Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕዝራ 8:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ወደ አለ​ቆ​ቹም ወደ አል​ዓ​ዛር፥ ወደ አር​ኤል፥ ወደ ሰማ​አያ፥ ወደ ሀሎ​ናም፥ ወደ ያሪብ፥ ወደ ሄል​ና​ታን፥ ወደ ናታን፥ ወደ ዘካ​ር​ያስ፥ ወደ ሜሱ​ላም፥ ደግ​ሞም ወደ ዐዋ​ቂ​ዎቹ ወደ ዮያ​ሪ​ብና ወደ ሄል​ና​ታን ላክሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ስለዚህ መራሕያኑን አልዓዛርን፣ አርኤልን፣ ሸማያን፣ ኤልናታንን፣ ያሪብን፣ ኤልናታን፣ ናታንን፣ ዘካርያስንና ሜሱላምን እንዲሁም መምህራኑን ዮያሪብንና ኤልናታንን አስጠራኋቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ወደ አለቆቹም ወደ ኤሊዔዘር፥ አሪኤል፥ ሽማዕያ፥ ኤልናታን፥ ያሪብ፥ ኤልናታን፥ ናታን፥ ዘካርያስ፥ ሜሹላምና እንዲሁም ወደ መምህራኑ ወደ ዮያሪብና ኤልናታን ላክሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ስለዚህም ኤሊዔዘር፥ አሪኤል፥ ሸማዕያ፥ ኤልናታን፥ ያሪብ፥ ኤልናታን፥ ናታን፥ ዘካርያስና መሹላም ተብለው ወደሚጠሩ ዘጠኝ መሪዎች፥ እንዲሁም ዮያሪብና ኤልናታን ተብለው ወደሚጠሩ ሁለት መምህራን ላክሁባቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ወደ አለቆቹም ወደ አልዓዛር፥ ወደ አርኤል፥ ወደ ሸማያ፥ ወደ ኤልናታን፥ ወደ ያሪብ፥ ወደ ኤልናታን፥ ወደ ናታን፥ ወደ ዘካርያስ፥ ወደ ሜሱላም፥ ደግሞም ወደ አዋቂዎቹ ወደ ዮያሪብና ወደ ኤልናታን ላክሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዕዝራ 8:16
16 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ፍር​ድን ትለይ ዘንድ ለራ​ስህ ማስ​ተ​ዋ​ልን ለመ​ንህ እንጂ ለራ​ስህ ብዙ ዘመ​ና​ትን፥ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ንም፥ የጠ​ላ​ቶ​ች​ህ​ንም ነፍስ ሳት​ለ​ምን ይህን ነገር ለም​ነ​ሃ​ልና፥


እስ​ራ​ኤ​ልም የሚ​ገ​ባ​ውን ያደ​ርግ ዘንድ ዘመ​ኑን የሚ​ያ​ውቁ ጥበ​በ​ኞች ሰዎች የይ​ሳ​ኮር ልጆች አለ​ቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበሩ።


የም​ሥ​ራ​ቁም በር ዕጣ ለሰ​ሌ​ም​ያና ለዘ​ካ​ርያ ወደቀ። የዮ​አ​ስም ልጆች ለም​ል​ክያ ዕጣ ጣሉ፤ ዕጣ​ውም በሰ​ሜን በኩል ወጣ።


የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራ​ምም ደግሞ አለ፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ለመ​ን​ግ​ሥ​ቱም ቤት ይሠራ ዘንድ ጥበ​በ​ኛና ብል​ሃ​ተኛ፥ አስ​ተ​ዋ​ይም ልጅ ለን​ጉሡ ለዳ​ዊት የሰጠ፥ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን የፈ​ጠረ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ይሁን።


ከኤ​ራም ልጆ​ችም መሳ​ሔል፥ ኤልያ፥ ሴሚያ፥ ያሔል፥ ዖዝያ።


ሰሌ​ምያ፥ ናታን፥ ሐዳያ፤


ከኋ​ለ​ኞቹ ከአ​ዶ​ኒ​ቃም ልጆች ስማ​ቸው ይህ ነው፤ ኤሊ​ፋ​ልጥ፥ ይኢ​ኤል፥ ሰማ​አያ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ስድሳ ወን​ዶች።


ወደ አኅ​ዋም ወደ​ሚ​ፈ​ስስ ወንዝ ሰበ​ሰ​ብ​ኋ​ቸው፤ በዚ​ያም ሦስት ቀን ሰፈ​ርን፤ ሕዝ​ቡ​ንና ካህ​ና​ቱ​ንም ስቈ​ጥ​ራ​ቸው በዚያ ከሌዊ ልጆች ማን​ንም አላ​ገ​ኘ​ሁም።


በካ​ሲ​ፍያ ስፍራ ወደ ነበ​ረው ወደ አለ​ቃው ወደ አዶ ላክ​ኋ​ቸው፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤትም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን ያመ​ጡ​ልን ዘንድ በካ​ሲ​ፍያ ስፍራ ለሚ​ኖ​ሩት ለአ​ዶና ለወ​ን​ድ​ሞቹ ለና​ታ​ኒም የሚ​ነ​ግ​ሩ​አ​ቸ​ውን በአ​ፋ​ቸው አደ​ረ​ግሁ።


በላ​ያ​ች​ንም መል​ካም በሆ​ነው በአ​ም​ላ​ካ​ችን እጅ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጅ ከሌዊ ልጅ ከሞ​ሐሊ ልጆች ወገን የነ​በ​ረ​ውን አስ​ተ​ዋይ ሰው ሰራ​ብ​ያን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ዐሥራ ስም​ን​ቱን ልጆ​ቹ​ንና ወን​ድ​ሞ​ቹን አመ​ጡ​ልን።


እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፤ ከፊቱም ዕውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፤


ምክር በሰው ልብ እንደ ጥልቅ ውኃ ነው፤ አእምሮ ያለው ሰው ግን ይቀዳዋል።


የምለውን ተመልከት፤ ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ።


የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos