሎቹ ወደ አን​ዲቱ አግ​ባ​ቸው፤ የወ​ይን ጠጅም አጠ​ጣ​ቸው።”


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በበ​ረ​ኛው በሰ​ሎም ልጅ በማ​ሴው ጓዳ በላይ ባለው በአ​ለ​ቆቹ ጓዳ አጠ​ገብ ወደ አለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ወደ ጎዶ​ልያ ልጅ ወደ ሐና​ንያ ልጆች ጓዳ አገ​ባ​ኋ​ቸው።


ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባ​ይም አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም በአ​ደ​ባ​ባዩ ዙሪያ የተ​ሠሩ ዕቃ ቤቶ​ችና ወለል ነበሩ፤ በወ​ለ​ሉም ላይ ሠላሳ ዕቃ ቤቶች ነበሩ።


ወደ ውስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም ሁለት ቤቶች ነበሩ፤ አንዱ ወደ ሰሜን በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አጠ​ገብ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ውም ወደ ደቡብ ይመ​ለ​ከት ነበረ፤ ሌላ​ውም ወደ ደቡብ በሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አጠ​ገብ ነበረ፤ መግ​ቢ​ያ​ውም ወደ ሰሜን ይመ​ለ​ከት ነበር።


በመ​ቅ​ደ​ሱም ፊት ርዝ​መ​ቱን አርባ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም ሃያ ክንድ አድ​ርጎ ለካና፥ “ይህ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ነው” አለኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እኔ በስ​ር​የቱ መክ​ደኛ ላይ በደ​መ​ናው ውስጥ እታ​ያ​ለ​ሁና እን​ዳ​ይ​ሞት በመ​ጋ​ረ​ጃው ውስጥ በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ወዳ​ለው ወደ ስር​የቱ መክ​ደኛ ወደ ተቀ​ደ​ሰው ስፍራ ሁል​ጊዜ እን​ዳ​ይ​ገባ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን ንገ​ረው።


ሙሴም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን እር​ሱን ለመ​ነ​ጋ​ገር በገባ ጊዜ በቃል ኪዳኑ ታቦት ላይ ካለው ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛው በላይ ከኪ​ሩ​ቤ​ልም መካ​ከል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ይና​ገር ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos