Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 34:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት በባ​ሶራ፥ ታላ​ቅም እርድ በኤ​ዶ​ም​ያስ ምድር አለ​ውና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ በደም ተሞ​ል​ታ​ለች፤ በበግ ስብ፥ በፍ​የል ደምም፥ በአ​ው​ራም በግ ስብ ወፍ​ራ​ለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተነክራለች፤ ሥብ ጠግባለች፤ በበግ ጠቦትና በፍየል ደም፣ በአውራም በግ ኵላሊት ሥብ ተሸፍናለች። እግዚአብሔር በባሶራ ከተማ መሥዋዕት፣ በኤዶምም ታላቅ ዕርድ አዘጋጅቷልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ጌታ መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና፥ የጌታ ሰይፍ በደም ትርሳለች፤ ስብ ትጠግባለች፤ በበግ ጠቦትና በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ኩላሊት ስብ ትወፍራለች።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ለመሥዋዕት የቀረቡ የበግና የፍየል ጠቦቶች በሚሠዉበት ጊዜ ደማቸውና ስባቸው ሰይፉን እንደሚሸፍን የእርሱም ሰይፍ በኤዶማውያን ደምና ስብ ይሸፈናል፤ እግዚአብሔር ይህን መሥዋዕት በቦጽራ ከተማ፥ ይህንንም ታላቅ ዕርድ በኤዶም ምድር ያቀርባል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እግዚአብሔር መሥዋዕት በባሶራ፥ ታላቅም እርድ በኤዶምያስ ምድር አለውና የእግዚአብሔር ሰይፍ በደም ተሞልታለች፥ በስብም፥ በበግ ጠቦትና በፍየል ደምም፥ በአውራም በግ ኵላሊት ስብ ወፍራለች።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 34:6
25 Referencias Cruzadas  

ከሞ​ቱት ደምና ከኀ​ያ​ላን ስብ፥ የዮ​ና​ታን ቀስት ባዶ​ዋን አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ የሳ​ኦ​ልም ሰይፍ ባዶ​ዋን አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም።


ባላ​ቅም ሞተ፤ በእ​ር​ሱም ፋንታ የባ​ሶራ ሰው የዛራ ልጅ ኢዮ​ባብ ነገሠ።


በመ​ከራ መካ​ከል እንኳ ብሄድ፥ አንተ ታድ​ነ​ኛ​ለህ፤ በጠ​ላ​ቶች ቍጣ ላይ እጆ​ች​ህን ትዘ​ረ​ጋ​ለህ፥ ቀኝ​ህም ያድ​ነ​ኛል


አር​ኤ​ል​ንም አስ​ጨ​ን​ቃ​ለሁ፤ ይህ​ችም ኀይል፥ ይህ​ችም ብዕል የእኔ ትሆ​ና​ለች፥


ሰይፌ በሰ​ማይ ሆና ሰከ​ረች፤ እነሆ፥ በኤ​ዶ​ም​ያ​ስና በሚ​ጠ​ፉት ሕዝብ ላይ ለፍ​ርድ ትወ​ር​ዳ​ለች።


ከኤ​ዶ​ም​ያስ፥ ከባ​ሶራ የሚ​መጣ፥ ልብ​ሱም የቀላ፥ የሚ​መካ ኀይ​ለኛ፥ አለ​ባ​በ​ሱም ያማረ፥ ይህ ማን ነው? ስለ ጽድቅ የም​ከ​ራ​ከር፥ ስለ ማዳ​ንም የም​ፈ​ርድ እኔ ነኝ።


መጭ​መ​ቂ​ያ​ውን ብቻ​ዬን ረግ​ጫ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አል​ነ​በ​ረም፤ በቍ​ጣ​ዬም ረገ​ጥ​ኋ​ቸው፤ በመ​ዓ​ቴም ወደ መሬት ጣል​ጥ​ህ​ዋ​ቸው፤ ደማ​ቸ​ው​ንም በም​ድር ላይ አፈ​ሰ​ስሁ፤ ልብ​ሴም ሁሉ በደም ታለለ።


እኔም ለሰ​ይፍ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሁላ​ች​ሁም በሰ​ይፍ ትገ​ደ​ላ​ላ​ችሁ፤ በፊቴ ክፉ ነገር አደ​ረ​ጋ​ችሁ፤ ያል​ወ​ደ​ድ​ሁ​ት​ንም መረ​ጣ​ችሁ እንጂ በጠ​ራ​ኋ​ችሁ ጊዜ አል​መ​ለ​ሳ​ች​ሁ​ል​ኝ​ምና፥ በተ​ና​ገ​ር​ሁም ጊዜ አል​ሰ​ማ​ች​ሁ​ኝ​ምና።”


ወራ​ዶች ወደ ዱር ሁሉ መጥ​ተ​ዋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ ከም​ድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይበ​ላ​ልና፤ ለሥጋ ለባሽ ሁሉ ሰላም የለም።


ትታ​ረ​ዱና ትበ​ተኑ ዘንድ ቀና​ችሁ ደር​ሶ​አ​ልና፥ እንደ ተወ​ደደ የሸ​ክላ ዕቃ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ች​ሁና እና​ንተ እረ​ኞች! አል​ቅሱ፤ እና​ን​ተም የበ​ጎች አው​ራ​ዎች! ጩኹ።


ያ ቀን ጠላ​ቶ​ቹን የሚ​በ​ቀ​ል​በት የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የበ​ቀል ቀን ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ በልቶ ይጠ​ግ​ባል፤ በደ​ማ​ቸ​ውም ይሰ​ክ​ራል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት በሰ​ሜን ምድር በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ ነውና።


ባሶራ ምድረ በዳ፥ መሰ​ደ​ቢ​ያና መረ​ገ​ሚ​ያም እን​ድ​ት​ሆን በራሴ ምያ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከተ​ሞ​ች​ዋም ሁሉ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ባድማ ይሆ​ናሉ።


ስለ ኤዶ​ም​ያስ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴ​ማን ጥበብ የለ​ምን? ከብ​ል​ሃ​ተ​ኞ​ችስ ምክር ጠፍ​ቶ​አ​ልን? ጥበ​ባ​ቸ​ውስ አል​ቆ​አ​ልን?


ፍሬ​ዋን ሁሉ አድ​ር​ቁ​ባት፤ ወደ መታ​ረ​ድም ይው​ረዱ፤ ቀና​ቸው ደር​ሳ​ለ​ችና፥ እነ​ሱን የሚ​በ​ቀ​ሉ​በት ጊዜ ደር​ሷ​ልና ወዮ​ላ​ቸው!


እንደ ጠቦ​ቶ​ችና እንደ አውራ በጎች፥ እንደ አውራ ፍየ​ሎ​ችም ወደ መታ​ረድ አወ​ር​ዳ​ቸ​ዋ​ለሁ።


ወግ​ተሽ ትገ​ድሊ ዘንድ፥ ታብ​ረ​ቀ​ር​ቂም ዘንድ ተሳዪ፤ ትገ​ድ​ሊም ዘንድ፥ ዕን​ጨ​ቱ​ንም ሁሉ ትጥዪ ዘንድ ጨክኚ፤


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ በላዩ ደስ እን​ዳ​ለህ፥ እን​ዲሁ አደ​ር​ግ​ብ​ሃ​ለሁ፤ የሴ​ይር ተራራ ሆይ! አን​ተና መላው ኤዶ​ም​ያስ ባድማ ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ለህ።”


ተራ​ሮ​ች​ህ​ንም በተ​ገ​ደ​ሉት ሰዎች እሞ​ላ​ለሁ፤ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ች​ህና በሸ​ለ​ቆ​ዎ​ችህ፥ በፈ​ሳ​ሾ​ች​ህም ሁሉ ላይ በሰ​ይፍ የተ​ገ​ደ​ሉት ሁሉ ይወ​ድ​ቃሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦“ወን​ድ​ሙን በሰ​ይፍ አሳ​ድ​ዶ​ታ​ልና፥ በም​ድር ላይም ማኅ​ፀ​ንን አር​ክ​ሶ​አ​ልና፥ የሚ​ዘ​ል​ፈ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ደ​ነ​ግ​ጠ​ውን በር​ብ​ሮ​አ​ልና፥ መዓ​ቱ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ጠብ​ቆ​አ​ልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የኤ​ዶ​ም​ያስ ኀጢ​አት መቅ​ሠ​ፍ​ቴን ከማ​ድ​ረግ አል​መ​ለ​ስ​ላ​ቸ​ውም።


የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአልና፥ እግዚአብሔር መሥዋዕትን አዘጋጅቶአልና፥ የጠራቸውንም ቀድሶአልና በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ዝም በሉ።


በላሙ ቅቤ፥ በበ​ጉም ወተት፥ ከፍ​የል ጠቦ​ትና ከላም፥ ከጊ​ደ​ሮ​ችና ከበ​ጎች ስብ ጋር፥ ከፍ​ትግ ስንዴ ጋር መገ​ባ​ቸው፤ የዘ​ለ​ላ​ው​ንም ደም የወ​ይን ጠጅ አድ​ር​ገው ጠጡ።


ሰይ​ፌን እንደ መብ​ረቅ እስ​ላ​ታ​ለሁ፤ እጄም ፍር​ድን ትይ​ዛ​ለች፤ ለሚ​ጠ​ሉ​ኝም ፍዳ​ቸ​ውን እከ​ፍ​ላ​ለሁ፤ ጠላ​ቶ​ች​ንም እበ​ቀ​ላ​ለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos