Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 28:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም በካ​ህ​ና​ቱና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በቆ​ሙት ሕዝብ ሁሉ ፊት ለሐ​ሰ​ተ​ኛው ነቢይ ለሐ​ና​ንያ ተና​ገረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ነቢዩ ኤርምያስም በካህናቱና በእግዚአብሔር ቤት ቆመው በነበሩት ሕዝብ ሁሉ ፊት፣ ለነቢዩ ለሐናንያ እንዲህ ብሎ መለሰለት፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ነቢዩ ኤርምያስም በካህናቱና በጌታ ቤት በቆሙት ሕዝብ ሁሉ ፊት ለነቢዩ ለሐናንያ ተናገረ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እኔም በካህናቱና በቤተ መቅደስ በቆሙት ሕዝብ ሁሉ ፊት ሐናንያን እንዲህ አልኩት፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ነቢዩ ኤርምያስም በካህናቱና በእግዚአብሔር ቤት በቆሙት ሕዝብ ሁሉ ፊት ለነቢዩ ለሐናንያ ተናገረ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 28:5
5 Referencias Cruzadas  

የፈ​ዳ​ያም ልጆች ዘሩ​ባ​ቤ​ልና ሰሜኤ ነበሩ፤ የዘ​ሩ​ባ​ቤ​ልም ልጆች፤ ሜሱ​ላም፥ ሐና​ንያ፥ እኅ​ታ​ቸ​ውም ሰሎ​ሚት።


ኤር​ም​ያ​ስም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትን​ቢት ሊና​ገር ወደ​ዚያ ልኮት ከነ​በ​ረው ስፍራ ከቶ​ፌት ተመ​ለሰ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት አደ​ባ​ባይ ቆሞ ለሕ​ዝቡ ሁሉ እን​ዲህ አላ​ቸው፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አደ​ባ​ባይ ቁም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት ውስጥ ይሰ​ግዱ ዘንድ ለሚ​መ​ጡት ለይ​ሁዳ ከተ​ሞች ሁሉ ትነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ቃል ሁሉ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ አን​ዲ​ትም ቃል አታ​ጕ​ድል።


ከዚ​ህም በኋላ እን​ዲህ ሆነ፤ በዚያ ዓመት፥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ መን​ግ​ሥት መጀ​መ​ሪያ፥ በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመት በአ​ም​ስ​ተ​ኛው ወር ሐሰ​ተ​ኛው ነቢይ የገ​ባ​ዖን ሰው የዓ​ዙር ልጅ ሐና​ንያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በካ​ህ​ና​ትና በሕ​ዝብ ሁሉ ፊት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረኝ፦


“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር ቁም፤ ይህ​ንም ቃል እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትሰ​ግዱ ዘንድ በእ​ነ​ዚህ በሮች የም​ት​ገቡ ከይ​ሁዳ ያላ​ችሁ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos