Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 5:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ቸው እርሻ ይወ​ስዱ ዘንድ፥ ምድ​ር​ንም ለብ​ቻ​ቸው ይይ​ዟት ዘንድ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚ​ያ​ያ​ይዙ፥ እር​ሻ​ንም ከእ​ርሻ ጋር ለሚ​ያ​ቀ​ራ​ርቡ ወዮ​ላ​ቸው!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስፍራ ለሌሎች እስከማይተርፍ፣ ቤትን በቤት ላይ በመጨመር፣ መሬትን ከመሬት ጋራ በማያያዝ፣ ለብቻችሁ በምድር ተስፋፍታችሁ ለምትኖሩ ወዮላችሁ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ምንም ስፍራ ለሌሎች እስከማይተርፍ ድረስ፤ ቤትን በቤት ላይ በመጨመር፤ መሬትን ከመሬት ጋር በማያያዝ፤ ለብቻችሁ በምድር ተስፋፍታችሁ ለምትኖሩ ወዮላችሁ!

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በአገሪቱ ላይ መኖር የሚገባችሁ እናንተ ብቻ መስሎአችሁ፥ ቀድሞ በነበራችሁ ይዞታ ላይ ለመቀላቀል ሰዎችን ሁሉ እያስወጣችሁ ቤትን ከቤት ማያያዝና እርሻንም በእርሻ ላይ ለመቀላቀል ለምትፈልጉ ወዮላችሁ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ስፍራ እስከማይቀር ድረስ እናንተም በምድር ላይ ብቻችሁን እስክትቀመጡ ድረስ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ እርሻን ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 5:8
14 Referencias Cruzadas  

በእርሻው ላይ ይመኛሉ፥ በግዴታም ይይዙታል፥ በቤቶችም ላይ ይመኛሉ፥ ይወስዱአቸውማል፥ ሰውንና ቤቱን፥ ሰውንና ርስቱንም ይነጥቃሉ።


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


“የሰው ልጅ ሆይ! በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር በአሉ በባ​ድማ ስፍ​ራ​ዎች የተ​ቀ​መጡ፦ አብ​ር​ሃም ብቻ​ውን ሳለ ምድ​ሪ​ቱን ወረሰ፤ እኛም ብዙ​ዎች ነን፤ ምድ​ሪ​ቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰ​ጥ​ታ​ለች ይላሉ። ስለ​ዚህ እን​ዲህ በላ​ቸው፦


“የሰው ልጅ ሆይ! በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖሩ፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ራቁ፤ ይህች ምድር ርስት ሆና ለእኛ ተሰ​ጥ​ታ​ለች የሚ​ሉ​አ​ቸው ወን​ድ​ሞ​ች​ህና ዘመ​ዶ​ችህ፥ የም​ርኮ ሰዎ​ች​ህም ሁሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ ያል​ቃሉ።


በተ​ፈ​ቱም ከተ​ሞች ውስጥ ይኖ​ራል፥ ሰውም በሌ​ለ​ባ​ቸው ቤቶች ይገ​ባል፥ እርሱ ያዘ​ጋ​ጀ​ው​ንም ሌሎች ይወ​ስ​ዱ​ታል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ዳር​ቻ​ቸ​ውን ያሰፉ ዘንድ የገ​ለ​ዓ​ድን ነፍሰ ጡሮች ቀድ​ደ​ዋ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የአ​ሞን ልጆች ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስም።


ለሀ​ብቱ ትርፍ የለ​ውም፤ ስለ​ዚህ በረ​ከቱ አት​ከ​ና​ወ​ን​ለ​ትም።


መማለጃን የሚቀበል ራሱን ያጠፋል፤ መማለጃ መቀበልን የሚጠላ ግን ይድናል። በምጽዋትና በእምነት ኀጢአት ይሰረያል። እግዚአብሔርንም በመፍራት ክፉ ሁሉ ይወገዳል።


በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው! ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል።


እነዚህ ሁሉ፦ ለእርሱ ያልሆነውን ወደ እርሱ ለሚሰበስብ መያዣውንም ለራሱ የሚያበዛ ወዮለት! እስከ መቼ ነው? እያሉ ምሳሌ አይመስሉበትምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios