ኤርምያስ 6:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድር ሆይ፥ ስሚ! እነሆ ቃሌን ስላልሰሙ፥ ሕጌንም ስለ ጣሉ፥ እኔንም ስለ ናቁ በዚህ ሕዝብ ላይ እንደ ሥራቸው ፍሬ፥ ክፉን ነገር አመጣባቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድር ሆይ፤ ስሚ፤ ቃሌን ስላላደመጡ፣ ሕጌንም ስለ ናቁ፣ በዚህ ሕዝብ ላይ የሐሳባቸውን ውጤት፣ ጥፋትን አመጣባቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድር ሆይ! ስሚ፤ እነሆ፥ ቃሎቼን ስላልሰሙ ሕጌንም ስለ ጣሉት፥ በዚህ ሕዝብ ላይ የሐሳባቸውን ፍሬ፥ ክፉን ነገር አመጣባቸዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድር ሆይ! ስሚ! እነርሱ ያስተማርኳቸውን ሥርዓት ስለ ተቃወሙ፤ ለሕጌም ስላልታዘዙ ስለ ክፉ ሐሳባቸው ሁሉ እቀጣቸው ዘንድ በሕዝቡ ላይ ጥፋትን አመጣለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድር ሆይ፥ ስሚ፥ እነሆ፥ ቃሌን ስላልሰሙ ሕጌንም ስለ ጣሉ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ የአሳባቸውን ፍሬ፥ ክፉን ነገር አመጣባቸዋለሁ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአልና፥ “ሰማይ ስማ፤ ምድርም አድምጪ፤ ልጆችን ወለድሁ፤ አሳደግሁም፤ እነርሱም ዐመፁብኝ።
ስለዚህ ገለባ በእሳት ፍም እንደሚቃጠል፥ በነበልባልም እንደሚበላ፥ እንዲሁ የእነርሱ ሥር የበሰበሰ ይሆናል፤ አበባቸውም እንደ ትቢያ ይበንናል፤ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ሕግ ጥለዋልና፤ የእስራኤልም ቅዱስ የተናገረውን ቃል አቃልለዋልና።
እግሮቻቸውም ለተንኮል ይሮጣሉ፤ ደምን ለማፍሰስም ይፈጥናሉ፤ ሰውን ለመግደል ይመክራሉ፤ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ።
“ሥራቸውንና አሳባቸውን ዐውቄአለሁ፤ እነሆም እኔ እመጣለሁ፤ አሕዛብንና ልሳናትንም ሁሉ እሰበስባለሁ፤ እነርሱም ይመጣሉ፤ ክብሬንም ያያሉ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ሊያመልጡት የማይችሉትን ክፉ ነገር በዚህ ሕዝብ ላይ አመጣለሁ፤ ወደ እኔም ይጮኻሉ፤ እኔ ግን አልሰማቸውም።
አንቺ እኔን ከድተሽኛል፤ እኔንም መከተል ትተሻል፤ ይላል እግዚአብሔር፤ ወደ ኋላሽም ተመልሰሻል፤ ስለዚህ እጄን በአንቺ ላይ ዘርግቼ አጠፋሻለሁ፤ ይቅርም አልላቸውም።
እኔ እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱና፥ እንደ ሥራው ፍሬ እሰጥ ዘንድ ልብን እመረምራለሁ፤ ኵላሊትንም እፈትናለሁ።”
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ቃሌን እንዳይሰሙ አንገታቸውን አደንድነዋልና እነሆ በዚች ከተማና በመንደሮችዋ ሁሉ ላይ የተናገርሁባትን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣለሁ።”
“የይሁዳ ነገሥታትና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህ ስፍራ ክፉ ነገርን አመጣለሁ፤ የሰማውም ሰው ሁሉ ይደነግጣል፤ ጆሮዎቹንም ይይዛል።
እንደ ሥራችሁም ፍሬ እቀጣችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር በዱርዋም ውስጥ እሳትን አነድዳለሁ፤ በዙሪያዋም ያለውን ሁሉ ይበላል።”
ይህም የሆነው ቃሌን ስላልሰሙ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በማለዳ ባሪያዎችን ነቢያትን ወደ እነርሱ ሰድጃለሁና፤ እናንተ ግን አልሰማችሁም፤ ይላል እግዚአብሔር።
ለአሕዛብ አሳስቡ፥ “እነሆ፥ መጡ! ጠላቶች ከሩቅ ሀገር ይመጣሉ፤ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውጁ።
እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳይነድ ለአምላካችሁ ተገረዙ፤ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።
በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውን በሚሹአት ፊት ኤላምን አስደነግጣለሁ። ክፉ ነገርን እርሱም ጽኑ ቍጣዬን አመጣባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ እስካጠፋቸውም ድረስ በኋላቸው ሰይፍን እሰድድባቸዋለሁ።
ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ? ለማንስ አዳኛለሁ? እነሆ፥ ጆሮአቸው ያልተገረዘች ናት፤ ለመስማትም አይችሉም፤ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቃል ለስድብ ሆኖባቸዋል፥ ይሰሙት ዘንድ አልፈቀዱምና።
ጥበበኞች አፍረዋል፤ ደንግጠውማል፤ ተማርከውማል፤ እነሆ የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል፤ ምን ዓይነት ጥበብ አላቸው?
ዐመፅን ለምን ተከላችሁ? ኀጢአትንስ ለምን አጨዳችሁ፤ የሐሰትንም ፍሬ በልታችኋል፤ በሠረገሎችህና በሠራዊትህ ብዛት ታምነሃል።
ሕዝቤ አእምሮ እንደሌላቸው ይመስላሉ፤ አንተም አእምሮህ ተለይቶሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እተውሃለሁ፤ የአምላክህንም ሕግ ረስተሃልና እኔ ደግሞ ልጆችህን እረሳለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርሰዋልና፥ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፥ አባቶቻቸውም የተከተሉት ከንቱ ነገር አስቶአቸዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የይሁዳ ኀጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስላቸውም።
ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳልና የእግዚአብሔርን ክርክር ስሙ።
የሚክደኝን፥ ቃሌንም የማይቀበለውን ግን የሚፈርድበት አለ፤ እኔ የተናገርሁት ቃል እርሱ በመጨረሻዪቱ ቀን ይፈርድበታል።
በፊትህ ሕይወትንና ሞትን፥ በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤
ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትገቡባት ምድር ፈጥናችሁ እንድትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ አስመሰክራለሁ፤ ፈጽሞም ትጠፋላችሁ እንጂ ረዥም ዘመን አትቀመጡባትም።
ኀጢኣት እንደ ምዋርተኝነት ናትና አምልኮተ ጣዖትም ደዌንና ኀዘንን ያመጣል። የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ” አለው።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃልና ከአንተ ጋር አልመለስም” አለው።