Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 11:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ስለ​ምን ነው? አል​ወ​ዳ​ች​ሁ​ምና ነውን? እን​ደ​ም​ወ​ድ​ዳ​ች​ሁስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያው​ቃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ይህን የምለው ለምንድን ነው? ስለማልወድዳችሁ ነውን? እንደምወድዳችሁ እግዚአብሔር ያውቃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ስለምን? ስለማልወዳችሁ ይመስላችኋል? እንደምወዳችሁ እግዚአብሔር ያውቃል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ምክንያቱስ ምንድን ነው? ስለማልወዳችሁ ነውን? እንደምወዳችሁስ እግዚአብሔር ያውቃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ስለ ምን? ስለማልወዳችሁ ነውን? እግዚአብሔር ያውቃል።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 11:11
15 Referencias Cruzadas  

ሦስ​ተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ጴጥ​ሮ​ስም ሦስት ጊዜ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን? ስላ​ለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታው​ቃ​ለህ፤ እኔም እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “እን​ኪ​ያስ ግል​ገ​ሎ​ችን ጠብቅ” አለው።


ልብን የሚ​ያ​ውቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለእኛ እንደ ሰጠን መን​ፈስ ቅዱ​ስን በመ​ስ​ጠት መሰ​ከ​ረ​ላ​ቸው።


ባለ​ማ​ቋ​ረጥ በም​ጸ​ል​የው ጸሎት እን​ደ​ማ​ስ​ባ​ችሁ ልጁ በአ​ስ​ተ​ማ​ረው ወን​ጌል በፍ​ጹም ልቡ​ናዬ የማ​መ​ል​ከው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምስ​ክሬ ነው።


የክ​ር​ስ​ቶስ ዕው​ነት አብ​ሮኝ ይኖ​ራ​ልና፥ ይህቺ ደስ​ታዬ በአ​ካ​ይያ አው​ራጃ አል​ተ​ከ​ለ​ከ​ለ​ች​ብ​ኝም።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም ቡሩክ አም​ላክ የሆነ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አባት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሐሰት እን​ደ​ማ​ል​ና​ገር ያው​ቃል።


እኔ ግን እጥፍ ድርብ አወ​ጣ​ለሁ፤ ስለ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ሰው​ነ​ቴን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እና​ን​ተ​ንም እጅግ ብወ​ዳ​ችሁ ራሴን ወደ​ድሁ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በሌላ ቀላ​ቅ​ለው እን​ደ​ሚ​ሸ​ቅጡ እንደ ብዙ​ዎች አይ​ደ​ለ​ን​ምና፤ በቅ​ን​ነት ግን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተላከ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በክ​ር​ስ​ቶስ እን​ና​ገ​ራ​ለን።


ይህ​ንም የም​ለው በእ​ና​ንተ ለመ​ፍ​ረድ አይ​ደ​ለም፤ ለሞ​ትም፥ ለሕ​ይ​ወ​ትም ቢሆን እና​ንተ በል​ባ​ችን እን​ዳ​ላ​ችሁ ፈጽሜ ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና።


እኛን በሚ​ቈ​ጣ​ጠር በእ​ርሱ በዐ​ይ​ኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተ​ራ​ቈ​ተና የተ​ገ​ለጠ ነው እንጂ በእ​ርሱ ፊት የተ​ሰ​ወረ ፍጥ​ረት የለም።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነው፤ ጌታም ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ማ​ል​ክት አም​ላክ ነው፤ እርሱ ያው​ቃል። እስ​ራ​ኤ​ልም ያው​ቀ​ዋል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያደ​ረ​ግ​ነው ለበ​ደ​ልና ለመ​ካድ ከሆነ ዛሬ አያ​ድ​ነን፤


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos