Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 2:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በባ​ሕ​ሩም መር​ከብ ሁሉ ላይ፥ በተ​ጌጡ ጣዖ​ታ​ትም ምስል ሁሉ ላይ ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የተርሴስን መርከቦች ሁሉ፣ የክብር ጀልባዎችን ሁሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የተርሴስን መርከቦች ሁሉ፤ የክብር ጀልባዎችን ሁሉ የሚያዋርድበት ቀን አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እጅግ የተዋቡ ዕቃዎችንና የተርሴስ መርከቦችን እንኳ ያሰጥማል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በተርሴስም መርከብ ሁሉ ላይ፥ የሚያማምሩ ጣዖታትም ሁሉ ላይ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 2:16
13 Referencias Cruzadas  

ለን​ጉ​ሡም ከኪ​ራም መር​ከ​ቦች ጋር በባ​ሕር ውስጥ የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ነበ​ሩት፤ በየ​ሦ​ስት ዓመ​ትም አንድ መር​ከብ ከተ​ር​ሴስ ወር​ቅና ብር፥ የተ​ቀ​ረ​ጸና የተ​ደ​ረ​ደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።


ስለ ጢሮስ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት። የኬ​ል​ቀ​ዶን መር​ከ​ቦች ሆይ፥ አል​ቅሱ፤ ጠፍ​ተ​ዋ​ልና፤ እን​ግ​ዲ​ህም ከኬ​ጤ​ዎን ሀገር አይ​መ​ጡ​ምና ማር​ከ​ውም ይወ​ስ​ዱ​አ​ቸ​ዋ​ልና።


የመርከባቸውንም ጭነት ከእንግዲህ ወዲህ የሚገዛ የለምና የምድር ነጋዴዎች ያለቅሱላታል፤ ያዝኑላትማል፤


ደሴ​ቶች እኔን ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ የተ​ር​ሴ​ስም መር​ከ​ቦች አስ​ቀ​ድ​መው ይመ​ጣሉ፤ ልጆ​ችሽ ስለ ከበ​ረው ስለ እስ​ራ​ኤል ቅዱስ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ወር​ቅና ብር ይዘው ከሩቅ ሀገር ይመ​ጣሉ።


በኀ​ይ​ለኛ ነፋስ የተ​ር​ሴ​ስን መር​ከ​ቦች ትቀ​ጠ​ቅ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ።


በዚ​ያ​ችም ምድር የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ አጥ​ፉ​አ​ቸው፤ የተ​ቀ​ረ​ጹ​ት​ንም ድን​ጋ​ዮ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ታጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ት​ንም ምስ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ ታጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ በኮ​ረ​ብታ ላይ ያሉ​ትን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም ታፈ​ር​ሳ​ላ​ችሁ፤


በባሕርም ከሚኖሩ ሕይወት ካላቸው ፍጥረቶች ሲሶው ሞተ፤ የመርከቦችም ሲሶው ጠፋ።


ሰውም ሁሉ ይዋ​ረ​ዳል፤ የሰ​ውም ኵራት ይወ​ድ​ቃል፤ በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።


እና​ንተ የኬ​ል​ቀ​ዶን መር​ከ​ቦች ሆይ፥ ምሽ​ጋ​ችሁ ፈር​ሶ​አ​ልና ዋይ በሉ።


በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ምል​ክት አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ከሞት የዳ​ኑ​ትን ዝና​ዬን ወዳ​ል​ሰሙ፥ ክብ​ሬ​ንም ወዳ​ላዩ ወደ አሕ​ዛብ ወደ ተር​ሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ኤላድ በሩቅ ወዳሉ ደሴ​ቶች እል​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ክብ​ሬን ይና​ገ​ራሉ።


የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ሸቀ​ጥ​ሽን የሚ​ሸ​ከሙ ነበሩ፤ አን​ቺም ተሞ​ል​ተሽ ነበር፤ በባ​ሕ​ርም ውስጥ እጅግ ከበ​ርሽ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios