Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሰቈቃወ 4:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሣን። በዖፅ ምድር የም​ት​ኖሪ የኤ​ዶ​ም​ያስ ሴት ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፥ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዋ ደግሞ ወደ አንቺ ያል​ፋ​ልና፥ አን​ቺም ትሰ​ክ​ሪ​አ​ለሽ፥ ትራ​ቆ​ቻ​ለ​ሽም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 አንቺ በዖፅ ምድር የምትኖሪ፣ የኤዶምያስ ሴት ልጅ ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ፤ ነገር ግን ለአንቺም ደግሞ ጽዋው ይደርስሻል፤ ትሰክሪያለሽ፤ ዕርቃንሽንም ትጋለጫለሽ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሳን። በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ ሐሤትም አድርጊ፥ ጽዋው ደግሞ ወደ አንቺ ያልፋል፥ አንቺም ትሰክሪአለሽ ትራቈቻለሽም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እናንተ በዑፅ ምድር የምትኖሩ የኤዶም ሕዝብ ሆይ ደስ ይበላችሁ ሐሴትም አድርጉ! ይሁን እንጂ የእናንተም ጽዋ ተራውን ጠብቆ በመምጣት ላይ ነው፤ እናንተም ሰክራችሁ ትራቈታላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሳን። በዖፅ ምድር የምትኖሪ የኤዶምያስ ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበልሽ ሐሤትም አድርጊ፥ ጽዋው ደግሞ ወደ አንቺ ያልፋል፥ አንቺም ትሰክሪአለሽ ትራቈቻለሽም።

Ver Capítulo Copiar




ሰቈቃወ 4:21
24 Referencias Cruzadas  

“እነሆ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ ኀፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦“ወን​ድ​ሙን በሰ​ይፍ አሳ​ድ​ዶ​ታ​ልና፥ በም​ድር ላይም ማኅ​ፀ​ንን አር​ክ​ሶ​አ​ልና፥ የሚ​ዘ​ል​ፈ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ውን በር​ብ​ሮ​አ​ልና፥ መዓ​ቱ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጠብ​ቆ​አ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የኤ​ዶ​ም​ያስ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


አው​ስ​ጢድ በሚ​ባል ሀገር ስሙ ኢዮብ የተ​ባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው ቅን፥ ንጹ​ሕና ጻድቅ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈራ፥ ከክፉ ሥራም ሁሉ የራቀ ነበር።


በመ​ከራ መካ​ከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ታድ​ነ​ኛ​ለህ፤ በጠ​ላ​ቶች ቍጣ ላይ እጆ​ች​ህን ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፥ ቀኝ​ህም ያድ​ነ​ኛል


በሻፊር የምትቀመጪ ሆይ፥ በዕራቁትነትሽና በእፍረት እለፊ፥ በጸዓናን የምትቀመጠው አልወጣችም፥ የቤትኤጼል ልቅሶ ከእናንተ ዘንድ መኖሪያውን ይወስዳል።


የአ​ብ​ድዩ ራእይ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ኤዶ​ም​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መስ​ማ​ትን ሰማሁ፤ ከባ​ቢን ወደ አሕ​ዛብ ልኮ፥ “ተነሡ፤ በላ​ይ​ዋም እን​ነ​ሣና እን​ው​ጋት።


“የሰው ልጅ ሆይ፥ ጢሮስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ላይ፦ እሰይ፥ ተሰ​በ​ረች፥ ጠፋ​ችም፥ ሕዝ​ቧም ወደ እር​ስዋ ተመ​ለሱ፤ ሞልታ የነ​በ​ረች አለ​ቀች ብላ​ለ​ችና፤


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሞአ​ብና ሴይር፦ እነሆ የይ​ሁዳ ቤት እንደ አሕ​ዛብ ሁሉ ነው ብለ​ዋ​ልና፤


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ በእ​ጆ​ችህ አጨ​ብ​ጭ​በ​ሃ​ልና፥ በእ​ግ​ሮ​ች​ህም አሸ​ብ​ሽ​በ​ሃ​ልና፥ ሰው​ነ​ት​ህም በእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ላይ ደስ ብሎ​አ​ታ​ልና፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ እነሆ ጽዋ​ውን ያል​ተ​ገ​ባ​ቸው ሰዎች ጠጥ​ተ​ው​ታል፤ አን​ተም መን​ጻ​ትን ትነ​ጻ​ለ​ህን? እን​ግ​ዲህ አት​ነ​ጻም መጠ​ጣ​ትን ትጠ​ጣ​ለ​ህና።


አንተ ጐበዝ፥ በጕ​ብ​ዝ​ናህ ደስ ይበ​ልህ፥ በጕ​ብ​ዝ​ና​ህም ወራት ልብ​ህን ደስ ይበ​ለው፥ በል​ብ​ህም መን​ገድ፥ ዐይ​ኖ​ች​ህም በሚ​ያ​ዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለ​ዚህ ነገር ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ፍርድ እን​ዲ​ያ​መ​ጣህ ዕወቅ።


በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በአ​ካዝ ምክ​ን​ያት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሁ​ዳን አዋ​ረ​ደው፤ እርሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ርቆ​አ​ልና።


የሪ​ሶን ልጆ​ችም እነ​ዚህ ናቸው፤ ዑሳ፥ አራን።


በክብር ፋንታ እፍረት ሞልቶብሃል፣ አንተ ደግሞ ጠጥተህ ተንገድገድ፣ የእግዚአብሔር የቀኙ ጽዋ ይመለስብሃል፥ እፍረትም በክብርህ ላይ ይሆናል።


ስለ ኤዶ​ም​ያስ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴ​ማን ጥበብ የለ​ምን? ከብ​ል​ሃ​ተ​ኞ​ችስ ምክር ጠፍ​ቶ​አ​ልን? ጥበ​ባ​ቸ​ውስ አል​ቆ​አ​ልን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios