Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 23:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 “የማ​ሰ​ማ​ር​ያ​ዬን በጎች ለሚ​ያ​ጠ​ፉና ለሚ​በ​ትኑ እረ​ኞች ወዮ​ላ​ቸው!” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “በማሰማሪያ ቦታዬ ያሉትን በጎቼን ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው!” ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 “የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው!” ይላል ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 “የእግዚአብሔር መንጋ የሆነውን ሕዝብ ለሚበትኑና ለሚያጠፉ መሪዎች ወዮላቸው!” ይላል እግዚአብሔር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የማሰማርያዬን በጎች ለሚያጠፉና ለሚበትኑ እረኞች ወዮላቸው! ይላል እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 23:1
30 Referencias Cruzadas  

እረ​ኞች አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን አጥ​ተ​ዋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ለ​ጉ​ት​ምና፤ ስለ​ዚ​ህም መሰ​ማ​ሪ​ያ​ውን አላ​ወ​ቁም፤ መን​ጎ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተበ​ት​ነ​ዋል።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ፈጽሞ ሳያዩ ከገዛ ልባ​ቸው አን​ቅ​ተው ትን​ቢት ለሚ​ና​ገሩ ወዮ​ላ​ቸው!


ብዙ ሕዝብም ባየ ጊዜ፥ እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ተጨንቀው ተጥለውም ነበርና አዘነላቸው።


በግ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ሽን ሁሉ ነፋስ ይወ​ስ​ዳ​ቸ​ዋል፤ ወዳ​ጆ​ች​ሽም ተማ​ር​ከው ይሄ​ዳሉ፤ በዚ​ያን ጊዜም ስለ ክፋ​ትሽ ሁሉ ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ፤ በወ​ዳ​ጆ​ች​ሽም ፊት ቷረ​ጃ​ለሽ።


ብዙ እረ​ኞች የወ​ይ​ኑን ቦታ​ዬን አጥ​ፍ​ተ​ዋል፤ እድል ፈን​ታ​ዬ​ንም አር​ክ​ሰ​ዋል፤ የም​ወ​ድ​ዳ​ት​ንም እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድ​ር​ገ​ዋ​ታል።


“ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነ​ዋል፤ እረ​ኞ​ቻ​ቸው አሳ​ቱ​አ​ቸው፤ በተ​ራ​ሮ​ችም ላይ የተ​ቅ​በ​ዘ​በዙ አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው፤ ከተ​ራራ ወደ ኮረ​ብታ ዐለፉ፤ በረ​ታ​ቸ​ው​ንም ረሱ።


ካህ​ና​ቱም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወዴት አለ? አላ​ሉም፤ ሕጌን የተ​ማ​ሩ​ትም አላ​ወ​ቁ​ኝም፤ ጠባ​ቂ​ዎ​ችም ዐመ​ፁ​ብኝ፤ ነቢ​ያ​ትም በበ​ዐል ትን​ቢት ተና​ገሩ፤ የማ​ይ​ጠ​ቅ​ማ​ቸ​ው​ንም ነገር ተከ​ተሉ።


ጠባቂ ያይ​ደለ፥ በጎ​ቹም ገን​ዘቡ ያይ​ደሉ ምን​ደኛ ግን፥ ተኵላ ሲመጣ ባየ ጊዜ በጎ​ቹን ትቶ ይሸ​ሻል፤ ተኵ​ላም መጥቶ በጎ​ችን ይነ​ጥ​ቃ​ቸ​ዋል፥ ይበ​ት​ና​ቸ​ዋ​ልም።


ሌባ ግን ሊሰ​ር​ቅና ሊያ​ርድ፥ ሊያ​ጠ​ፋም ካል​ሆነ በቀር አይ​መ​ጣም፤ እኔ ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን እን​ዲ​ያ​ገኙ፥ እጅ​ግም እን​ዲ​በ​ዛ​ላ​ቸው መጣሁ።


ስለ​ዚህ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቤን ስለ​ሚ​ጠ​ብቁ እረ​ኞች እን​ዲህ ይላል፥ “በጎ​ችን በት​ና​ች​ኋል፤ አባ​ር​ራ​ች​ኋ​ቸ​ው​ማል፥ አል​ጐ​በ​ኛ​ች​ኋ​ቸ​ው​ምም፤ እነሆ! እንደ ሥራ​ችሁ ክፋት እጐ​በ​ኛ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ፤” አለ።


እና​ን​ተም በጎች፥ የማ​ሰ​ማ​ሪ​ያዬ በጎች፥ ሰዎች ናችሁ፤ እኔም አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


እስ​ክ​ት​በ​ት​ኑ​አ​ቸው ድረስ በእ​ን​ቢ​ያና በት​ከሻ ስለ​ም​ት​ገ​ፉ​አ​ቸው፥ የደ​ከ​ሙ​ት​ንም ሁሉ በቀ​ን​ዳ​ችሁ ስለ​ም​ት​ወ​ጉ​አ​ቸው፥


ሌባ በተ​ያዘ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ያ​ፍር፤ እን​ዲሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ እነ​ር​ሱና ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ውም፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውም፥ ካህ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ውም፥ ነቢ​ያ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ያፍ​ራሉ።


ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ ሌቦ​ችና ወን​በ​ዴ​ዎች ናቸው፤ ነገር ግን፤ በጎች አል​ሰ​ሙ​አ​ቸ​ውም።


ይህን ባት​ሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕ​ቢ​ታ​ችሁ በስ​ውር ታለ​ቅ​ሳ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መንጋ ተሰ​ብ​ሮ​አ​ልና ዐይኔ ታነ​ባ​ለች፤ እን​ባ​ንም ታፈ​ስ​ሳ​ለች።


እንደ ተቀ​ደሱ በጎች፥ በበ​ዓ​ላ​ቶ​ችዋ ቀን እን​ደ​ሚ​ሆኑ እንደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በጎች እን​ዲሁ የፈ​ረ​ሱት ከተ​ሞች በሰ​ዎች መንጋ ይሞ​ላሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


ቍጣዬ በእረኞች ላይ ነድዶአል፥ አውራ ፍየሎችንም እቀጣለሁ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም የይሁዳን ቤት መንጋውን ጐብኝቶአል፥ በሰልፍም ውስጥ እንዳለ እንደ ክብሩ ፈረስ ያደርጋቸዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios