ሚክያስም አለ፥ “እንዲህ አይደለም፤ የእግዚአብሔርን ቃል የሰማሁት እኔ አይደለሁምን? እንዲህ አይደለም፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።
ኤርምያስ 7:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በእግዚአብሔር ቤት በር ቁም፤ ይህንም ቃል እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ለእግዚአብሔር ትሰግዱ ዘንድ በእነዚህ በሮች የምትገቡ ከይሁዳ ያላችሁ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በእግዚአብሔር ቤት በር ቁም፤ በዚያም ይህን መልእክት ዐውጅ፤ “ ‘እግዚአብሔርን ለማምለክ በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ሕዝብ ሁላችሁ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በጌታ ቤት በር ቁም፥ ይህንም ቃል በዚያ እንዲህ ብለህ አውጅ፦ ጌታን ልታመልኩ በእነዚህ በሮች የምትገቡ የይሁዳ ሰዎች ሆይ! ሁላችሁ የጌታን ቃል ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ቤት በር ቁም፥ ይህንም ቃል እንዲህ ብለህ ተናገር፦ እግዚአብሔርን ልታመልኩ በእነዚህ በሮች የምትገቡ ከይሁዳ ያላችሁ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። |
ሚክያስም አለ፥ “እንዲህ አይደለም፤ የእግዚአብሔርን ቃል የሰማሁት እኔ አይደለሁምን? እንዲህ አይደለም፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።
እነሆ፥ የባሪያዎች ዐይኖች ወደ ጌቶቻቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የባሪያዪቱም ዐይን ወደ እመቤቷ እጅ እንደ ሆነ፥ እንዲሁም ይቅር እስከሚለን ድረስ ዐይኖቻችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ናቸው።
እናንተ የሰዶም አለቆች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሕዝብ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ሕግ አድምጡ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ይህችን ቃል ሁሉ በይሁዳ ከተሞችና በኢየሩሳሌም አደባባይ ተናገር፤ እንዲህም በል፦ የዚህን ቃል ኪዳን ቃል ስሙ፤ አድርጉትም።
ኤርምያስም እግዚአብሔር ትንቢት ሊናገር ወደዚያ ልኮት ከነበረው ስፍራ ከቶፌት ተመለሰ፤ በእግዚአብሔርም ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አላቸው፦
“ሂድ፤ እንዲህ ብለህ በኢየሩሳሌም ጆሮ ተናገር፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ምሕረት፥ የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስቤአለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ ቁም፤ በእግዚአብሔርም ቤት ውስጥ ይሰግዱ ዘንድ ለሚመጡት ለይሁዳ ከተሞች ሁሉ ትነግራቸው ዘንድ ያዘዝሁህን ቃል ሁሉ ተናገራቸው፤ አንዲትም ቃል አታጕድል።
“ነገር ግን የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ በሰይፍ አትሞትም፤
ባሮክም የኤርምያስን ቃል በእግዚአብሔር ቤት በላይኛው አደባባይ በእግዚአብሔር ቤት በአዲሱ በር መግቢያ ባለው በጸሓፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ክፍል በሕዝቡ ሁሉ ጆሮ በመጽሐፉ አንበበ።
አንተ ግን ገብተህ ከአፌ የጻፍኸውን የእግዚአብሔርን ቃል በጾም ቀን በእግዚአብሔር ቤት በሕዝቡ ጆሮ በክርታሱ አንብብ፤ ደግሞም ከከተሞቻቸው በሚወጡ በይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አንብበው።
ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ፥ ለሴቶቹም ሁሉ እንዲህ አለ፥ “በግብፅ ምድር የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
የእግዚአብሔርም እጅ በላዬ ነበረ፤ እግዚአብሔርም በመንፈሱ አወጣኝ፤ አጥንቶችም በሞሉበት ሸለቆ መካከል አኖረኝ።
ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! አድምጡ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ ለሚመለከት ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።
አሁንም የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ አንተ፦ በእስራኤል ላይ ትንቢት አትናገር፥ የያዕቆብንም ቤት አትዘብዝባቸው ብለሃል።
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፥ “እኔ ለዓለም በግልጥ ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብም፥ በቤተ መቅደስም ሁልጊዜ አስተማርሁ፤ በስውርም የተናገርሁት አንዳች ነገር የለም።
ሁልጊዜም በቤተ መቅደስና በቤት ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ማስተማርንና መስበክን አልተዉም።
መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።