Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 25:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከበ​ደ​ልሁ ወይም ለሞት የሚ​ያ​በ​ቃኝ የሠ​ራ​ሁት ክፉ ሥራ ካለ ሞት አይ​ፈ​ረ​ድ​ብኝ አል​ልም፤ ነገር ግን እነ​ዚህ በደል የሌ​ለ​ብ​ኝን በከ​ንቱ የሚ​ከ​ስ​ሱኝ ከሆነ፥ ለእ​ነ​ርሱ አሳ​ልፎ ሊሰ​ጠኝ ለማን ይቻ​ለ​ዋል? እኔ ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ብያ​ለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ይሁን እንጂ ለሞት የሚያበቃ በደል ከተገኘብኝ፣ አልሙት አልልም፤ እነዚህ አይሁድ የሚያቀርቡብኝ ክስ እውነት ካልሆነ ግን፣ እኔን ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጥ የሚችል የለም፤ ወደ ቄሳር ይግባኝ ብያለሁ!”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እንግዲህ በድዬ ወይም ሞት የሚገባውን ነገር አድርጌ እንደሆነ ከሞት ልዳን አልልም፤ እነዚህ የሚከሱኝ ክስ ከንቱ እንደሆነ ግን ለእነርሱ አሳልፎ ይሰጠኝ ዘንድ ማንም አይችልም፤ ወደ ቄሣር ይግባኝ ብዬአለሁ፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በደለኛ ከሆንኩ ወይም በሞት የሚያስቀጣ በደል ካደረግሁ ከሞት ልዳን አልልም፤ ነገር ግን የእነርሱ ክስ ከንቱ ከሆነ ማንም ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ አይችልም፤ እኔ ወደ ሮማ ንጉሠ ነገሥት ይግባኝ ብዬአለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እንግዲህ በድዬ ወይም ሞት የሚገባውን ነገር አድርጌ እንደ ሆነ ከሞት ልዳን አልልም፤ እነዚህ የሚከሱኝ ክስ ከንቱ እንደሆነ ግን ለእነርሱ አሳልፎ ይሰጠኝ ዘንድ ማንም አይችልም፤ ወደ ቄሳር ይግባኝ ብዬአለሁ” አለ።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 25:11
17 Referencias Cruzadas  

አይ​ሁድ ግን ሊቃ​ወ​ሙኝ በተ​ነሡ ጊዜ ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ለማ​ለት ግድ ሆነ​ብኝ፤ ነገር ግን ወገ​ኖ​ችን የም​ከ​ስ​በት ነገር ኖሮኝ አይ​ደ​ለም።


አግ​ሪ​ጳም ፊስ​ጦ​ስን፥ “ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ባይል ኖሮ ይህ ሰው ይፈታ ዘንድ በተ​ገባ ነበር” አለው።


እኔ ግን ለሞት የሚ​ያ​ደ​ር​ሰው በደል እን​ዳ​ል​ሠራ እጅግ መር​ምሬ፥ እር​ሱም ራሱ ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ማለ​ትን ስለ​ወ​ደደ እን​ግ​ዲህ ልል​ከው ቈር​ጫ​ለሁ።


ጳው​ሎስ ግን እንቢ ብሎ፥ እን​ዲ​ድን ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ አለ፤ ከዚ​ህም በኋላ ወደ ቄሣር እስ​ክ​ል​ከው ድረስ እን​ዲ​ጠ​ብ​ቁት አዘ​ዝሁ።”


እነዚያም ጌታን ኢየሱስን ደግሞ ገደሉ፤ ነቢያትንም እኛንም አሳደዱ፤ እግዚአብሔርንም ደስ አያሰኙም፤ ሰዎችንም ሁሉ ይቃወማሉ፤


ጳው​ሎ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፤ “እኔ ወደ ቄሣር ዙፋን ችሎት እቀ​ር​ባ​ለሁ፤ ፍር​ዴም በዚያ ሊታ​ይ​ልኝ ይገ​ባል፤ በአ​ይ​ሁ​ድም ላይ የበ​ደ​ል​ሁት በደል እን​ደ​ሌ​ለኝ ከሰው ሁሉ ይልቅ አንተ ራስህ ታው​ቃ​ለህ።


ሊገ​ር​ፉ​ትም በአ​ጋ​ደ​ሙት ጊዜ ጳው​ሎስ በአ​ጠ​ገቡ የነ​በ​ረ​ውን የመቶ አለቃ፥ “የሮ​ማን ሰው ያለ ፍርድ ልት​ገ​ርፉ ይገ​ባ​ች​ኋ​ልን?” አለው።


ጳው​ሎ​ስም ይመ​ል​ስ​ላ​ቸው ዘንድ አፉን ሊከ​ፍት ወድዶ ሳለ አገረ ገዢው ጋል​ዮስ መልሶ አይ​ሁ​ድን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ አይ​ሁድ ሆይ፥ የበ​ደ​ላ​ችሁ በደል ቢኖር፥ ወይም ሌላ በደል ቢኖ​ር​በት አቤ​ቱ​ታ​ች​ሁን በሰ​ማ​ሁና ባከ​ራ​ከ​ር​ኋ​ችሁ ነበር።


ጳው​ሎስ ግን፥ “እኛ የሮም ሰዎች ስን​ሆን፥ ያለ ፍርድ በአ​ደ​ባ​ባይ ገረ​ፉን፤ አሰ​ሩ​ንም፤ አሁ​ንም በስ​ውር ሊያ​ወ​ጡን ይሻሉ፤ አይ​ሆ​ንም፥ ራሳ​ቸው መጥ​ተው ያው​ጡን” አላ​ቸው።


ብዙ ረዳት እን​ዳ​ለኝ ተማ​ምኜ በድ​ሃ​አ​ደጉ ላይ እጄን አን​ሥቼ እንደ ሆነ፥


ዳዊ​ትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳ​ኦል እጅ እሞ​ታ​ለሁ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ምድር ከመ​ሸሸ በቀር የሚ​ሻ​ለኝ የለም፤ ሳኦ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል አው​ራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም ከእጁ እድ​ና​ለሁ” አለ።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነው፤ ጌታም ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ ነው፤ እርሱ ያው​ቃል። እስ​ራ​ኤ​ልም ያው​ቀ​ዋል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ግ​ነው ለበ​ደ​ልና ለመ​ካድ ከሆነ ዛሬ አያ​ድ​ነን፤


ኤር​ም​ያ​ስም ደግሞ ንጉ​ሡን ሴዴ​ቅ​ያ​ስን እን​ዲህ አለው፥ “በግ​ዞት ቤት የጣ​ላ​ች​ሁኝ አን​ተን፥ ወይስ አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህን፥ ወይስ ሕዝ​ብ​ህን ምን በድ​ያ​ችሁ ነው?


ከዚ​ህም በኋላ ፊስ​ጦስ ከአ​ማ​ካ​ሪ​ዎቹ ጋር ተማ​ክሮ፥ “ወደ ቄሣር ይግ​ባኝ ካልህ ወደ ቄሣር ትሄ​ዳ​ለህ” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios