ዓመቱም ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደነፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ የከበረውንም የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ የአባቱን የኢዮአቄምን ወንድም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ።
ኤርምያስ 25:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደ የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች! አልቅሱ፤ እናንተም የበጎች አውራዎች! ጩኹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ እረኞች፤ አልቅሱ፤ ዋይ በሉ፤ እናንተ የመንጋው ጌቶች፤ በዐመድ ላይ ተንከባለሉ፤ የምትታረዱበት ቀን ደርሷልና፤ እንደ ውብ የሸክላ ዕቃ ወድቃችሁ ትከሰከሳላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ልትታረዱና ልትበተኑ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደም የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች፥ አልቅሱ ጩኹም፤ እናንተ የመንጋ አውራዎች፥ በአመድ ውስጥ ተንከባለሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተ መሪዎች አልቅሱ፤ እናንተ የሕዝብ ጠባቂዎች ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ‘ዋይ፥ ዋይ!’ በሉ፤ በዐመድ ላይ እየተንከባለላችሁ እዘኑ፤ ሁላችሁም የምትታረዱበት ጊዜ ደርሶአል፤ ውድ የሆነ የሸክላ ዕቃ ሲወድቅ ተሰብሮ እንደሚበታተን፥ እናንተም ትበታተናላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ትታረዱና ትበተኑ ዘንድ ቀናችሁ ደርሶአልና፥ እንደ ተወደደም የሸክላ ዕቃ ትወድቃላችሁና እናንተ እረኞች፥ አልቅሱ ጩኹም፥ እናንተ የመንጋ አውራዎች፥ በአመድ ውስጥ ተንከባለሉ። |
ዓመቱም ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደነፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ የከበረውንም የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ የአባቱን የኢዮአቄምን ወንድም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ።
ስለዚህ እንዲህ ይሆናል፤ ጌታ ሥራውን ሁሉ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ በፈጸመ ጊዜ የአሦርን ንጉሥ የኵሩ ልብን ፍሬ፥ የዐይኑንም ከፍታ ትምክሕት ይቀጣል።
አወዳደቁም እንደ ሸክላ ሠሪ ገንቦ የደቀቀ ይሆናል፤ ሳይራራም ያደቅቀዋል፤ ከስባሪውም እሳት ከማንደጃ የሚወስዱበት፥ ወይም ውኃ ከጕድጓድ የሚቀዱበት ገል አይገኝም።”
ለሚያዋርዱአችሁ ወዮላቸው! እናንተን ግን የሚያዋርዳችሁ የለም፤ የሚወነጅላችሁ እናንተን የሚወነጅል አይደለም፤ ወንጀለኞች ይጠመዳሉ፤ ይያዛሉም፤ ብል እንደበላው ልብስም ያልቃሉ።
እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፤ በበግ ስብ፥ በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ስብ ወፍራለች።
ኀያላን ከእነርሱ ጋር፥ ወይፈኖችም ከኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ፤ ምድራቸውም በደም ትሰክራለች፤ በስባቸውም ትወፍራለች።
ሊይዙኝ ጕድጓድ ቈፍረዋልና፥ ለእግሮችም ወጥመድ ሸሽገዋልና፥ በቤታቸው ጩኸት ይሰማ፤ ድንገትም በላያቸው ወንበዴን አምጣባቸው።
ኢኮንያን ተዋረደ፤ ለምንም እንደማይጠቅም የሸክላ ዕቃ ሆነ፤ እርሱንና ዘሩን ወደማያውቀው ሀገር ወርውረው ጥለውታልና።
“ሰባው ዓመትም በተፈጸመ ጊዜ፥ የባቢሎንን ንጉሥና ያን ሕዝብ ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ የከለዳውያንንም ምድር ለዘለዓለም አጠፋቸዋለሁ።
የገዛ ራሱም ምድር ጊዜ እስኪመጣ ድረስ አሕዛብ ሁሉ ለእርሱና ለልጁ ለልጅ ልጁም ይገዛሉ፤ በዚያን ጊዜም ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት ለእርሱ ይገዙለታል።
“እኔም፦ ይሁን አልሁ፤ በወንዶች ልጆች መካከል እሾምሃለሁ፤ አሕዛብን የሚገዛ ሁሉን ቻይ የሆነ የእግዚአብሔርን ርስት የተመረጠችውን ምድር ለአንተ እሰጥሃለሁ፤ አባቴ ትለኛለህ፤ ከእኔም አትመለስም አልሁ ብለሃልና።
“በእግዚአብሔር ላይ ኰርቶአልና፥ አስክሩት፤ ሞአብም በትፋቱ ላይ ይንከባለላል፤ በእጁም ያጨበጭባል፤ ደግሞ መሳቂያ ይሆናል።
ሞአብንም ለምንም እንደማይጠቅም ዕቃ ሰብሬአለሁና በሞአብ ሰገነት ሁሉ ላይ፥ በአደባባዩም ላይ ልቅሶ አለ፥” ይላል እግዚአብሔር።
ፍሬዋን ሁሉ አድርቁባት፤ ወደ መታረድም ይውረዱ፤ ቀናቸው ደርሳለችና፥ እነሱን የሚበቀሉበት ጊዜ ደርሷልና ወዮላቸው!
የሕዝቤ ልጅ ሆይ፥ ማቅ ልበሺ፤ በራስሺም ላይ አመድ ነስንሺ፥ አጥፊ በላያችን በድንገት ይመጣብናልና ለተወዳጅ ልጅ እንደሚደረግ ልቅሶ መራራ ልቅሶ አልቅሺ።
ሣን። በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶምያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ፥ ሐሤትም አድርጊ፤ የእግዚአብሔር ጽዋ ደግሞ ወደ አንቺ ያልፋልና፥ አንቺም ትሰክሪአለሽ፥ ትራቆቻለሽም።
ድሃውንም ደብድባችኋልና፤ መማለጃንም ከእርሱ ወስዳችኋልና፤ ያማሩ ቤቶችንም መርጣችሁ ሠርታችኋልና፥ ነገር ግን አትኖሩባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታዎችም ተክላችኋል፤ ነገር ግን ወይንን አትጠጡም።
ቍጣዬ በእረኞች ላይ ነድዶአል፥ አውራ ፍየሎችንም እቀጣለሁ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም የይሁዳን ቤት መንጋውን ጐብኝቶአል፥ በሰልፍም ውስጥ እንዳለ እንደ ክብሩ ፈረስ ያደርጋቸዋል።