Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 2:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 የያ​ዕ​ቆብ ቤት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ወገ​ኖች ሁሉ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ወገን ሁላችሁ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የያዕቆብ ቤት የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እናንተ የያዕቆብ ልጆች የሆናችሁ፤ የእስራኤል ነገድ ሁሉ! እግዚአብሔር የተናገረውን ቃል ስሙ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የያዕቆብ ቤት የእስራኤልም ቤት ወገኖች ሁሉ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 2:4
14 Referencias Cruzadas  

እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ንተ ላይ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ቃል ስሙ።


ስሙ፤ አድ​ምጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና አት​ታ​በዩ።


“የይ​ሁዳ ነገ​ሥ​ታ​ትና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የም​ት​ኖሩ ሆይ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህ ስፍራ ክፉ ነገ​ርን አመ​ጣ​ለሁ፤ የሰ​ማ​ውም ሰው ሁሉ ይደ​ነ​ግ​ጣል፤ ጆሮ​ዎ​ቹ​ንም ይይ​ዛል።


እስ​ራ​ኤል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነበረ፤ የቡ​ቃ​ያው በኵ​ራ​ትም ነበረ፤ የበ​ሉት እንደ በደ​ለ​ኞች ይቈ​ጠ​ራሉ፤ ክፉም ነገር ያገ​ኛ​ቸ​ዋል፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “አባ​ቶ​ቻ​ችሁ ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ ከን​ቱ​ነ​ት​ንም የተ​ከ​ተሉ፥ ከን​ቱም የሆኑ ምን ክፋት አግ​ኝ​ተ​ው​ብኝ ነው?


በዚያ ዘመን ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሁሉ አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል።


“ይህ ሕዝብ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የመ​ረ​ጣ​ቸ​ውን ሁለ​ቱን ወገን ጥሎ​አ​ቸ​ዋል፥ እን​ዲሁ በፊ​ታ​ቸው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ሕዝብ እን​ዳ​ይ​ሆን ሕዝ​ቤን አቃ​ል​ለ​ዋል ያለ​ውን ነገር አት​መ​ለ​ከ​ት​ምን?


“ነገር ግን የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አንተ እን​ዲህ ይላል፦ በሰ​ይፍ አት​ሞ​ትም፤


እና​ንተ ሰነ​ፎች ልበ ቢሶች፥ ዐይን እያ​ላ​ችሁ የማ​ታዩ፥ ጆሮም እያ​ላ​ችሁ የማ​ት​ሰሙ ሕዝብ ሆይ! ይህን ስሙ።


“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር ቁም፤ ይህ​ንም ቃል እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትሰ​ግዱ ዘንድ በእ​ነ​ዚህ በሮች የም​ት​ገቡ ከይ​ሁዳ ያላ​ችሁ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! እው​ነ​ትና ምሕ​ረት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማወቅ በም​ድር ስለ​ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ይወ​ቅ​ሳ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


አሁን፦ ተነሣ፥ በተራሮችም ፊት ተፋረድ፥ ኮረብቶችም ቃልህን ይስሙ ብሎ እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos