Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


2 ነገሥት 9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ኢዩ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ እንደ ነገሠ

1 ነቢ​ዩም ኤል​ሳዕ ከነ​ቢ​ያት ልጆች አን​ዱን ጠርቶ እን​ዲህ አለው፥ “ወገ​ብ​ህን ታጥ​ቀህ ይህን የዘ​ይት ቀንድ በእ​ጅህ ያዝ፤ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድም ሂድ።

2 በዚ​ያም በደ​ረ​ስህ ጊዜ የና​ሜ​ሲን ልጅ የኢ​ዮ​ሣ​ፍ​ጥን ልጅ ኢዩን ታገ​ኘ​ዋ​ለህ፤ ገብ​ተ​ህም ከወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል አስ​ነ​ሣው፤ ወደ ጓዳም አግ​ባው።

3 የዘ​ይ​ቱ​ንም ቀንድ ይዘህ በራሱ ላይ አፍ​ስ​ሰ​ውና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባ​ሁህ በለው፤ ከዚ​ህም በኋላ በሩን ከፍ​ተህ ሽሽ፥ አት​ዘ​ግ​ይም።”

4 እን​ዲ​ሁም ጐል​ማ​ሳው ነቢይ ወደ ሬማት ዘገ​ለ​ዓድ ሄደ።

5 በገ​ባም ጊዜ፥ እነሆ፥ የሠ​ራ​ዊት አለ​ቆች ተቀ​ም​ጠው አገኘ፤ እር​ሱም፥ “አለቃ ሆይ፥ የም​ና​ገ​ረው መል​እ​ክት አለኝ” አለ። ኢዩም፥ “ከማ​ን​ኛ​ችን ጋር ነው?” አለ። እር​ሱም፥ “አለቃ ሆይ፥ ከአ​ንተ ጋር ነው” አለ።

6 ተነ​ሥ​ቶም ወደ ቤቱ ገባ፥ ዘይ​ቱ​ንም በራሱ ላይ አፍ​ስሶ እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባ​ሁህ።

7 የባ​ሪ​ያ​ዎቼን የነ​ቢ​ያ​ትን ደም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ባሪ​ያ​ዎች ሁሉ ደም ከኤ​ል​ዛ​ቤል እጅና ከአ​ክ​ዓብ ቤት ሁሉ እጅ እበ​ቀል ዘንድ የጌ​ታ​ህን የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ታጠ​ፋ​ለህ።

8 የአ​ክ​ዓ​ብን ቤት ሁሉ ታጠ​ፋ​ለህ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ አጥር ተጠ​ግቶ እስ​ከ​ሚ​ሸን የቀ​ረ​በ​ውን ሁሉና ከእ​ነ​ርሱ የቀ​ረ​ውን ሁሉ ታጠ​ፋ​ለህ።

9 የአ​ክ​ዓ​ብ​ንም ቤት እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ቤት፥ እንደ አኪ​ያም ልጅ እንደ ባኦስ ቤት አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።

10 ኤል​ዛ​ቤ​ል​ንም በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል እርሻ ውሾች ይበ​ሉ​አ​ታል፥ የሚ​ቀ​ብ​ራ​ትም አታ​ገ​ኝም።” በሩ​ንም ከፍቶ ሸሸ።

11 ኢዩም ወደ ጌታው ብላ​ቴ​ኖች ወጣ፤ እነ​ር​ሱም፥ “ደኅና ነውን? ይህ እብድ ለምን ወደ አንተ መጣ?” አሉት። እር​ሱም፥ “ሰው​ዬው ፌዝ እን​ደ​ሚ​ና​ገር አታ​ው​ቁ​ምን?” አላ​ቸው።

12 እነ​ር​ሱም፥ “ዋሸ​ኸን፤ ነገር ግን ንገ​ረን” አሉት፤ ኢዩም፦ ለጌ​ታው ልጆች፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባ​ሁህ ብሎ እን​ዲ​ህና እን​ዲህ ነገ​ረኝ” አላ​ቸው።

13 በሰ​ሙም ጊዜ ሁሉም ፈጥ​ነው ልብ​ሳ​ቸ​ውን ወሰዱ፤ በሰ​ገ​ነቱ መውጫ እር​ከን ላይም ከእ​ግሩ በታች አነ​ጠ​ፉት፥ መለ​ከ​ትም እየ​ነፉ፥ “ኢዩ ነግ​ሦ​አል” አሉ።

14 እን​ዲ​ሁም የና​ሜሲ ልጅ የኢ​ዮ​ሣ​ፍጥ ልጅ ኢዩ ኢዮ​ራ​ምን ከዳው። ኢዮ​ራ​ምና የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል የተ​ነሣ ሬማት ዘገ​ለ​ዓ​ድን ይጠ​ብቁ ነበር።

15 ንጉሡ ኢዮ​ራም ግን ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ ሶር​ያ​ው​ያን ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል ይታ​ከም ዘንድ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ተመ​ልሶ ነበር። ኢዩም ከእ​ርሱ ጋር ለነ​በ​ሩት እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ከእኔ ጋር ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ለሞት መስ​ጠት ትች​ላ​ላ​ች​ሁን? እን​ግ​ዲህ ማንም የሚ​ያ​መ​ል​ጣ​ችሁ፥ ከከ​ተ​ማ​ች​ሁም የሚ​ወጣ እን​ዳ​ይ​ኖ​ርና በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል እን​ዳ​ያ​ወራ ተጠ​ን​ቀቁ።”

16 የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ኢዮ​ራ​ምም ከሶ​ርያ ንጉሥ ከአ​ዛ​ሄል ጋር በተ​ዋጋ ጊዜ አረ​ማ​ው​ያን የሶ​ርያ ሰዎች በሬ​ማት ያቈ​ሰ​ሉ​ትን ቍስል በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ይታ​ከም ስለ ነበረ ኢዩ በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ተቀ​ምጦ ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ሄደ። ጠን​ካ​ራና ኀይ​ለኛ ሰው ነበ​ርና፤ የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ኢዮ​ራ​ምን ለማ​የት ወርዶ ነበር።

17 ሰላ​ይም ያያ​ቸው ዘንድ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ግንብ ላይ ቆመ፤ ሲመ​ጡም የእ​ነ​ኢ​ዩን አቧራ አየ። “እነ​ሆም፥ አቧራ አያ​ለሁ” አለ። ኢዮ​ራ​ምም፥ “ይገ​ና​ኛ​ቸው ዘንድ አንድ ፈረ​ሰኛ ይሂድ፤ እር​ሱም፦ ሰላም ነውን? ይበ​ላ​ቸው” አለ።

18 ፈረ​ሰ​ኛ​ውም ሊቀ​በ​ላ​ቸው ሄዶ፥ “ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፦ ሰላም ነውን?” አላ​ቸው። ኢዩም፥ “አንተ ከሰ​ላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ ተመ​ል​ሰህ ተከ​ተ​ለኝ” አለ። ሰላ​ዩም፥ “መል​እ​ክ​ተ​ኛው ደረ​ሰ​ባ​ቸው፥ ነገር ግን አል​ተ​መ​ለ​ሰም” ብሎ ነገ​ረው።

19 ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ፈረ​ሰኛ ሰደደ፤ ወደ እነ​ር​ሱም ደርሶ ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፥ “ሰላም ነውን?” አላ​ቸው። ኢዩም፥ “አንተ ከሰ​ላም ጋር ምን አለህ? ወደ ኋላዬ ተመ​ል​ሰህ ተከ​ተ​ለኝ” አለ።

20 ሰላ​ዩም፥ “መል​እ​ክ​ተ​ኛው ደረ​ሰ​ባ​ቸው፥ ነገር ግን አል​ተ​መ​ለ​ሰም፤ የሚ​መ​ራው ግን እንደ ናሜሲ ልጅ እንደ ኢዩ ይመ​ራል በች​ኮላ ይሄ​ዳ​ልና” ብሎ ነገ​ረው።

21 ኢዮ​ራ​ምም፥ “ሰረ​ገላ አዘ​ጋጁ” አለ፤ ሰረ​ገ​ላ​ው​ንም አዘ​ጋ​ጁ​ለት። የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​ራ​ምና የይ​ሁዳ ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ሁለ​ቱም በሰ​ረ​ገ​ሎ​ቻ​ቸው ተቀ​ም​ጠው ወጡ፤ ኢዩ​ንም ሊገ​ና​ኙት ሄዱ፤ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊ​ውም በና​ቡቴ እርሻ ውስጥ አገ​ኙት።

22 ኢዮ​ራ​ምም ኢዩን ባየ ጊዜ “ኢዩ ሆይ፥ ሰላም ነውን?” አለ። እር​ሱም፥ “የእ​ና​ትህ የኤ​ል​ዛ​ቤል ግል​ሙ​ት​ና​ዋና መተቷ ሲበዛ ምን ሰላም አለ?” ብሎ መለሰ።

23 ኢዮ​ራ​ምም መልሶ ነዳና ሸሸ፤ አካ​ዝ​ያ​ስ​ንም፥ “አካ​ዝ​ያስ ሆይ፥ ዐመፅ ነው” አለው።

24 ኢዩም በእጁ ቀስ​ቱን ለጠጠ፤ ኢዮ​ራ​ም​ንም በጫ​ን​ቃው መካ​ከል ወጋው ፤ ፍላ​ጻ​ውም በልቡ አለፈ፤ ወደ ሰረ​ገ​ላ​ውም ውስጥ በጕ​ል​በቱ ላይ ወደቀ።

25 ኢዩም ጋሻ​ጃ​ግ​ሬ​ውን ቢድ​ቃ​ርን እን​ዲህ አለው፥ “አን​ሥ​ተህ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤ​ላ​ዊው በና​ቡቴ እርሻ ጣለው፤ አን​ተና እኔ ጎን ለጎን በፈ​ረስ ተቀ​ም​ጠን አባ​ቱን አክ​ዓ​ብን በተ​ከ​ተ​ልን ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ይህን መከራ እንደ ተና​ገ​ረ​በት እኔ አስ​ባ​ለ​ሁና አን​ተም ታው​ቃ​ለ​ህና፤

26 በእ​ው​ነት የና​ቡ​ቴ​ንና የል​ጆ​ቹን ደም ትና​ን​ትና አይ​ቻ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ በዚ​ህም እርሻ እበ​ቀ​ለ​ዋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ረው ቃል ወስ​ደህ በእ​ር​ሻው ውስጥ ጣለው።”

27 የይ​ሁ​ዳም ንጉሥ አካ​ዝ​ያስ ያን ባየ ጊዜ በአ​ት​ክ​ልት ቤት መን​ገድ ሸሸ። ኢዩም፥ “እር​ሱ​ንም ደግሞ አል​ተ​ወ​ውም” ብሎ ተከ​ተ​ለው። በይ​ብ​ላ​ሄ​ምም አቅ​ራ​ቢያ ባለ​ችው በጋይ አቀ​በት በሰ​ረ​ገ​ላው ላይ ወጋው። ወደ መጊ​ዶም ሸሸ፥ በዚ​ያም ሞተ።

28 ብላ​ቴ​ኖ​ቹም በሰ​ረ​ገ​ላው ጭነው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወሰ​ዱት፥ በዳ​ዊ​ትም ከተማ በመ​ቃ​ብሩ ቀበ​ሩት።

29 በአ​ክ​ዓ​ብም ልጅ በኢ​ዮ​ራም በዐ​ሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት አካ​ዝ​ያስ በይ​ሁዳ ላይ ነገሠ።


የኤ​ል​ዛ​ቤል መገ​ደል

30 ኢዩም ወደ ኢይ​ዝ​ራ​ኤል ሄደ፤ ኤል​ዛ​ቤ​ልም ይህን በሰ​ማች ጊዜ ዐይ​ን​ዋን ተኳ​ለች፤ ራስ​ዋ​ንም አስ​ጌ​ጠች፤ በመ​ስ​ኮ​ትም ዘልቃ ትመ​ለ​ከት ነበር።

31 ኢዩም ወደ ከተማ በገባ ጊዜ፥ “ጌታ​ውን የገ​ደለ ዘምሪ ሰላም ነውን?” አለ​ችው።

32 ፊቱ​ንም አቅ​ንቶ በመ​ስ​ኮቱ አያት። “አንቺ ማን ነሽ? ወደ​ዚህ ወደ እኔ ውረጂ” አላት። ከዚ​ህም በኋላ ሁለት ጃን​ደ​ረ​ቦች ወደ እርሱ ተመ​ለ​ከቱ።

33 እር​ሱም፥ “ወደ ታች ወር​ው​ሩ​አት” አላ​ቸው፤ ወረ​ወ​ሩ​አ​ትም፥ ደም​ዋም በግ​ን​ቡና በፈ​ረ​ሶች መግ​ሪያ ላይ ተረጨ፥ ረገ​ጡ​አ​ትም።

34 ኢዩም ገብቶ በላ፤ ጠጣም፥ ከዝ​ያም በኋላ፥ “ሂዱ፥ ይህ​ችን የተ​ረ​ገ​መች እዩ​አት፤ የን​ጉሥ ልጅ ናትና ቅበ​ሩ​አት” አለ።

35 ሊቀ​ብ​ሩ​አ​ትም በሄዱ ጊዜ ከአ​ና​ቷና ከእ​ግ​ርዋ ተረ​ከዝ ከመ​ዳ​ፍ​ዋም በቀር ምንም አላ​ገ​ኙም።

36 ተመ​ል​ሰ​ውም ለኢዩ ነገ​ሩት፤ እር​ሱም፥ “በባ​ሪ​ያው በቴ​ስ​ብ​ያ​ዊው ኤል​ያስ እጅ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል እርሻ የኤ​ል​ዛ​ቤ​ልን ሥጋ ውሾች ይበ​ላሉ፥

37 የኤ​ል​ዛ​ቤ​ልም ሬሳ በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል እርሻ መሬት ላይ እንደ ፍግ ይሆ​ና​ልና ማንም፦ ይህች ኤል​ዛ​ቤል ናት ይል ዘንድ አይ​ች​ልም ብሎ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው” አለ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos