Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 23:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አሁ​ንም እና​ንተ ከሸ​ን​ጎው ጋር ወደ ሻለ​ቃው ሂዱና የም​ት​መ​ረ​ም​ሩ​ትና የም​ት​ጠ​ይ​ቁት አስ​መ​ስ​ላ​ችሁ ጳው​ሎ​ስን እን​ዲ​ያ​መ​ጣው ንገ​ሩት፤ እኛ ግን ወደ እና​ንተ ከመ​ድ​ረሱ አስ​ቀ​ድሞ ልን​ገ​ድ​ለው ቈር​ጠ​ናል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እንግዲህ እናንተ ከሸንጎው ጋራ ሆናችሁ፣ ስለ ጕዳዩ ትክክለኛ የሆነ ተጨማሪ መረጃ ከርሱ እንደምትፈልጉ አስመስላችሁ ጳውሎስን ወደ እናንተ እንዲሰድደው የጦር አዛዡን ለምኑት፤ እኛም ገና ወደዚህ ሳይደርስ ልንገድለው ዝግጁ ነን።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 እንግዲህ አሁን እናንተ ከሸንጎው ጋር ሆናችሁ ስለ እርሱ አጥብቃችሁ እንደምትመረምሩ መስላችሁ ወደ እናንተ እንዲያወርደው ለሻለቃው አመልክቱት፤ እኛም ሳይቀርብ እንድንገድለው የተዘጋጀን ነን፤” አሉአቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ እናንተ ከሸንጎው ጋር ተስማምታችሁ በጥብቅ የምትመረምሩት ነገር እንዳለ በማስመሰል ጳውሎስን እንዲያመጡላችሁ አዛዡን ጠይቁት፤ እኛም እዚህ ከመድረሱ በፊት ልንገድለው ተዘጋጅተናል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እንግዲህ አሁን እናንተ ከሸንጎው ጋር ሆናችሁ ስለ እርሱ አጥብቃችሁ እንደምትመረምሩ መስላችሁ ወደ እናንተ እንዲያወርደው ለሻለቃው አመልክቱት፤ እኛም ሳይቀርብ እንድንገድለው የተዘጋጀን ነን አሉአቸው።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 23:15
14 Referencias Cruzadas  

ኢዮ​ና​ዳ​ብም አለው፦“ ታም​ሜ​አ​ለሁ ብለህ በአ​ል​ጋህ ላይ ተኛ፤ አባ​ት​ህም ሊያ​ይህ ይመ​ጣል፦ እኅቴ ትዕ​ማር እን​ድ​ት​መ​ጣና እኔ የም​በ​ላ​ውን እን​ጀራ እን​ድ​ት​ሰ​ጠኝ፥ መብ​ሉ​ንም እኔ እያ​የሁ እን​ድ​ታ​በ​ስ​ል​ልኝ፥ ከእ​ጅ​ዋም እን​ድ​በ​ላው እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ በለው።”


ልጨ​ነቅ ቀር​ቤ​አ​ለ​ሁና፥ የሚ​ረ​ዳ​ኝም የለ​ምና ከእኔ አት​ራቅ።


እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና፥ ደም ለማፍሰስም ይፈጥናሉና።


ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ ከዐይናቸው እንቅልፋቸው ይወገዳል አይተኙምም።


እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውም ለተ​ን​ኮል ይሮ​ጣሉ፤ ደምን ለማ​ፍ​ሰ​ስም ይፈ​ጥ​ናሉ፤ ሰውን ለመ​ግ​ደል ይመ​ክ​ራሉ፤ ጕስ​ቍ​ል​ናና ቅጥ​ቃጤ በመ​ን​ገ​ዳ​ቸው አለ።


ጭፍ​ሮ​ችና የሺ አለ​ቃው፥ የአ​ይ​ሁ​ድም ሎሌ​ዎች ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይዘው አሰ​ሩት።


በማ​ግ​ሥ​ቱም የሻ​ለ​ቃው አይ​ሁድ የሚ​ከ​ሱት ስለ ምን እን​ደ​ሆነ ያውቅ ዘንድ ወደ​ደና ከእ​ስ​ራቱ ፈታው፤ ሊቃነ ካህ​ና​ቱና ሸን​ጎ​ውም ሁሉ እን​ዲ​መጡ አዘዘ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንም አም​ጥቶ በፊ​ታ​ቸው አቆ​መው።


ጳው​ሎ​ስም በአ​ደ​ባ​ባዩ ወደ​አ​ሉት ሰዎች አተ​ኵሮ ተመ​ለ​ከ​ተና፥ “እና​ንተ ሰዎች ወን​ድ​ሞች፥ እኔስ እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ በመ​ል​ካም ሕሊና ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሳገ​ለ​ግል ኑሬ​አ​ለሁ” አላ​ቸው።


ጳው​ሎ​ስም እኩ​ሌ​ቶቹ ሰዱ​ቃ​ው​ያን እኩ​ሌ​ቶ​ቹም ፈሪ​ሳ​ው​ያን እንደ ሆኑ ዐውቆ፥ “እኔ ፈሪ​ሳዊ የፈ​ሪ​ሳዊ ልጅ ነኝ፤ ስለ ተስ​ፋና ስለ ሙታን መነ​ሣ​ትም ይፈ​ረ​ድ​ብ​ኛል” ብሎ በአ​ደ​ባ​ባይ ጮኸ።


ልኮም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አደ​ባ​ባይ እን​ዲ​ያ​ስ​መ​ጣ​ውና እን​ዲ​ሰ​ጣ​ቸው ለመ​ኑት፤ እነ​ርሱ ግን ወደ​ዚያ ሄደው በመ​ን​ገድ ሸም​ቀው ሊገ​ድ​ሉት ፈል​ገው ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos