Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዮሐንስ 18:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እኔ ለዓ​ለም በግ​ልጥ ተና​ገ​ርሁ፤ አይ​ሁድ ሁሉ በሚ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት በም​ኵ​ራ​ብም፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ሁል​ጊዜ አስ​ተ​ማ​ርሁ፤ በስ​ው​ርም የተ​ና​ገ​ር​ሁት አን​ዳች ነገር የለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እኔ ለዓለም በግልጽ ተናግሬአለሁ፤ አይሁድ በተሰበሰቡበት ምኵራብ፣ በቤተ መቅደስም ሁልጊዜ አስተምሬአለሁ፤ በስውር የተናገርሁት የለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ኢየሱስም መልሶ “እኔ በግልጥ ለዓለም ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በመቅደስ ሁልጊዜ አስተማርሁ፤ በስውርም ምንም አልተናገርሁም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “እኔ ለሰው ሁሉ በግልጥ ተናገርኩ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኲራብም ሆነ በቤተ መቅደስ፥ ዘወትር አስተማርኩ፤ በስውር የተናገርኩት ምንም ነገር የለም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ኢየስስም መልሶ፦ “እኔ በግልጥ ለዓለም ተናገርሁ፤ አይሁድ ሁሉ በሚሰበሰቡበት በምኵራብና በመቅደስ እኔ ሁልጊዜ አስተማርሁ፥ በስውርም ምንም አልተናገርሁም።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 18:20
25 Referencias Cruzadas  

እነሆ፥ እርሱ በገ​ሀድ ይና​ገ​ራል፤ እነ​ርሱ ግን ምንም የሚ​ሉት የለም፤ ይህ በእ​ው​ነት ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ምና​ል​ባት አለ​ቆች ዐው​ቀው ይሆን?


ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።


ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህ​ንም ስሙ፤ እኔ ከጥ​ንት ጀምሬ በስ​ውር አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም፤ ከሆ​ነ​በት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበ​ርሁ፤ አሁ​ንም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና መን​ፈሱ ልከ​ው​ኛል።


ቀን ቀን በመ​ቅ​ደስ ያስ​ተ​ምር ነበር፤ ሌሊት ግን ወጥቶ ደብረ ዘይት በሚ​ባ​ለው ተራራ ያድር ነበር።


ሊገ​ለጥ ወድዶ ሳለ በስ​ውር አን​ዳች ነገር የሚ​ያ​ደ​ርግ ማንም የለ​ምና፤ አንተ ግን ይህን የም​ታ​ደ​ርግ ከሆነ ራስ​ህን ለዓ​ለም ግለጥ።


በየ​ም​ኵ​ራ​ባ​ቸ​ውም ሁሉ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ነበር፤ ትም​ህ​ር​ቱ​ንም ያደ​ንቁ ነበር፤ ሁሉም ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር።


በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ለሕዝቡ “ወንበዴን እንደምትይዙ ሰይፍና ጐመድ ይዛችሁ ልትይዙኝ ወጣችሁን? በመቅደስ ዕለት ዕለት እያስተማርሁ ከእናንተ ጋር ስቀመጥ ሳለሁ አልያዛችሁኝም።


ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተማዎችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።


በስ​ውር ወይም በጨ​ለማ ስፍራ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም፤ ለያ​ዕ​ቆብ ዘር፦ በከ​ንቱ ፈል​ጉኝ አላ​ል​ሁም፤ ጽድ​ቅን የም​ና​ገር፥ ቅን ነገ​ር​ንም የም​ና​ገር እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


ስለ እና​ንተ የም​ና​ገ​ረ​ውና የም​ፈ​ር​ደው ብዙ አለኝ፤ የላ​ከ​ኝም እው​ነ​ተኛ ነው፤ እኔ በእ​ርሱ ዘንድ የሰ​ማ​ሁ​ትን ለዓ​ለም እና​ገ​ራ​ለሁ።”


በጥ​ዋ​ትም ገስ​ግሦ ዳግ​መኛ ወደ ቤተ መቅ​ደስ ገባ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ፤ እር​ሱም ተቀ​ምጦ ያስ​ተ​ም​ራ​ቸው ጀመር።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም በመ​ቅ​ደስ ሲያ​ስ​ተ​ምር ቃሉን ከፍ አድ​ርጎ እን​ዲህ አለ፥ “እኔን ታው​ቁ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ከወ​ዴ​ትም እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ እኔ ራሴ የመ​ጣሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ ነገር ግን እና​ንተ የማ​ታ​ው​ቁት የላ​ከኝ እው​ነ​ተኛ አለ።


በበ​ዓሉ ቀኖች እኩ​ሌ​ታም ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ መቅ​ደስ ወጥቶ ያስ​ተ​ምር ጀመረ።


በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ “ተሳድቦአል፤ እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል?” አለ።


በፊቱ ገልጬ የም​ና​ገ​ር​ለት እርሱ ራሱ ንጉሥ አግ​ሪጳ ያው​ቅ​ል​ኛል፤ ከዚ​ህም የሚ​ሳ​ተው ነገር ያለ አይ​መ​ስ​ለ​ኝም፤ ወደ ጎን የተ​ሰ​ወረ አይ​ደ​ለ​ምና።


እንግዲህ ‘እነሆ፥ በበረሀ ነው፤’ ቢሉአችሁ፥ አትውጡ፤ ‘እነሆ፥ በእልፍኝ ነው፤’ ቢሉአችሁ፥ አትመኑ፤


ደግሞ የሰ​ላሜ ሰው የታ​መ​ን​ሁ​በት፥ እን​ጀ​ራ​ዬን የበላ በእኔ ላይ ተረ​ከ​ዙን አነሣ።


ጴጥሮስም ወደ እርሱ ወስዶ ይገሥጸው ጀመር።


በቅ​ፍ​ር​ና​ሆ​ምም በም​ኵ​ራብ ሲያ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸው ይህን ተና​ገረ፤


እን​ግ​ዲህ እኔን ለምን ትጠ​ይ​ቀ​ኛ​ለህ? የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን የሰ​ሙ​ኝን ጠይ​ቃ​ቸው፤ እኔም የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን እነሆ፥ እነ​ርሱ ያው​ቃሉ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios