Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -


መዝሙር 82 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


የአ​ሳፍ የም​ስ​ጋና መዝ​ሙር።

1 አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አት​በል፥ ቸልም አት​በል።

2 እነሆ፥ ጠላ​ቶ​ችህ ጮኸ​ዋ​ልና፥ ጠላ​ቶ​ች​ህም ራሳ​ቸ​ውን አን​ሥ​ተ​ዋ​ልና።

3 ሕዝ​ብ​ህን በም​ክር ሸነ​ገ​ሉ​አ​ቸው፥ በቅ​ዱ​ሳ​ን​ህም ላይ ተማ​ከሩ።

4 “ኑ ከሕ​ዝብ ለይ​ተን እና​ጥ​ፋ​ቸው፥ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ስም አያ​ስቡ” አሉ።

5 በአ​ን​ድ​ነት ተካ​ክ​ለው ተማ​ክ​ረ​ዋ​ልና፤ በአ​ንተ ላይ ሤራ ቈረጡ፤ ቃል ኪዳ​ንም አደ​ረጉ፤

6 የኤ​ዶ​ም​ያስ ወገ​ኖች፥ እስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም፥ ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም፥ አጋ​ራ​ው​ያ​ንም፥

7 ጌባል፥ አሞ​ንም፥ አማ​ሌ​ቅም፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ከጢ​ሮስ ሰዎች ጋር፤

8 አሦ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ተባ​በረ፥ ለሎጥ ልጆ​ችም ረዳት ሆኑ​አ​ቸው።

9 እንደ ምድ​ያ​ምና እንደ ሲሣራ፥ በቂ​ሶ​ንም ወንዝ እንደ ኢያ​ቢስ አድ​ር​ግ​ባ​ቸው።

10 እንደ ዕን​ዶር ሰዎች ይጥፉ እንደ ምድር ትቢያ ይሁኑ።

11 አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውን እንደ ሔሬ​ብና እንደ ዜብ፥ ታላ​ላ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ እንደ ዛብ​ሄ​ልና እንደ ስል​ማና አድ​ር​ጋ​ቸው።

12 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሠ​ዊያ እን​ወ​ር​ሳ​ለን የሚ​ሉ​ትን።

13 አም​ላኬ ሆይ፥ እንደ መን​ኰ​ራ​ኵር፥ በእ​ሳት ፊትም እንደ አለ ገለባ አድ​ር​ጋ​ቸው።

14 እሳት ዱርን እን​ደ​ሚ​ያ​ቃ​ጥል፥ ነበ​ል​ባ​ልም ተራ​ሮ​ችን እን​ደ​ሚ​ያ​ነ​ድድ፥

15 እን​ዲሁ በቍ​ጣህ አሳ​ድ​ዳ​ቸው፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም አስ​ደ​ን​ግ​ጣ​ቸው።

16 በፊ​ታ​ቸው እፍ​ረ​ትን ሙላ፥ አቤቱ፥ ስም​ህን ይወቁ።

17 ይፈሩ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙም ይታ​ወኩ፤ ይጐ​ስ​ቍሉ፥ ይጥ​ፉም።

18 ስም​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነ፥ በም​ድር ሁሉ ላይም አንተ ብቻ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ።

Síguenos en:



Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos