በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ ይቅርም በል፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ሁሉ ልብ ታውቃለህና ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለውና ስጠው።
ኢያሱ 22:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ጌታም ነው፤ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ ነው፤ እርሱ ያውቃል። እስራኤልም ያውቀዋል። በእግዚአብሔር ፊት ያደረግነው ለበደልና ለመካድ ከሆነ ዛሬ አያድነን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ኀያሉ አምላክ፣ እግዚአብሔር! ኀያሉ አምላክ፣ እግዚአብሔር! እርሱ ያውቃል! እስራኤልም ይህን ይወቅ! ይህ የተደረገው በማመፅ ወይም ለእግዚአብሔር ባለመታዘዝ ከሆነ፣ ዛሬ አትማሩን! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የአማልክት አምላክ ጌታ! የአማልክት አምላክ ጌታ! እርሱ አውቆታል፥ እስራኤልም ራሱ ይወቀው፤ በጌታ ላይ ዐምፀንና ተላልፈን እንደሆነ ዛሬ አታድነን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል እግዚአብሔር ነው! እርሱ የሁሉ ጌታ ነው! እርሱ ከሁሉ የሚበልጥ ኀያል አምላክ ነው! እኛ ስለምን ይህን እንደ ሠራን እርሱ ያውቃል፤ እናንተም ስለምን እንደ ሠራነው እንድታውቁት እንፈልጋለን፤ በእውነት ካመፅንና በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት አጓድለን ከተገኘን፥ በሕይወት እንድንኖር አትፍቀዱልን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር፥ የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር እርሱ አውቆታል፥ እስራኤልም ያውቀዋል፥ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀንና ተላልፈን እንደ ሆነ ዛሬ አታድነን፥ |
በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ ይቅርም በል፤ አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ሁሉ ልብ ታውቃለህና ልቡን ለምታውቀው ሰው ሁሉ እንደ መንገዱ ሁሉ መጠን ክፈለውና ስጠው።
አንተ ግን አቤቱ! ዐውቀኸኛል፤ አይተኸኛል፤ ልቤንም በፊትህ ፈትነሃል፤ እንደ በጎች ለመታረድ ጐትተህ ለያቸው፤ ለመታረድም ቀን አዘጋጃቸው።
እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱና፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ፤ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።”
በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን ለእኔ እስኪያደርግ ድረስ ቍጣውን እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቅንም አያለሁ።
ሦስተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?” አለው፤ ጴጥሮስም ሦስት ጊዜ ትወደኛለህን? ስላለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እኔም እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው፤ “እንኪያስ ግልገሎችን ጠብቅ” አለው።
ከበደልሁ ወይም ለሞት የሚያበቃኝ የሠራሁት ክፉ ሥራ ካለ ሞት አይፈረድብኝ አልልም፤ ነገር ግን እነዚህ በደል የሌለብኝን በከንቱ የሚከስሱኝ ከሆነ፥ ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ ለማን ይቻለዋል? እኔ ወደ ቄሣር ይግባኝ ብያለሁ።”
ለዘለዓለም ቡሩክ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ሐሰት እንደማልናገር ያውቃል።
እግዚአብሔርን መፍራት ዐውቀን ሰዎችን እናሳምናለን፤ ለእግዚአብሔር ግን እኛ የተገለጥን ነን፤ እንዲሁም በልቡናችሁ የተገለጥን እንደ ሆን እንታመናለን።
አምላካችሁ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፥ የጌቶች ጌታ፥ ታላቅ አምላክ፥ ኀያልም፥ የሚያስፈራም፥ በፍርድም የማያደላ፥ መማለጃም የማይቀበል ነውና።
እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኀይል ይሁን፤ አሜን።
እኛን በሚቈጣጠር በእርሱ በዐይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቈተና የተገለጠ ነው እንጂ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።
ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።
ኀጢኣት እንደ ምዋርተኝነት ናትና አምልኮተ ጣዖትም ደዌንና ኀዘንን ያመጣል። የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ” አለው።
አትመኩ፤ የኵራት ነገሮችንም አትናገሩ፤ ፅኑዕ ነገርም ከአፋችሁ አይውጣ፤ እግዚአብሔር አምላክ ዐዋቂ ነውና፥ እግዚአብሔርም ዙፋኑን ያዘጋጃል።