አሁንም በአንተ ላይ ክፉ ማድረግ በቻልሁ ነበር፤ ነገር ግን የአባትህ አምላክ ትናንት፦ በያዕቆብ ላይ ክፉ እንዳታደርግ ተጠንቀቅ ብሎ ነገረኝ።
ሚክያስ 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው! ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣ በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ሲነጋ በማለዳ ይፈጽሙታል፤ የሚያደርጉበት ኀይል በእጃቸው ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፋትን ለማድረግ በምስጢር ለሚያቅዱና በመኝታቸው ላይ ክፋ ነገርን ለሚሠሩ ወዮላቸው! ሲነጋ ይፈጽሙታል፥ ኃይል በእጃቸው ነውና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሥራ ለመሥራት ለሚያቅዱና በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ያን ለማድረግ ሥልጣን ስላላቸው ሌሊቱ ሲነጋ ዕቅዳቸውን በሥራ ላይ ያውሉታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው! ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል። |
አሁንም በአንተ ላይ ክፉ ማድረግ በቻልሁ ነበር፤ ነገር ግን የአባትህ አምላክ ትናንት፦ በያዕቆብ ላይ ክፉ እንዳታደርግ ተጠንቀቅ ብሎ ነገረኝ።
የእስራኤልም ንጉሥ የሀገሩን አለቆች ሁሉ ጠርቶ፥ “ተመልከቱ፤ ይህም ሰው ክፉ እንዲሻ እዩ፤ ስለ ሚስቶቼ ስለ ወንዶች ልጆቼና ሴቶች ልጆቼ ላከብኝ፤ ብሬንና ወርቄን ግን አልከለከልሁትም” አላቸው።
ስሕተተኞች ክፉን ያስባሉ፤ ደጋጎች ግን ምሕረትንና እውነትን ያስባሉ። ክፋትንም የሚሠሩ ምሕረትንና ይቅርታን አያውቁም። ነገር ግን ታማኝነትና ቸርነት ደግ በሚሠሩ ዘንድ ናቸው።
እግዚአብሔር ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከአለቆቻቸው ጋር ለፍርድ ይመጣል፤ እንዲህም ይላል፥ “ወይኔን አቃጥላችኋል፤ ከድሃው የበዘበዛችሁትም በቤታችሁ አለ፤
በዐመፃቸው ነገር ድሃውን ይገድሉት ዘንድ፥ የድሆችንም ፍርድ ይገለብጡ ዘንድ የክፉዎች ሕሊና ዐመፅን ትመክራለች።
ከጎረቤቶቻቸው እርሻ ይወስዱ ዘንድ፥ ምድርንም ለብቻቸው ይይዟት ዘንድ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ፥ እርሻንም ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!
እጃችሁ በደም ጣታችሁም በኀጢአት ተሞልትዋል፤ ከንፈራችሁም ዐመፅን ተናግሮአል፤ ምላሳችሁም ኀጢአትን አሰምቶአል።
እነርሱም፥ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፤ በኤርምያስ ላይ ምክርን እንምከር። ኑ፤ በምላስ እንምታው፤ ቃሉንም ሁሉ አናዳምጥ” አሉ።
ሰይፋችሁን ይዛችሁ ቆማችኋል፤ ርኩስ ነገርን ታደርጋላችሁ፤ የባልንጀሮቻችሁንም ሚስቶች ታስነውራላችሁ፤ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን? ስለዚህም እንዲህ በላቸው፦
አለቃውም ሕዝቡን ከይዞታቸው ያወጣቸው ዘንድ ከርስታቸው በግድ አይወሰድ፤ ሕዝቤ ሁሉ ከየይዞታቸው እንዳይነቀሉ ከገዛ ይዞታው ለልጆቹ ርስትን ይስጥ።”
ወዲያውም ማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎችና ከጻፎች ከሸንጎውም ሁሉ ጋር ከተማከሩ በኋላ፥ ኢየሱስን አሳስረው ወሰዱትና ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።
ያን ጊዜም የካህናት አለቆችና ጻፎች ሊይዙት ወደዱ፤ ይህን ስለ እነርሱ እንደ መሰለ ዐውቀዋልና፤ ነገር ግን ሕዝቡን ፈሩአቸው።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “ከሰማይ ካልተሰጠህ በቀር በእኔ ላይ አንዳች ሥልጣን የለህም፤ ስለዚህ ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢኣት አለበት” አለው።
በነጋም ጊዜ አይሁድ ተሰብስበው፥ ጳውሎስን እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተስማምተው ተማማሉ።
አሁንም እናንተ ከሸንጎው ጋር ወደ ሻለቃው ሂዱና የምትመረምሩትና የምትጠይቁት አስመስላችሁ ጳውሎስን እንዲያመጣው ንገሩት፤ እኛ ግን ወደ እናንተ ከመድረሱ አስቀድሞ ልንገድለው ቈርጠናል።”
ሐሜተኞች፥ እግዚአብሔርን የሚጠሉ፥ ተሳዳቢዎች፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክሕተኞች፥ ክፋትን የሚፈላለጉ፥ ለወላጆቻቸውም የማይታዘዙ ናቸው።
ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ ለሌላ ሕዝብ ይሰጣሉ፤ ራሳቸውንም ሲመቱአቸው በዐይኖችህ ታያለህ፤ ልታደርገውም የምትችለው የለም።