Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ራእይ 2:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለሚነሣ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤ ደግሞም ከሚቀበለው ሰው በቀር ማንም የማያውቀው አዲስ ስም የተጻፈበትን ነጭ ድንጋይ እሰጠዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፤ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፤ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር ማንም የማያውቀው አዲስ ስም ተጽፎአል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያን የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ! ድል ለሚነሣ ከተሰወረው መና እሰጠዋለሁ፤ አዲስ ስም የተጻፈበትን ነጭ ድንጋይም እሰጠዋለሁ፤ ከተቀባዩ በቀር ይህን ሌላ ማንም አያውቀውም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው ከተሰወረ መና እሰጠዋለሁ፥ ነጭ ድንጋይንም እሰጠዋለሁ፥ በድንጋዩም ላይ ከተቀበለው በቀር አንድ ስንኳ የሚያውቀው የሌለ አዲስ ስም ተጽፎአል።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 2:17
24 Referencias Cruzadas  

አሕ​ዛብ ጽድ​ቅ​ሽን፥ ነገ​ሥ​ታ​ትም ሁሉ ክብ​ር​ሽን ያያሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አፍ በሚ​ጠ​ራ​በት በአ​ዲሱ ስም ትጠ​ሪ​ያ​ለሽ።


ስማ​ች​ሁ​ንም እኔ ለመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው ሕዝቤ ጥጋብ አድ​ር​ጋ​ችሁ ትተ​ዋ​ላ​ችሁ፤ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያጠ​ፋ​ች​ኋል፤ ባሪ​ያ​ዎች ግን በሐ​ዲስ ስም ይጠ​ራሉ።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል የነሣው በሁለተኛው ሞት አይጐዳም።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።


በዙፋኑም ፊት በአራቱም እንስሶችና በሽማግሌዎቹ ፊት አዲስ ቅኔ ዘመሩ፤ ከምድርም ከተዋጁት ከመቶ አርባ አራት ሺህ በቀር ያን ቅኔ ሊማር ለማንም አልተቻለውም።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።”


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።


እና​ንተ ፈጽ​ማ​ችሁ ሞታ​ች​ኋ​ልና፤ ሕይ​ወ​ታ​ች​ሁም ከክ​ር​ስ​ቶስ ጋራ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ሠ​ወ​ረች ናትና።


ለሥ​ጋዊ ሰው ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነገር ሞኝ​ነት ይመ​ስ​ለ​ዋ​ልና፥ አይ​ቀ​በ​ለ​ውም፤ በመ​ን​ፈ​ስም የሚ​መ​ረ​መር ስለ​ሆነ ሊያ​ውቅ አይ​ች​ልም።


እርሱም መልሶ እንዲህ አላቸ “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ይበ​ላሉ፤ እና​ንተ ግን ትራ​ባ​ላ​ችሁ፤ እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ይጠ​ጣሉ፤ እና​ንተ ግን ትጠ​ማ​ላ​ችሁ፤ እነሆ፥ ባሪ​ያ​ዎች ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ እና​ንተ ግን ትጐ​ሰ​ቍ​ላ​ላ​ችሁ፤


ኀጢአተኛ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ ርኩስ ነውና፤ ከጻድቃንም ጋር አንድ አይሆንም።


መዓ​ትን ተዋት፤ ቍጣ​ንም ጣላት፥ እን​ዳ​ት​በ​ድ​ልም አት​ቅና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ የም​በ​ላው እና​ንተ የማ​ታ​ው​ቁት ምግብ አለኝ” አላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለጃ​ን​ደ​ረ​ቦች እን​ዲህ ይላል፥ “ሰን​በ​ቴን ቢጠ​ብቁ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ኝ​ንም ነገር ቢመ​ርጡ፥ በቃል ኪዳ​ኔም ጸን​ተው ቢኖሩ፥


የዐዋቂ ሰው ልብ ለሰውነቱ ኀዘን ነው፤ ደስ ባለውም ጊዜ ከጥል ጋር ግንኙነት የለውም።


ሙሴም አሮ​ንን፥ “አንድ የወ​ርቅ መሶብ ወስ​ደህ ጎሞር ሙሉ መና አግ​ባ​በት፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም ይጠ​በቅ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አኑ​ረው” አለው።


በቤ​ቴና በቅ​ጥሬ ውስጥ ከወ​ን​ዶ​ችና ከሴ​ቶች ልጆች ይልቅ የሚ​በ​ልጥ ስም የሚ​ያ​ስ​ጠራ ቦታን እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የማ​ይ​ጠፋ የዘ​ለ​ዓ​ለም ስም​ንም እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


በልብሱና በጭኑም የተጻፈበት “የነገሥታት ንጉሥና የጌታዎች ጌታ” የሚል ስም አለው።


የሚሰማ ጆሮ ያለው ቢኖር ይስማ፤” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios