Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 97:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ባሕር በሞ​ላዋ፥ ዓለ​ምም በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖሩ ሁሉ ይና​ወጡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ፣ በጣዖታትም የሚመኩ ሁሉ ይፈሩ፤ እናንተ አማልክት ሁሉ፤ ለርሱ ስገዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፥ አማልክት በሙሉ፥ ስገዱለት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ለጣዖቶች የሚሰግዱና በእነርሱ የሚመኩ ሁሉ ያፍራሉ፤ እናንተ ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ ለእግዚአብሔር ስገዱ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 97:7
19 Referencias Cruzadas  

የእ​ነ​ዚ​ህም ኪሩ​ቤል ክን​ፎች ሃያ ክንድ ሙሉ ተዘ​ር​ግ​ተው ነበር፤ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም ቆመው ነበር፤ ፊቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ይመ​ለ​ከቱ ነበር።


“በላይ በሰ​ማይ ከአ​ለው፥ በታ​ችም በም​ድር ከአ​ለው፥ ከም​ድ​ርም በታች በውኃ ከአ​ለው ነገር የማ​ና​ቸ​ው​ንም ምስል ለአ​ንተ አም​ላክ አታ​ድ​ርግ።


ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ላይ ይዘ​ረ​ጋሉ፤ የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ው​ንም በክ​ን​ፎ​ቻ​ቸው ይሸ​ፍ​ናሉ፤ ፊታ​ቸ​ውም እርስ በርሱ ይተ​ያ​ያል፤ የኪ​ሩ​ቤ​ልም ፊቶ​ቻ​ቸው ወደ ስር​የት መክ​ደ​ኛው ይሁን።


የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም በከ​ንቱ ይሠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል።


በተ​ቀ​ረ​ጹ​ትም ምስ​ሎች የሚ​ታ​መኑ፥ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎች፥ “አም​ላ​ኮ​ቻ​ችን ናችሁ” የሚሉ ወደ ኋላ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ ፈጽ​መ​ውም ያፍ​ራሉ።


የዕ​ው​ራ​ን​ንም ዐይን ትከ​ፍት ዘንድ፥ የተ​ጋ​ዙ​ት​ንም ከግ​ዞት ቤት፥ በጨ​ለ​ማም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከወ​ህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ።


የሚ​ቃ​ወ​ሙት ሁሉም ያፍ​ራሉ፤ ይዋ​ረ​ዱ​ማል፤ አፍ​ረ​ውም ይሄ​ዳሉ።


ሰው ሁሉ ዕው​ቀት አጥቶ ሰን​ፎ​አል፤ አን​ጥ​ረ​ኛም ሁሉ ከቀ​ረ​ጸው ምስል የተ​ነሣ አፍ​ሮ​አል፤ ቀልጦ የተ​ሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስ​ት​ን​ፋ​ስም የለ​ው​ምና።


ሌባ በተ​ያዘ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ያ​ፍር፤ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ እነ​ር​ሱና ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውም፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ያፍ​ራሉ።


“ለእ​ና​ንተ በእጅ የተ​ሠራ ጣዖት አታ​ድ​ርጉ፤ የተ​ቀ​ረ​ጸም ምስል ወይም ሐው​ልት አታ​ቁሙ፤ ትሰ​ግ​ዱ​ለ​ትም ዘንድ በም​ድ​ራ​ችሁ ላይ የተ​ቀ​ረጸ ድን​ጋይ አታ​ኑሩ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ጠላ የሠ​ራ​ተኛ እጅ ሥራን፥ የተ​ቀ​ረፀ ወይም ቀልጦ የተ​ሠራ ምስ​ልን የሚ​ያ​ደ​ርግ፥ በስ​ው​ርም የሚ​ያ​ቆ​መው ሰው ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ መል​ሰው አሜን ይላሉ።


“በላይ በሰ​ማይ ካለው፥ በታ​ችም በም​ድር ካለው፥ ከም​ድ​ርም በታች በውኃ ካለው ነገር ማን​ኛ​ው​ንም ምሳሌ፥ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ው​ንም ምስል ለአ​ንተ አታ​ድ​ርግ፤


ዳግ​መ​ኛም በኵ​ርን ወደ ዓለም በላ​ከው ጊዜ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክት ሁሉ ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል” አለ።


ለእነርሱም ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን ባወሩላችሁ ነገር እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፤ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።


በነ​ጋ​ውም የአ​ዛ​ጦን ሰዎች ማለዱ፤ ወደ ዳጎ​ንም ቤት ገቡ፤ እነ​ሆም፥ ዳጎን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት በም​ድር ላይ በግ​ን​ባሩ ወድቆ አገ​ኙት፤ ዳጎ​ን​ንም አን​ሥ​ተው በስ​ፍ​ራው አቆ​ሙት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos